ቅዝቃዛው ጦርነት

ከውክፔዲያ
የአለም ሁኔታ በ1972 ዓም (1980 እ.ኤ.አ.)

«ቅዝቃዛው ጦርነት»ሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት በኋላ በተለይ ከአሜሪካሶቪዬት ሕብረት መካከል የነበረው መቀያየም ይገልጻል። ከ1937 እስከ 1982 ዓም ድረስ ያለው ዘመን ነው።

እነዚህ ሁለት ኃይለኛ አገራት መቸም «የሞቀ ጦርነት» ስላልነበራቸው ዘመኑ «ቅዝቃዛው ጦርነት» በመባል ታውቋል። እንዲያም ሁለቱ የኑክሌር መሣሪያ ሃያላት በመሆናቸው ጦርነቱ «የሞቀ» ከሆነ እንደ ሆነ «እርግጠኛ እርስ በርስ መጥፋት» ይሆን ነበር። የተረፈው አለም ወይም ከአንድ ወይም ከሌላው ወገን ወዳጅ ስለ ሆነ የአለም መጥፋት ማለት ነበር። ሁለቱ አገራት ግን በዛቻ፣ በሰላይ፣ በሴራ፣ በወኪል ጦርነት ይታገሉ ነበር። በተለይ አሜሪካ በቬትናም ጦርነት፣ በኋላም የሶቭየት ኅብረት በአፍጋኒስታን ጦርነት ተዋጉ። የቅዝቃዛው ጦርነት ዘመን በሶቭየት ኅብረት ውድቀት በ1982 ዓም ያህል ጨረሰ።