ቆላድባ

ከውክፔዲያ
ቆላድባ
ቆላድባ
ከፍታ 1881 ሜትር
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ ~25,000
ቆላድባ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ቆላድባ

13°03′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°25′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


ቆላድባ ከተማ የምትገኘው በአማራ ክልልሰሜን ጎንደር ዞንደምቢያ ወረዳ ውስጥ ነው ። ከጎንደር ከተማ በስተ ደቡብ 35 ኪ.ሜ ፣ ከጣና ሃይቅ በስተ ሰሜን 30 ኪ.ሜ መካከል ትገኛለች። ቆላድባ የተመሰረተችው በ1930ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ነው። ቆላድባ ከተማ በአሁኑ ስኣት ማለትም 2005 ዓ.ም. በ2 ሰፋፊ ቄበሌወች የተከፈለች ሲሆን የሕዝብ ቁጥሩዋም ወደ 25,000 አካባቢ ነው። ከተማዋ የደምቢያ ወረዳ ዋና ከተማ ስትሆን ፣ በውስጡዋም አንድ ቴክንክና ሙያ ፣አንድ መሰናዶ ፣ ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ፣ ሁለት መለስተኛ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሊሎች የትምህርት ተኩማት ይገግኛሉ። የህዝቡም መተዳደሪያ ግብርና ፣ንግድ ፣ ...... ናቸው።

በ1945 ዓ.ም. ቆላድባ ውስጥ በአረብ ነጋዴ የሚካሄድ የኑግ ዘይት መጭመቂያ ነበር። በዚሁ ዘመን አካባቢ 5ሺህ ሰዎች ያለቁበት የወባ እና ሌሎች በሽታ ወረርሽኝ ስለደረሰ የቀደመው የቆላድባ ገበያ በመንግሥት ትእዛዝ ወደ ከፍተኛ ቦታ እንዲዛዎር ተደርጓል[1]። ከ፫ አመት በኋላ በ1948 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ የመጀመሪያ ከሆኑት ፬ የጤና ማእከላት አንዱ በቆላ ድባ ከተማ ተቋቁሟል። ለዚህ ተግባር ሲባል የአካባቢው ኅብረተሰብ $ 8,000 ብር አዋጥቷል፣ ማእከሉም በተከፈተ ወቅት ፶ሺህ ሰዎችን እንዲያስተናግድ ኾኖ ነበር። [2]

የሕዝብ ስብጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የአዲስ ዘመን ሕዝብ ቁጥር [3]
ዓ.ም.** የሕዝብ ብዛት የተማሪዎች ብዛት
1958
4,002
614
2005
25,000


ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ [F J Simoons, Northwest Ethiopia .., Madison/USA 1960 p 59, 120, 197
  2. ^ [Ethiopia Observer 1957 no 4 p 121]
  3. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/k/ORTKOB05.pdf