ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው

ከውክፔዲያ
ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው
የኢሚረመሻው ሐውልት በ1889 ዓ.ም. ሲገኝ
የኢሚረመሻው ሐውልት በ1889 ዓ.ም. ሲገኝ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1766-1754 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ኡሰርካሬ ኸንጀር
ተከታይ ሰኸተፕካሬ አንተፍ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1766 እስከ 1754 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የኡሰርካሬ ኸንጀር ተከታይ ነበረ።

ቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ «<..>ካሬ ኢሚረመሻው» ይገኛል። ከተገኙት ሁለት ታላቅ ሐውልቶች በቀር ስሙ በአንድ ዶቃ ላይ ተቀርጾ ተግኝቷል።

በዚህ ዘመን «ኦሩስ፣ አኸንኸሬስ፣ አኮሪስ፣ ኸንክሬስ፣ አክኸሬስ» በግብጽ እንደ ገዙ በአንዳንድ ምንጭ ይገኛል። እነዚህ ስሞች ሆር አዊብሬሰኸምሬኹታዊ ኻውባውሰጀፋካሬኡሰርካሬ ኸንጀር፣ እና ስመንኽካሬ ቢመስሉም፣ ከማኔጦን ጀምሮ ስሞቻቸው ከ፲፱ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ጋር እንደ ተዛቡ ይመስላል። «አክኸሬስ» የ፲፪ ዓመታት ዘመን እንደ ነበረው ይባላል። በመምኅር ኪም ራይሆልት ግመት ስመንኽካሬ ለ5-10 ዓመታት ብቻ ገዛ፤ ማስረጃ ግን የለም።

ቀዳሚው
ኡሰርካሬ ኸንጀር
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1766-1754 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰኸተፕካሬ አንተፍ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)