ሪም-ሲን

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

1 ሪም-ሲን ከ1734 እስከ 1675 ዓክልበ. (ኡልትራ አጭሩ አቆጣጠር) የላርሳ ንጉሥ ነበረ።

ሪም-ሲን በ1734 ዓክልበ. ወንድሙን ዋራድ-ሲንን በላርሳ ዙፋን ተከተለው። ስለዚህ አባቱ ኤላማዊው አለቃ ኩዱር-ማቡግ እንደ ነበር ይመስላል። በ1721 ጎረቤቶቹ ባቢሎንኡሩክራፒቁምኢሲን ላርሳን ለመቃወም በውል ተባበሩ። ሪም-ሲን ግን ሁላቸውን በአንድ ውግያ አሸነፋቸውና መንግሥቱን ያስፋፋ ጀመረ። በ1714 ኡሩክን ዘረፈ። በ1712 ግን የባቢሎን ንጉስ ሲን-ሙባሊት ድል አደረገው። በ1710 ዓክልበ. የኢሲንን ግዛት ወረረው፣ በ1705 ኢሲንን ከመጨረሻ ንጉሱ ከዳሚቅ-ኢሊሹ ያዘ። ይህም በሪም-ሲን መንግሥት በ30ኛው አመት ሆነ።

በ1699 የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ኢሲንንና ኡሩክን ከሪም-ሲን ያዘ። በመጨረሻ በ1675 ዓክልበ. ሃሙራቢ ላርሳን ከበበው ከ6 ወር በኋላ ላርሳ ለባቢሎን ወደቀ።[1]ይህም በሪም-ሲን 60ኛው አመት ሆነ።

[ለማስተካከል] መጣቀሻዎች

  1. ^ History of the Ancient World, Susan Wise Bauer, W.W. Norton & Company, Inc., 2007, ISBN 978-0-393-05974-8

[ለማስተካከል] የውጭ መያያዣ

የኔ መሣርያዎች

Variants
Actions
የማውጫ ቁልፎች
ጠቃሚ መሣሪያዎች
በሌሎች ቋንቋዎች