ቦይንግ 787 ድሪምላይነር

ከውክፔዲያ
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ቦይንግ 787 ድሪምላይነር
All Nippon Airways Boeing 787-8

ቦይንግ 787 ድሪምላይነርቦይንግ የተሠራ የረዥም ርቀት፣ ጥንድ ሞተር አውሮፕላን ነው። የአውሮፕላኑ አብዛኛው ክፍሎች ከካርቦን ኮምፖሲት ማቴሪያል በመሠራታቸው፣ አውሮፕላኑ ከቀደምት አውሮፕላኖች የቀለለ ነው።[1] የነዳጅ ፍጆታው ከሌሎች አውሮፕላኖች በ20 ከመቶ የተሻለ ሲሆን ፍጥነቱ ከድምፅ ፍጥነት በ11 ከመቶ ያንሳል።[1] ጃፓን ከዓለም የመጀመሪያው የድሪምላይነር አብራሪ ናት። ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ብቸኛዋ አብራሪ ናት።[1] የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጠቅላላ አሥር ድሪምላይነሮችን በ1.5 ቢሊዮን ዶላር ገዝቷል።[1] ከተገዙት አሥር አየር-ዠበቦች የመጀመሪያውና በሰሌዳ ቁጥር ET-AOQ የተመዘገበው አየር-ዠበብ ነሐሴ ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ከዋሽንግተን ዲሲ ተነስቶ አዲስ አበባቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቅባበል ተደርጎለታል።[2]

ማመዛገቢያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ቅፅ 17 ቁጥር 49/1284፣ ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የወጣ፣ ገጾች 4፣55
  2. ^ http://www.flightglobal.com/news/articles/ethiopians-first-787-arrives-at-addis-ababa-375615/