ሚካኤል

ከውክፔዲያ
ቅዱስ ሚካኤል
ኅዳር ፲፪ - በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
ኅዳር ፲፪ - በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
ሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል
መዐረግ የስድስቱ ሊቃነመላዕክት አለቃ
፩ኛ ቅዱስ ገብርኤል
፪ኛ ቅዱስ ሩፋኤል
፫ኛ ቅዱስ ራጉኤል
፬ኛ ቅዱስ ፋኑኤል
፭ኛ ቅዱስ ዑራኤል
፮ኛ ቅዱስ አፍኒን
እንዲሁም የ፺፱ ነገደ መላእክት
፩ኛ በዓለ ንግሥ ኅዳር ፲፪ እስራኤላውያንን ቀይ ባሕርን ያሻገረበት
፪ኛ በዓለ ንግሥ ሰኔ ፲፪ የባሕራምን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት
ሚካኤል ማለት ዕፁብ ድንቅ ነገር


ሚካኤል (ዕብራይስጥ: מִיכָאֵל‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል, ሲተረጎም፡ 'ማንነው እንደ እግዚአብሔር?'; በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl; በላቲን: Michahel-ሲነበብ፡ ሚካኤል; በአረቢኛ: ميخائيل‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል) በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላዕክት ተብሎ ይጠራል

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት


ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት - ኦርና አውድማ

መላእክት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

የቅዱስ ማካኤልን ድርሳን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ ድርሳነ ሚካኤል

በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ይመለከቱ

ሰውን ይረዳሉ ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/

ስግደት ይገባቸዋል ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15

የቅዱስ ሚካኤል ስሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሚካኤል ማለት << መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው>> ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው መልሱ የለም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ - ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ ነው፡፡ ወደ ቅዱስ መጽሐፍ ስንገባ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች እንመለከታለን፡፡ በመጀመሪያ (ኢያሱ 5÷13-15) እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ ይላል፡፡ ይህን ጥቅስ ልብ ብለን ብናጤነው ለሌላው ሁሉ መርህ ይሆናልና ጥቂት ለማብራራት እንሞክራለን፡፡

እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱ ለኢያሱ ‹‹…በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆነው እንዲሁ ካንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውህም፡፡…›› (ኢያሱ 1÷1-9) በማለት ምን ያህል እንዳከበረው ያስረዳል፡፡ እስራኤላውያን አሞራውያንን በወጉ ጊዜ ቀኑ ስለመሸባቸው ከመደበኛው የተፈጥሮ ሕግ ውጭ ቀኑ እንደማይጨልምና መዓልቱ እንዲረዝም ኢያሱ በጸሎት ፈጣሪውን ስለጠየቀ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ቀኑን አስረዝሞ ከሰማይ በረድ አዝንሞ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት የፈጸመውን አስደናቂ ተአምር እንዲህ ብሎ ጸፏል፡፡

‹‹...ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል (ልመና) የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም›› (ኢያ 10÷12-14) በማለት ተገልጿል፡፡ በጠቅላላው ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ የአሕዛብ ምሽጐችን አፍርሶ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሰ ኢያሱ ነው፡፡

ይህ የእስራኤል መሪ በእጅ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጸለት ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን አላወቀም፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም ከመልአኩ የተሰጠው መልስ ታላቅ መሪና ነቢይ የሆነውን የኢያሱን አስተሳሰብ ለወጠው፡፡ ይኸውም <<ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ>> የሚለውን ቃል ሲሰማ ኢያሱ በፊቱ የቆመው ተራ ወታደር ሳይሆን የመላእክት ሠራዊት አለቃ ከሙሴ ሳይለይ የእስራኤልን ሕዝብ የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ <<ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው>> በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ አንተ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ለኢያሱ የምትነግረኝ ምንድነው; በማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም መላእክት ጌቶች ይባላሉ፡፡ ጌትነታቸውም የጸጋ ጌትነት ነው፡፡

ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛማ ኃጢአተኞች ጌታዬ፤ ቀዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ…በማለት የአክብሮት (የጸጋ) ስግደት በመስገድ ብንለምነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጭ አልወጣንም፡፡ የፈጣሪን ክብር ለፍጡር አልሰጠንም፡፡ ተሳስታችኋል የሚለን ሰው ቢኖር እኛ አብነት ያደረግነው የእግዚአብሔር ወዳጅ ኢያሱን ስለሆነ ኢያሱም ተሳስተሃል ይባል፡፡ መልአኩም ኢያሱ ያቀረበለትን የአክብሮት ስግደትና ጥያቄ በመቀበል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን መልእክት ነገረው፡፡ ኢያሱም ትእዛዙን ፈጸመ፡፡

የእግዚአብሔር ሠራዊት ጌታ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህም ማለት መላእክትን ፈጥሮ የሚገዛ፣ የሚያዛቸው፣ የሚቀድሳቸው ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ የሚለው ከፈጣሪ በታች በመላእክት ላይ በፈጣሪ የተሾመ ማለት ነው፡፡ መላእክት አለቆቻቸውን ያከብራሉ፤ ለእነሱም ይታዘዛሉ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ ስለሆነ ከትእዛዙ አይወጡም፤ ሠራዊተ መላእክት የሚያከብሩትንና የሚታዘዙለትን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እኛም እንደ ኢያሱ እናከብረዋለን እንታዘዘዋለን፡፡ መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ <<በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና…>>(ዘጸ.23÷20-22) በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ጊዜ ብቻ ለሙሴና ለሕዝቡ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን እስከዛሬና ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ✞✞✞ በስመ ሥላሴ ✞✞✞

† ♥ † እስጢፋኖስም ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ።† ♥ †(የሐዋ.ሥራ ፯፡፶፱-፷)

እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖ ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!! † ♥ † ሰው ግን ዓለምን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢጎዳ ምን ይረባዋል/ምን ይጠቅመዋል?† ♥ † ማቴ.፲፮፡፳፮ የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው። መዝ. 115/116፡15 † ♥ †እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ /መከራዬን ሳይሰለች/ ዕለት ዕለት ይከተለኝ † ♥ †፡፡ ማቴ ፲፡፴፰-፵፪ † ♥ † ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ፣ እንዲሁም የሚሰደዱ ብጹዓን ይጠግባሉና፣ መጽናናትንም ያገኛሉና…† ♥ † ጌታ በተራራ ስብከቱ ከተናገራቸው፣ ካስተማራቸው የሕይወት ምግብ የሆነ ቃሉ ማቴ.፭፡፩-ፍጻሜ ቅዱስ እስጢፋኖስ በፍርድ አደባባይ ሲቆምና ሲከሠስ እውነቱን መናገሩ ሕይወቱን እንደሚያስከፍለው እያውቀ፡፡ እውነቱን መናገር አልፈራም፡፡ አያችሁ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነበር ያስተዋለው፡፡ ውጤቱ ምንም ይሁን፡፡ እግዚአብሔር በእውነት የተሞላን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ የክርስቶስ ምስክር ሆነው የተሰዉት ቅዱሳን የክብር አክሊል የተቀዳጁት ለእውነት ስለሞቱ ነው፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ሕያዋን ናቸው፡፡ በዘላለማዊ ደስታም ከእግዚአብሔር ጋር ኖረዋል፡፡ እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር። የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። በዚያን ጊዜ። በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና። ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ። በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። ፮፡፰-፲፭) “ይህ እንዴት ያለ ይቅርታ ነው? ልክ ጌታ በዚያ በመከራ ሰዓት ብዙ መከራ ሲያጸኑበት አባት ሆይ የሚያደርጉት አያቁምና የቅር በላቸው ብሎ የፍቅር አምላክ ይቅርታ እንዳደረገላቸው ሁላ የጌታው ተከታይ የሆነው፤ እስጢፋኖስም።” “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።” (የሐዋ.ሥራ ፯፡፶፱-፷) የሰማዕቱ በረከት ይደርብን እስከ ሞት ድረስ ለአምላካችን እንድንታመን እርሱ ይርዳን፡፡ እስከ መጨረሻ ድረስ የታመንህ ሁን የህይወት አክሊል እሰጣሃለሁ ራዕይ 2፡10 ለዚህ ነው እኮ ቅ/ጳውሎስ “እሩጫዬን ጨርሻለሁ ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ ከእንግዲህ የሕይወት አክሊል ይጠብቀኛል” ያለው ፪ጢሞ.፬፡፮-፯ የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ለመስቀሉ ክቡር አሜን ። ይቆየን ጊዜ ሕዝበ እስራኤልን ፊት ፊት እየመራ ጠላቶቻቸው አሕዛብን አጥፍቶ ምድረ ርስትን ምድራዊት ኢየሩሳሌምን እንዳወረሳቸው ዛሬም ይኸው መልአክ ቅዱስ ማካኤል እስራኤል ዘነፍስ የተባልን ህዝበ ክርስቲያንን ፊት ፊት እየመራ ጠላቶቻችን ሠራዋተ አጋንንትን እያጠፋ ምድረ ርስት ወደተባለች ሰማየ ሰማያት ያገባናል፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ለአዲስ ኪዳን ሕዝብ ምሳሌ ስለሆነ በታሪክነቱ ብቻ ተነግሮ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ኦሪት ሰም ሲሆን ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ወርቅ ነውና፡፡

