መካከለኛ ቢኮልኛ
ከውክፔዲያ
መካከለኛ ቢኮልኛ በፊልፒንስ የሚነገር ቋንቋ ነው። ከቢኮልኛ ቋንቋዎች መሀከል አንድ አባል ነው። 2.5 ሚሊዮን ተናጋሪዎች አሉ። ዛሬ በላቲን አልፋቤት ቢጻፍም ድሮ (ከስፓኒሾች አስቀድሞ) በባይባዪን ጽሕፈት ይጻፍ ነበር። አንዳንድ ቃላት ከእስፓንኛ ወይም ከሳንስክሪት በብድር ተወስደዋል።