ማሞ ውድነህ

ከውክፔዲያ

ማሞ ውድነሀህሀህሀህሀህህ የቴአትር ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ለ12 አመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ነበሩ [1]። በአቡነ ጳውሎስ በሚመራው የሃይማኖት ኮሚቴ ውስጥ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን ለማምጣት ጥረት ካደረጉ ሰዎችም አንዱ ነበሩ። የ54 መጻህፍት ደራሲና ተርጓሚ የነበሩት አቶ ማሞ በማስታወቂያ ሚኒሰቴር ስር በሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በጋዜጠኝነት የሰሩ ሲሆን የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ መስራችና ተባባሪ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ተጠሪ ሆነዉ በተመደቡበት የጋዜጠኝነትና የፖለቲካ ስራ በተጨማሪ ህብረት በተሰኘዉ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ዘገባዎችና ትንታኔዎች ያቀርቡ ነበር።

ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምናቸዉን ሲከታተሉ የነበሩት አቶ ማሞ ዓርብ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ፀሎተ ፍትሐቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሪነት ተፈፅሟል፡፡ አስክሬናቸውም በደራሲ ሐዲስ ዓለማየውና ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን መካነ መቃብር አጠገብ አርፏል፡፡ በቀብራቸዉ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የቀድሞዉ የአዲስ አበባ ከንቲባዎች ከንቲባ ዘውዴ ተክሉና ከንቲባ ብርሃነ ደሬሳ ተገኝተዋል፡፡[2]

ልጅነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ከአባታቸው አቶ ውድነህ ተፈሪና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ወልደየስ የተወለዱት ማሞ ውድነህ በፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ጊዜ ወላጆቻቸውን አጥተዋል። የሕይወት አጋጣሚ በሻጊያን በቦምብ ከደደቡት ፓይለቶች አንዱን እንዲያገኙ አብቅቶያችው ይቅር እንዳሉት በአንድ ጽሁፋቸው ዘግበዋል ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በ 15 አመታቸው የጀመሩት አቶ ማሞ በተለያዩ ችግሮች ምክኒያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መጨረስ ባይችሉም በአዲስ አበባ እና አስመራ ውስጥ የሚታተሙ ፖሊስ እና እርምጃውህብረት እና የዛሬይቱ ኢትዮጲያ የተሰኙ ጋዜጦች ውስጥ አገልግለዋል። [3]

የግል ህይወት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አቶ ማሞ ከባለቤታቸዉ ወይዘሮ አልማዝ ገብሩ ስድስት ልጆችና 10 የልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡

የደራሲ ማሞ ውድነህ ገጸ በረከቶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አቶ ማሞን ይበልጥ ታዋቂና ተወዳጅ ያደረጋቸው በሥነ ጽሑፉ መስክ ያበረከቱት መጠነ ብዙና ዘርፈ ሰፊ የድርሰት ሥራዎቻቸው ናቸው፡፡ 53 መጻሕፍት ያሳተሙ ሲሆን፣ 54ኛው ‹‹ጣጣኛው›› ልብወለድ በሕትመት ላይ ነው፡፡ ሥራዎቻቸው በስለላ፣ በታሪክ፣ በልብለወድና በተውኔት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡[4] ከነዚህ ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ።

  • 1.ሁለተኛው የዓለም ጦርነት
  • 2.የሴቷን ፈተና
  • 3.ከወንጀለኞቹ አንዱ
  • 4.ቬኒቶ ሙሶሊኒ
  • 5.የገባር ልጅ
  • 6.ሁለቱ ጦርነቶች
  • 7.አደገኛው ሰላይ
  • 8.ዲግሪ ያሳበደው
  • 9.ካርቱም ሔዶ ቀረ?
  • 10.የ፮ቱ ቀን ጦርነት
  • 11.የደቡብ ሱዳን ብጥብጥ
  • 12.ብዕር እንደዋዛ
  • 13.ሞንትጐመሪ
  • 14.የኤርትራ ታሪክ
  • 15.“የኛው ሰው በደማስቆ“
  • 16.የ፪ ዓለም ሰላይ
  • 17.ምጽአት-እሥራኤል
  • 18.ሰላዩ ሬሳ
  • 19.የ፲፯ቱ ቀን ጦርነት
  • 20.የካይሮ ጆሮ ጠቢ
  • 21.የበረሃው ተኰላ
  • 22.ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ
  • 23.ጊለን-የክፍለ ዘመኑ ሰላይ
  • 24.የኦዲሣ ማኅደር
  • 25.ከታተኞቹ
  • 26.ከሕይወት በኋላ ሕይወት
  • 27.ስለላና ሰላዮች
  • 28.ምርጥ ምርጥ ሰላዮች
  • 29.ዕቁብተኞቹ
  • 30.አሉላ አባነጋ
  • 31.የሰላዩ ካሜራ
  • 32.“ሰላይ ነኝ“
  • 33.በዘመናችን ከታወቁ ሰዎች
  • 34.ዕድርተኞቹ
  • 35.ሾተላዩ ሰላይ
  • 36.ማኅበርተኞቹ
  • 37.በረመዳን ውዜማ
  • 38.የበረሃው ማዕበል
  • 39.ኬ.ጂ.ቢ.
  • 40.ሲ.አይ.ኤና ጥልፍልፍ ሲሆኑ
  • 41.ዩፎስ-በሪራ ዲስኮች
  • 42.መጭው ጊዜ
  • 43.ዮሐንስ
  • 44.የአሮጊት አውታታ
  • 45.እኔና እኔ
  • 46.ኤርትራና ኤርትራውያን
  • 47.ሞት የመጨረሻ ነውን?
  • 48.የደረስኩበት_፩
  • 49.የደረስኩበት_፪

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "አንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ". thearadaonline.com (04 March 2012). Archived from the original on 11 March 2016. በ04 April 2012 የተወሰደ.
  2. ^ "የደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ቀብር ተፈጸመ". ethiopianreporter.com (03 March 2012). Archived from the original on 5 March 2012. በ04 March 2012 የተወሰደ.
  3. ^ "Journalist and Historian Mamo Wudneh dies at 81". newsdire.com (02 March 2012). በ04 March 2012 የተወሰደ.
  4. ^ "‹‹አምስት ዓይናው›› ማሞ ውድነህ". ethiopianreporter.com (07 MARCH 2012). በ07 March 2012 የተወሰደ.

የውጭ ማያዣ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]