ይህ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ያወጣ፣ በበረሃ 4ዐ ዓመት የመራቸው፣ ምድር ርስትን ያወረሳቸው መሆኑን በሌላ ስፍራ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹…በእስራኤል ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፊቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፡፡›› (ዘጸ.14÷15-20) በዚህ መሠረት እስራኤልን ይመራ የነበረው የእዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ እንዲሁም በኮሬብ ተራራ እግዚአብሔር ለሙሴ ሐመልማል ከነበልባል ተዋሕዶ በተገለጸለት ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አልተለየም ነበር፡፡ (ዘጸ.3÷1-6፣ የሐዋ. 7÷30-34) በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ (መዝ.33÷7) ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ (ቅዱስ ሚካኤል) እግዚአብሔርን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋል (በኢሳ.37÷36) ›› የእግዚአብሔር መልአክ(ቅዱስ ሚካኤል) መጣ፡፡ ከአሞራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ…›› በማለት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝቅያስን እንዴት እንዳዳነው ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

በዳን.10÷13 ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል /ዳን.10÷21/፡፡

በዚሁ በትንቢተ ዳንኤል ም.12÷1 ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል በማለት ታላቅነቱን፤ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡

ከዚህም ሌላ ዲያብሎስ ከነሠራዊቱ በእግዚአብሔር ላይ ባመፀ ጊዜ ከክብሩ ያዋረደው ወደምድር የጣለው ቅዱስ ሚካኤል ቅዱሳን መላእክትን በመምራት ከዲያብሎስና ከሠራዊቱ ጋር ስላደረገው ጦርነትና ስለተቀዳጀው ድል ቅዱስ ዮሐንስ እንዲሀ በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፡፡ አልቻላቸውምም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም፡፡ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው፡፡ ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀድሞው እባብ ወደ ምድር ተጣለ፡፡ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ…›› (ራእ.12÷7-9) ዛሬም ቅዱስ ሚካኤል ሰዳዴ አጋንት አጋንንትን የሚያሳድድ በመሆኑ ከሰይጣንና ከሠራዊቱ መከራ እንዲያድናቸው በጸሎት ለሚለምኑት በቃል ኪዳኑ ለሚማፀኑት ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ይታደጋቸዋል፡፡ በዙሪያቸው እየከተመ አጥር ቅጥር ሆኖ ይጠብቃቸዋል፡፡ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድናቸዋል (መዝ.33÷7)፡፡

