መጠነ እንቅፋት

ከውክፔዲያ
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

ተመልከት · ውይይት · ቀይር

የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት (ሬዚስታንስ) የሚባለው አንድ ኤሌክትሪክ አባል በውስጡ ሊያልፍ የሚሞክር የኤሌክትሪክ ጅረትን የሚያደናቅፍበት መጠን ልኬት ነው። የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት ከሰበቃ ጋር ተመሳሳይ ባህርይ አለው።

የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት የተደረሰበት በ1819 ዓ፣ም በጆርጅ ኦም ሲሆን፤ በዚህ ሰው ጥናት መሰረት የአንድ ነገር ኤሌክትሪካዊ መጠነ እንቅፋት በዚያ ነገር ላይ ያለ የቮልቴጅ ለ በውስጡ የሚያልፍ ጅረት ሲካፈል ጋር እኩል ነው። በሒሳብ ቋንቋ፡ የኦም ህግ

R የነገሩ መጠነ እንቅፋት ሲሆን የሚለካ በኦም ወይንም ohm (Ω) ነው
V ነገሩን የሚሻገር ቮልቴጅ ሲሆን የሚለካውም በ ቮልት ወይንም volt (V) ነው
I በነገሩ ውስጥ ሰንጥቆ ሚያልፍ የኤሌክትሪክ ጅረት ሲሆን የሚለካውም በአምፔር ወይንም amperes (A) ነው

ለብዙ ቁሶችና ሁኔታዎች፣ የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት R ጸንቶ የሚቆይ ቋሚ ቁጥር ነው። ማለት በኤሌክትሪክ ጅረትና በቮልቴጅ መጠን አይቀየርም። እነዚህ ነገሮች ኦማዊ ቁሶች ይባላሉ። ይዩ

የኤሌክትሪክ አባላት መጠነ እንቅፋት መጠን ስሌት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቀጥተኛ ጅረትመጠነ እንቅፋት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአንድ ሽቦ መጠነ እንቅፋት መጠን በርዝመቱና በስፋቱ ይወሰናል። የሽቦው ርዝመት በጨመረ ቁጥር እንቅፋቱ እየጨመረ ይሄዳል፣ በአንጻሩ ስፋቱ ሲጨምር እንቅፋቱ ይቀንሳል። ልክ ውሃ በሰፊ ቱቦ ውስጥ በቶሎ ሊሄድ እንደሚችልና፣ በረጅም ቱቦ ውስጥ ብዙ ሰበቃ ስለሚገጥመው በቀስታ እንደሚጓዝ ሁሉ። ከዚህ በተጨማሪ የሽቦው መጠነ እንቅፋት ሽቦው ከተሰራበት ዕቃ ተፈጥሮ ጋር ይዛመዳል። ስለሆነም የአንድ ሽቦን መጠነ እንቅፋት በሒሳብ ለማስላት የሚከተለው ቀመር ይጠቅማል፡

ኤዚህ ላይ፤ የሽቦው ርዝምት በሜትር meters [m], A የሽቦው ጎናዊ ስፋት በ ካሬ ሜትር square meters [m²], እና ρ (ግሪክ ሮ) ሽቦው የተሰራበት ቁስ ልዩ መጠነ እንቅፋት ሲሆን የሚለካውም በ ኦም-ሜተር ወይንም ohm-meters (Ω m) ነው።

ምሳሌ: አንድ ከመዳብ የተሰራ ሽቦ ርዝመቱ 5 ሜትር ቢሆንና ፣ የጎን ፊቱ ሬዲየስ 2mm ቢሆን፣ እንቅፋቱ ስንት ነው?

መፍትሔ:

የመዳብ ልዩ መጠነ እንቅፋት መጠን () ከኢንተርኔት እንደሚገኝ Ω m. ነው
የሽቦው የጎን ስፋት () በሒሳብ ሲሰላ ካሬ ሜትር ነው።
የሽቦው ርዝመት () ደግሞ ሜትር ነው።

ስለዚህ፣ የሽቦውመጠነ እንቅፋት መጠን

ነው ማለት ነው።

የአመንቺ ጅረት መጠነ እንቅፋት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአመንቺ ጅረት በሽቦ ውስጥ ሲፈስ የሚያጋጥመው ተቃውሞ መጠነ እንቅፋት ብቻ ሳይሆን ከጅረቱን መቀያየር ጋር የሚነሱ የየኤሌክትሪክ እና የመግነጢስ መስኮች ተቃውሞዎች ጭምር ናቸው። ይህ የኤልክትሮ መግነጢስ ተቃውሞ ሪአክታንስ ወይንም አድኅሮት ተብሎ ሲስላ፣ የመጠነ እንቅፋት ና የአድኅሮት ጥምር ተቃውሞ ኢምፔዳንስ ወይንም ተቃውሞ ይሰኛል።


ተግባራዊ መጠነ እንቅፋት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኤሌክትሪክ መጠነ እንቅፋት (ሬዚስተር) በውኑ አለም የቅዋሜን ጽንሰ ሐሳብ ለመተግበር የሚረዱ መሳሪያዎች ናቸው። ዋና ጥቅማቸውም የሚመነጨው የቅዋሜያቸው መጠን አስቀድሞ ስለሚታወቅ የኤሌክትሪክ ጅረትን በተፈለገው መልኩ ለመቀያየር ያስችላሉና። resistance.

የተለያዩ አይነት የኤሌክትሪክ ተቃዋሚዎች
የተለያዩ አይነት የኤሌክትሪክ ተቃዋሚዎች

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፡1. ^  አልፎ አልፎ ያሉ አንድ አንድ ነገሮች፣ የኦምን ህግ አይከተሉም። ስለሆነም የቮልቴጃቸውና የጅረታቸው ውድር ሊቀያየር ይችልላል። ስልሆነም የ I–V ግራፍአቸዎን ኩርባ ግልባጭ እንደ ውሱን ቋሚ መጠነ እንቅፋት መውሰድ ግድ ይላል።}}