ማግና ካርታ

ከውክፔዲያ
1217 በድጋሚ የወጣው የማግና ካርታ ቻርተር አሁን እንደሚታይ

ማግና ካርታ በ1207 ዓ.ም. የእንግሊዙ ንጉስ ጆን (ዮሐንስ) የተቀበለው የመብት ቻርተር ሰነድ ነው። ሰነዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የረቀቀው በካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን ዋና ዓላማውም በተጠላው ንጉስ እና በአማጺ መኳንንቱ መካከል ሰላም ለማውረድ ነበር። የቤተክርስቲያንን መብት እንዲጠበቅ፣ የመኳንንቱን ያለህግ መታሰር እንዲከልከል፣ ፍትህ ሳይጓተት በፍጥነት እንዲገኝ፣ ለንጉሱ የሚደርገው ክፍያ ገደብ እንዲኖረው የሚያዘው ይህ ቻርተር በ25 መኳንንት ምክር ቤት እንዲተገበር ያዛል።

ማግና ካርታ፣ የንጉሱ ሥልጣን ከህግ በታች እንደሆነ እና ነጻ ሰዎች ያላቸውን መብት በማጽደቁ፣ በእንግሊዝና በኋላም በአሜሪካ አገሮች ለተገኘው ግለሰባዊ ነጻነት መሰረት የጣለ ሰነድ ነው።