በመልእክተ ይሁዳ ቁ.9 ‹‹የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም›› በማለት ቅዱስ ሚካአል ዲያበሎስን እንኳ እግዚአብሔር ይፍረድብህ ከማለት በቀር ሌላ ቃል አለመናገሩ ታጋሽነቱን ያሳያል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ክብር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ሚካኤል ለማንም ያልተሰጠ እጅግ ታላቅ የሆነ ክብር እንደተሰጠው ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይኸውም በዕለተ ምጽአት ጌታችን ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በክበበ ትስብአት በግርማ መለኮት በሚመጣበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሙታን ላይ ሥልጣን የተሰጠው ለዚሁ ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ገልጾታል፡፡ ‹‹እነሆ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ ሁላችን አናንቀላፋም፡፡ ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋል፤ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን ይላል›› (1ቆሮ.15÷51-52) ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ‹‹በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስ የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ…›› (1ተሰ..4÷15-16) በማለት በዕለተ ምጽአት ምን ያህል ክብርና ጌትነት እንደሚሰጠው ይገልጽልናል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል በዓል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ12 መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዐበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ እነዚህም ኅዳር 12 ቀን ቀጥሎ ሰኔ 12 ቀን ከዚያም ነሐሴ 12 ቀንና ታኅሳስ 12 ቀን ናቸው፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ታላቁ በዓሉ ኅዳር 12 ቀን ነው፡፡ በዚህም ዕለት እግዚአብሔር በሰማይ ካሉ ሁሉ በላይ አድርጐ ሾመው፡፡ ስለትሕትናውና ስለ መታዘዙ ጌታውን ፈጣሪውን የከዳና የበጐ ሥራ ሁሉ ጠላት የሆነውን ሰይጣንን ድል ይነሣ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው፡፡ በዚህ ዕለት እንዲሁ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ ክብር ሆኖ በንጉሥ ጭፍራ አምሳል ለነዌ ልጅ ለኢያሱ የታየበት ዕለት ነው፡፡

በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው ይላል፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፡፡ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል (ሄኖክ. 6 ቁ.5 ምዕ.10 ቁ.12) ፡፡

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን ርኀሩኀ ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል የሠራውን ሥራ የክብሩን ገናንነት ጽፈን ለመጨረስ ስለማይቻለን በዚሁ እናበቃለን፡፡ ጸሎቱ እና በረከቱ፣ ተራዳኢነቱም ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡

ድርሳነ ሚካኤል ዘየካቲት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም።


በየካቲት ወር በአሥራ ሁለት ቀን የሚነበብ ኃያል ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ድርሳን ይህ ነው። ልመናው በረከቱ ከኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

ከዚህ ነገር በኋላ በዚህ አገር የሚኖር ሃይማኖቱ የፀና አንድ ድሃ ነበር። በመዓልትም በሌሊትም ይጸልይ ነበር። ቅዱስ ሚካኤልን ጌታዬ ሆይ እዘንልኝ የዕለት ምግብ የዓመት ልብስ ስጠኝ ይለው ነበር። ሰውዬው ግን ሰነፍ ነው። ከቤቱ ወደሥራ አይወጣም ልድከም አይልም የሚያውቀው ሥራ የለም። አንዲት ሰዓት ስንኳ ልሥራ አይልም። ንግድም አያውቅም።


ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በሕልም ተገልጦ ወደዚህ ደሃ ሰው መጣ። እንዲህም አለው።እርሻውም ቢሆን ንግድም ቢሆን ጥቂት ሥራ የማትወድ አንተ ሰነፍ ሰው በመዓልትም በሌሊትም ይቅር በለኝ እያልክ እንዴት ትለምነኛለህ።


