ማቻከል

ከውክፔዲያ


ማቻከል
ማቻከል
ማቻከል is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ማቻከል

10°40′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°20′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ማቻከልአማራ ክልል የሚገኝ ወረዳ ነው።

የማቻከል ወረዳ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የማቻከል ወረዳ በአማራ ክልል ምስራቅ ጐጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ 18 ወረዳዎች መካከል አንዱ ሲሆን በሰሜን ስናን ወረዳ በደቡብ ደ/ኤልያስ፣ በምዕራብ ደንበጫ ወረዳና በምስራቅ የጐዛምን ወረዳ ያዋስኗቷል፡፡ የወረዳው ርዕሰ ከተማ የሆነችው አማኑኤል ከአዲስ አበባ በተዘረጋው የአስፖልት መንገድ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከሃገሪቱ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ 328 ኪ.ሜ ፣ በክልሉ ርዕሰ ከተማ ባህርዳር 234 ኪ.ሜ እንዲሁም የዞኑ ከተማ የሆነችው ደብረ ማርቆስ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ በወረዳው 24 ቀበሌዎች፣ 3 ንዑስ ከተማና በ1 የከተማ ቀበሌ የተከፋፈለ ሲሆን የወረዳው ዋና ከተማ አማኑኤልም በ1886 በደጃዝማች ጓሉ እንደተቆረቆረች ይነገራል፡፡ የማቻከል ወረዳ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 73558 ሄ/ር ሲሆን የአየር ፀባይ ሁኔታ 58.76 % ደጋ ፣39.1% ወይናደጋ 2.12% ውርጭና 0.02% ቆላ እንዲሁም ከባህር ወለል በላይ 1200-3200 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ አማካኝ የሙቀት መጠኑ ከ22oc -28oc የሚደርስ ሲሆን ከ1500-1800 ሚሊ ሜትር አመታዊ የዝናብ መጠን ይኖረዋል፡፡

በወረዳው ወ 6488 ሴት 66017 በድምሩ 130998 ህዝብ የሚኖር ሲሆን ከነዚህም መካከል ወንድ 59266 ሴት 60406 በድምሩ 119669 የሚሆነው ህዝብ በገጠር የሚኖር ነው፡፡ ሁሉም የወረዳው ህዝብ መቶ በመቶ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆን 98.98 የኦርቶዶክስ ክርስትና 1.02 የሚሆነው ደግሞ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ነው፡፡ የወረድዋ ህዝብ በአብዛኛው ኑሮው የተመሰረተው በግብርናው ክፍለ ኢኮኖው በተለይም በእርሻ ስራ ላይ ሲሆን ጥቂቶች ደግሞ በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ከወረዳው ጠቅላላ ስፋት ውስጥ 46372.19 ሄ/ር መሬት ለእርሻ ሰብል፣ 7648 ሄ/ር መሬት ለግጦሽ ፣ 4654 ሄ/ር መሬት በደን የተሸፈኑ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በልዩ ልዩ ቆጥቋጦዎች፣ አትክልትና ወንዞች የተሸፈነ ነው፡፡ የአፈር አይነቱም 12.7% መሬት ጥቁር አፈር፣ 5.7% ግራጫ፣ 70.2% ቀይ አፈርና 11.35% ቡናማ አፈርን ያካተተ ነው፡፡ ይህም በወረዳው ውስጥ ለሚመረቱ የአገዳ ፣የብዕርና የቅባት ሰብሎች ምቹ ስብጥር እንዳለው ያመላክታል፡፡

በወረዳው ውስጥ 51 ቅድመ መደበኛ ፣ 72 የጐልማሶች ትምህርት ቤት ፣ 51 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ 2 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፣1 የመሰናዶ ት/ቤት ፣ 1 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ በጤናው ዘርፍም 6 ጤና ጣቢያዎች እና በሁሉም ቀበሌዎች የጤና ኬላዎች ያሉ ሲሆን አንድም እናት በወሊድ ምክንያት አትሞትም የሚለውን መርህ ከግብ ለማድረስም 1 የቀይ መስቀልና 1 የጤና በድምሩ 2 አንቡላንሶች ለወረዳው ህዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

