ሴንጋን

ከውክፔዲያ

ሴንጋንአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ሚስቱ አኑስት ተባለች።

5000 ፊር ቦልግ አይርላንድን በ1130 መርከቦች በወረሩበት ጊዜ (1538 ዓክልበ. ግድም) ሴንጋን ከዴላ ሌላ ልጆች ጋር ሻለቃ ነበረ። ሴንጋንና ወንድሙ ጋን ማክ ዴላ ደሴቱን በእንበር ዱብግላይዝ (አሁን ኮርክ ወደብ) ገቡ። የሴንጋን ክፍል ደቡብ መንስተር ሲሆን ጋን ስሜን መንስተር ተቀበለ። ወንድሞቹ ጋንና ጌናን ለ፬ አመት በጋርዮሽ ገዝተው በቸነፈር ካረፉ በኋላ፣ ሴንጋን ከፍተኛ ንጉሥ ሆኖ ተከተላቸው። ነገር ግን ከአምስት አመት በኋላ ሴንጋን በወንድሙ ሩድራይግ ልጅ ስታርን ልጅ በፍያካ ኬንፊናን እጅ በውግያ ተገድሎ ፍያካ ያንጊዜ ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘ።

ቀዳሚው
ጋንጌናን
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1530-1525 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ፍያካ ኬንፊናን