እባርክልህ ዘንድ ወይንህ የት ነው ስንዴህ የት ነው የሠራኸው የትነው የደከምክበት የት ነው። አንተ ሰነፍ ሰው የምተሸጠው የምትገዛበት የት አለ ጌታዬ ሚካኤል እዘንልኝ እንደምን ትለኛለህ። የደከምክበት ሥራ የት አለ። የሁሉ አባት አዳምን እግዚአብሔር እንዳለው አልሰማህምን፡


በክፉ በዲያብሎስ ሽንገላ የአዘዘውን ሕግ በተላለፈ ጊዜ። ይህች የተገኘህባት ምድር ናት ወደሷም ትመለሳለህ። ሥራ በፊትህ ወዝ እንጀራህን ብላ። እሾህ አሜከላ ይብቀልብህ አላለውምን አንተ ግን አትሠራም ግን ባርክልኝ ትለኛለህ። ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ወጣ።


በነጋ ጊዜም ይህ ድሃ ተነስቶ ሊጸልይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደ። ሊጸልይም በቅዱስ ሚካኤል ስም ወደ ተሠራው መቅደስ ገባ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ከኔ ጋር ሁን አትለየኝ አለ። ከቤተ ክርስቲያንም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈራ ለደሆች ለችገረኞች ብዙ ምጽዋት የሚሰጥ አንድ ባለጸጋ ሰው አገኘ።


ይህ ድሃ ጌታዬ እዘንልኝ መቶ ወቄት ወርቅ ስጠኝ ሔጄ እነግድበት ራሴን እረዳበት ዘንድ ገንዘብህንም ከነወለዱ እከፍለሃለሁ አለው። ባለጸጋውም ድሃውን እኔ አላውቅህም ይህም ባይሆን ዛሬ ከዚህ ሀገር የሚዋስህ አንድ ሰው አምጣ። በኔና በአንተ መካከል ፀብ እንዳይሆን ገንዘቤን የሚመልስልኝ ዋስ ስጠኝ አለው።


ይህም ድሃ ባለጸጋውን እኔ ድጋ ነኝና የሚዋሰኝ አላገኝም። አሁንም ፈቃድህ ከሆነ ከራራህልኝም ተነስተህ እኔም አንተም ሁለታችንም የመላእክት አለቃ ወደ ሚሆነ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንሒድ እሱ አለቃዬ ነውና ይዋሰኛል አለው። ይህም ባለጸጋ አንተስ በቅዱስ ሚካኤል የምታምን ከሆነ እኔም አምንበታለሁና ተነሥ እንሒድ አለው።


ከዚህ በኋላ ሁለቱም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔደው የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ባለበት አንድነት ቆሙ። ይህም ደሃ የመላእክት አለቃ ጌታዬ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ስለዚህ ባለጻጋ አላመነኝምና አንተ ጌታዬ ተዋሰኝ አለው። ከዛሬ ጀምሮ በዓልህ እስከሚከበርበት ሰኔ አሥራ ሁለት ቀን ድረስ ለባለገንዘቡ ወርቁን እመልሳለሁ አለው።


ይህም ባለጸጋ ነገርክን ሰማሁ ተነስ እንሂድ ልስጥህ አለው። ይህ ነገር ለባለጸጋው ድንቅ ሆኖበታልና። ከዚህ በኋላ ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ሁለቱም አንድነት ወደባለጸጋው ቤት ሔዱ። ባለጸጋውም መቶ ወቄት ወርቅ ሰጠው። ድሃውም የተሰጠውን ወቄት ወርቅ ይዞ ደስ እያለው ወደቤቱ ተመለሰ ከዚህም በኋላ ወደሮም አገር ሔደ በዚያ ወርቅም ነገደና አተረፈ።

ከዚህ በኋላ ቀጠሮው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዓል የሚሆንበት ዕለት ሰኔ አሥራ ሁለት ቀን እንደደረሰና ወደ ሀገሩ ሊመለስ እንዳልቻለ በአወቀ ጊዜ ጽኑ ኀዘን አዘነ። ተቆረቀረ። በልቡናውም አስቦ እንዲህ አለ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ዋስ ያደረግሁበት ጊዜው ደረሰ ዛሬ መድረስ አልተቻለኝም ምን ላድርግ አለ።