አጠቃላይ ሃገራዊና ወረዳዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን የተሳለጡ ለማድረግ እንደ ማንኛውም አካባቢ ህ/ሰቡ ግብር የመክፈል ልምዱ እየዳበረ የመጣ ሲሆን በገጠር 23715 ግብር ከፋይ አርሶ አደርና በከተማ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋይ 13 ፤ የደረጃ “ለ” 168 ፤ ደረጃ “ሐ” 1149 በድምሩ 1330 የሚሆኑ ነጋዴ ግብር ከፋዮች ሲኖሩ በተያዘው የበጀት አመትም ከ12 ሚሊዩን 56 ሸህ 40 ብር ግብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 7 ሚሊዩን 759 ሽህ 627 ብር ከ18 ሳንቲም ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም የእቅዱን 64.36 በመቶ ማለት ነው፡፡ከመጠረተ ልማት ዝርጋታ አንፃር ስንመለከት የወረዳውን ከተማ ጨምሮ ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የመብራት ተጠቃሚ ናቸው፡፡ በወረዳው ውስጥ በሁሉም ቀበሌዎች የኔትወርክ ዝርጋታ በመኖሩ የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠሟ መሆን ችሏል፡፡ ዋና ከተማውን ጨምሮ በድምሩ 8 ቀበሌዎች የ24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው ካሉ ቀበሌዎች ከ18 በላይ የሚሆኑት በጋ ከክረምት አገልግሎት በሚሰጡ መንገዶች ከወረዳ ማቻከል ጋር የተገናኙ ናቸው፡፡

በወረዳው ውስጥ የተለያዩ ታሪካዊና ባህላዊ ቦታዎች የሚገኙ ሲሆን1880 ዓ.ም በንጉስ ተክለሃይማኖት ዘመን ቆሎቤና ሰሎሜ በተባሉ ጣልያዊያን እንደተሰሩ የሚነገርላትና 6 ሜትር ከፍታ 4 ሜትር ስፋትና 4 ሜትር ርዝመት ያለው የአድያ ድልድይ በዘመኑ በነበሩ ሰዎች በአበያ በረሃ ድንጋይ በማምጣት የተሰሩ በመሆኑ ቀልብን ይስባል፡፡ የኳሽባ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ከተፈጥሯዊ መስህብነት ባለፈ በአትክልትና ፍራፍሬ ተሸፍኖ በልማት ስራውም ሊጐበኝ የሚገባ ሌላው የቱሪስት መስህብ ሲሆን የጨኔ አንድነት ብሮግን እቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም ሌላው ተፈጥሯዊና ማራኪ ገዳም የወረዳው እንቁና ማራኪ የቱሪስት መስህብ ሃብቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ የማቻከል ወረዳ ለነዋሪዎቹ ምቹ፣ ለጐብኝዎቹ እንግዳ ተቀባይና ማልማት ለሚፈልጉ የአየር ፀባዩ ተስማሚ የሆነ ተፈጥሯዊ ስነ ምህዳር በጋን ሰርቶ ለመለወጥ ተነሳስቶ ያለው ሰው አክባሪ ህዝብ ያለበት በመሆኑ ወደ ወረዳችን ደግመው ደጋግመው ይመጡና ያልመጡ ይጐብኙ ይዝናኑ፡፡

የማቻ/ወ/የመን/ኮሙ/ጉ/ጽ/ቤት

ህዝብ ቆጠራ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የማቻከል ወረዳ ህዝብ ቁጥር
ዓ.ም.** የሕዝብ ብዛት የተማሪዎች ብዛት


ማቻከል አቀማመጥ

ማቻከል
ማቻከል



ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]