ያን ጊዜም የቅዱስ ሚካኤልን ተራዳኢነት የፈጣሪውንም ከሃሊነት አሰበ።ከዚህ በኋላ እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ አንገቱን ወደ ላይ አቅንቶ ጸለየ። በፍጹም ልቡና በፀና ሃይማኖት ታምኖ ለባለ ዕዳው ከአምሳ ትርፍ ጋራ መቶውን ወቄት ወርቅ ይዞ በከረጢት ቋጥሮ በከረጢቱም ውስጥ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ስምና የባለጸጋውን ስም ከነሱም ጋር የእሱን ስም ጻፈ።


ከዚህ በኋላ ተነስቶ ወደ እንጥረኛ ሔዶ አንጥረኛውን የእርሳስ ሣጥን ሥራልኝ አለው። የእርሳስ ሣጥን ሠራለት። ከዚህ በኋላ ይህን ከረጢት ወስዶ ከውስጡ ጨምሮ ዘጋው።


ከዚህ በኋላ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ዋዜማ ቀን ወደ ወንዝ ሔደ ከባሕር ዳርም ቆሞ አቡነ ዘበሰማያት ደገመ እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰገነ።


በፍጹም ሃይማኖቱም ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ እነደተዋስከኝ ባለጠጋውና እኔ የተቃጠርንበት የበዓልህ ቀን ዛሬ እንደሆነ እኔም ከሩቅ አገር እንዳለሁ ዛሬም እስክንድርያ መድረስ እንዳይቻለኝ አንተ ታውቃለህ አሁንም የባለጠጋውን ገንዘብ ከነወለዱ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ ለባለ ዕዳዬ መልስልኝ ብሎ ጸለየ ጸሎቱንም በጨረሰ ጊዜ ሣጥኑን ከነ መክፈቻው ወደ ባሕር ወረወረው ያን ጊዜ ጊዜውን ታላቅ ዓሣ ወጥቶ ሣጥኑን ተቀብሎ ዋጠው።


ከዚህ በኋላ ያ ዓሣ በአንዲት ሌሊት የስድስት ወር ከስድስት ቀን ጎዳና ተጉዞ በነጋው ፀሐይ በወጣ ጊዜ ከእስክንድርያ ባሕር ወደብ ደረሰ። በዚች ቀን ያ ባለጸጋ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል በዓል ዓሣ ሊያሠግሩ ሔደው ከባሕር ላይ መረባቸውን ይጥሉ ዘንድ ብላቴኖቹን አዘዘ።


ያ ዓሣ ተያዘና ወደ ባለ ጸጋው ወሰዱት ባለጠጋውም ባየው ጊዜ ደስ አለው ታላቅ ነበርና። ባለጠጋውም ብላቴኖችን ይህን ዓሣ ለበዓሉ ቅዱስ ሚካኤል አመጣልኝ አላቸው። ብላቴኖችን ያን ዓሣ ጥቡት ብሎ አዘዛቸው ሆዱንም በቀደዱት ጊዜ በዓሣው ሆድ ውስጥ ይህን የዋጠውን ሣጥን አገኙት።


ያም ባለጸጋ ዕቃ ቤቱን በሀገራችን የተደረገውን በባሕርም ውስጥ የሆነውን ሁሉ ሰምተን እስክናውቅ ድረስ ይህን ሣጥን አስቀምጥ አለው። ከጥቂት ቀን በኋላ ያ ድሃ ወደ እስክንድርያ ከተማ ገባ። ባለዕዳውም አገኘውና ለምን እንዲህ አደረግህ አምኜ ገነዘቤን ብሰጥህ በጊዜው እንዴት አልሰጠኸኝም ለምንስ አልከፈልከኝም አለው።


ያም ድሃ እኔስ ለተዋሰኝ ሰጥቼው ነበር በውኑ በቀጠሮው አልሰጠህምን አለው። ዋስህን ወዴት አግኝተኸው ሰጠኸው አለው ድኀውም እኔ ሩቅ አገር ስለ አለሁ የተቃጠረንበት ቀን በደረሰ ጊዜ ወደ አንተ መድርስ ባይቻለኝ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን መቶውን ወቄት ከአተረፍኩልህ ከአምሳ ትርፍ ጋር በከረጢት ውስጥ አድርጌ በላዩም የቅዱስ ሚካኤልን ስም የኔንና የአንተንም ስም ጽፌ በሣጥን ውስጥ አደርጌ ቆለፍኩና ያንንም ሣጥን ወስጄ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ዋዜማ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ሆይ እንደተዋስከኝ አንተ ታውቃለህ እነሆ እንካ ለባለ ዕዳዬ ገንዘቡን መልሰህ ሰጥልኝ ብዬ ከባሕር ጣልኩት አለው።


ያ ድኀም ይህን ነገር በነገረው ጊዜ ባለጠጋው ከጥቂት ቀን በፊት የሆነውን ነገር አሰበና በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ቀን በዓሣው ሆድ ውስጥ የተኘገውን ሣጥን አምጣ ብሎ ዕቃ ቤቱን አዘዘው። አመጣለት በእጁም ይዞ ድኀውን ሣጥኔ ነው የምትለው ይህ ነውን አለው። ባለጠጋውም አዎን ጌታዬ አለው። ፈጥኖ ከፈተው። በከረጢቱ ላይም የቅዱስ ሚካኤልን ስምና የራሱንም ስም የባለጠጋውንም ስም እንደ ተጻፈ እንደ ታተመ አገኙ። መቶ ወቄትና ትርፉንም አምሳ ወቄት በውስጡ አገኙ።

ስለዚህም ነገር ባለጸጋው የቅዱስ ሚካኤልን የተአምራቱን ገናንነት የአምላኩንም ከሀሊነት አደነቀ እግዚአብሔርንም አመሰገነ አከበረ ከፍ ከፍ አደረገ። መቶውን ወቄት ትርፉንም ይዞ ባለፀጋው ድሃውን እንዲህ አለው ወንድሜ ሆይ ሃይማኖትህ ፍጹም ነው።


በእውነት አንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነህ ይህን ትርፍ ከአንተ አልቀበልም አለው። ያም ባለጸጋ ከገንዘቡ አምሳውን ወቄተ ወርቅ ወስዶ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጽዋዕ አሠራው። ለመታሰቢያው ይሆነው ዘንድ


ሁለቱም ከዚያን ቀን ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው ወዳጅ ሆነው በእግዚአብሔር ፍቅር ፀንተው ኖሩ። ይህም ሁሉ የሆነው በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ነው። እኛንም በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል የጸሎት ኃይል እግዚአብሔር ይማረን ይቅር ይበለን በጥምቀት የተወለድን ሁላችንንም ይጠብቀን ለዘለዓለሙ አሜን።


እሳታዊ ባሕርይ ያለው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው። ልመናው አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።


ቸር እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው እንደነበር ተነገረ። ለድኆች ለችግረኞች ቸርነትን ያደርግ ነበር። የአዳም ልጆች ሁሉ ባለጋራ በጎ ነገርን የሚጠላ ሰይጣንም ይህን ባየ ጊዜ ቀንቶ ጽኑ ደዌ አመጣበት። ሽባ ሆነ ጽኑ ደዌ ታመመ። ይህም ሰው ደዌው ስለጸናበት ሁል ጊዜ ይጮህ ነበር።


ከደዌው ጽናት የተነሣ ከተኛበት መነሣት ተሳነው። ስለዚህም ዘመዶቹን ጎረቤቶቹን ወደመላእክት አለቃ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን በሥውር ተሸክመው እንዲወስዱት ለመናቸው አንሱም ሰው ሳያውቅ በሌሊት ወሰዱት። እንደለመናቸውም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል በአለበት ወስደው አስቀመጡት።


ከዚህ በኋላ ያ ሰው በፍጹም ልቡና ወደ ቅዱስ ሚካኤል ይለምን ይማለል ይማልድ ጀመር። እንዲህ እያለ ጌታዬ የመላእከት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎትህ አስበኝ ከአሁንም ና እርዳኝ። ከዚህ ከአገኘኝ ጽኑ ደዌም ፈውሰኝ አድነኝ እኔ አገልጋይህ ልመናህን አምኜ መታሰቢያህን ሳደርግ ኖሬአለሁና።


ከልቅሶና ከጽኑ ዕንባ ጋረ ደረቱን እየመታ እንዲህ ሲል እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ በላዩ ላይ ታላቅ ብርሃን ወጣ።የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከብርሃኑ ውስጥ ሆኖ እንዲህ ብሎ ተናገረው። ከዚህ ደዌህ እግዚአብሔር አድኖሃልና ከዚህ ደዌህ ዳን ተነሥ እነሆ እግዚአብሔር አድኖሃል ድኅነትንም ሰጥቶሃል እንግዲህ ዳግመኛ አትበድል ኃጢኣት አትሥራ ከዚህ የበለጠ እንዳያገኝህ።


ይህንን ብሎት እጁን ዘርግቶ ሁለንተናውን ዳስሶ እግዚአብሔር ፈጽሞ አድኖሃልና ተነስተህ ሒድ አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ቀንቶ በእግሩ ተነስቶ ሔደ። የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ፈጣሪ እግዚአብሔርን እያመሰገነ።ከደዌው ስለ ዳነ ፈጽሞ ደስ አለው። በፍጹም ደስታ ቃል እያመሰገነ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ሰገደ።


ሕዝቡም ሁሉ ይህን ታላቅ ተአምራት ባዩ ጊዜ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ገናንነት ፈጽመው አደነቁ። የተአምራቱን የነገሩን ምስጋና አበዙ። የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ተአምር ያዩትም ለሰው ሁሉ ነገሩ። ያ የዳነው ሰውም ከቀድሞው ይልቅ በጎ ሥራን አበዛ። እስኪሞትም ድረስ በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያ ማድረጉን አላስታጎለም።


የቸርነትና የይቅርታ መልእክተኛ በሚሆን በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ገባ። እኛንም የክብር ባለቤት ጌታ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ከኃጢኣት ሞት ያድነን ከክፉ ቀን ከመከራ ዘመን ይሠውረን። መንግስተ ሰማያትን ያውርሰን። በዚህ ዓለም በሚመጣውም ዓለም የሕይወትን ተስፋ ያድለን አሜን።


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የካቲት አሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን ክብር ምስጋና ይግባውና እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን የረዓይት ወገን ወደሚሆን ወደ ሶምሶን ልኮታልና።

ሊገድሉት የፈለጉትን የፍልስጥኤምን ሰዎች ድል እስኪያደርጋቸው ድረስ ረድቶታልና። በእነሱ ላይ እግዚአብሔር ኃይል ሰጥቶት አጠፋቸው ከእነሱ በአንዲት ቀን በአህያ መንጋጋ ሺህ ሰው ገደለ። ውሃ ጠምቶት ሊሞት በደረሰ ጊዜም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ታይቶ አፀናው ከአህያ መንጋጋ አጥንትም ውሃ አወጣለት ጠጥቶም ከውሃ ጥም ዳነ።


የፍልስጥኤም ሰዎች ድል በሆኑ ጊዜ ከሚስቱ ጋር ተማክረው ዓይኑን አጥፍተው ወደ ጣኦታቸው ቤት ወሰዱት። የእግዚአብሔር መልእክተኛ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ታየው ተነጋገረው ኃይልንም ሰጠውና ሁሉንም አጠፋቸው ስለዚህ ነገር የቤተ ክርስቲያን መምህራን በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ። አዝዘውናል።


ልመናው ከእኛ ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።