ቮሮኛ

ከውክፔዲያ

ቮሮኛ (võro kiil´), የቮሮ ሕዝብ ቋንቋ ነው። በፊኖ-ኡግሪክ ቋንቋ ቤተሰብ ወስት ያለ በደቡብ ኤስቶኒያም የሚገኝ ቋንቋ ነው። የፊንላንድኛ፣ የኤስቶንኛ ቅርብ ዘመድ ነው። በ70,000 ሰዎች ይናገራል።

የቋንቋው ስፋት በጣም ትንሽ በመሆኑ፣ በኤስቶኒያ ውስጥ በ26 ትምህርት ቤቶች ከሳምንቱ በ1 ቀን ብቻ ያስተምሩታል። አንድ ጋዜጣ በቮሮኛ አለ፤ በየወሩ 2 ጊዜ የወጣል።

የሥነ-ጽሑፉ መጀመርያ በ1679 ዓ.ም. የታተመው አዲስ ኪዳን ትርጉም ነበር። የሚጻፍበት በላቲን ፊደል ሲሆን በቮሮኛ ተራ የሆነ 'q' የሚያመለክተው በጉሮሮ ውስጥ የሚሰማ እንደ 'አሊፍ የሆነ ድምጽ ይመስላል።

አንዳንዴ የራሱ ቋንቋ ሳይሆን እንደ ኤስቶንኛ ቀበሌኛ ይቆጠራል። ነገር ግን ከኤስቶንኛ ያለው ልዩነት ብዙ ነው።

ለምሳሌ፦

አማርኛ: ቮሮኛ: ኤስቶንኛ:
(ይጽፋል) kirotas (ኪሮታስ) kirjutab (ኪርዩታብ)
(አይጽፍም) kirota aiq (ኪሮታ አይእ) ei kirjuta (ኤይ ኪርዩታ)
(አልጻፈም) kirota es (ኪሮታ ኤስ) ei kirjutanud {ኤይ ኪርዩታኑድ)
(ይሰጣል) and (አንድ) annab (አናብ)
(አንተ አትሰጥም) saq anna eiq (ሳእ አና ኤእ) sa ei anna (ሳ ኤይ አና)
(እኔ አልመጣም) maq tulo oiq (ማእ ቱሎ ኦይእ) ma ei tule (ማ ኤይ ቱለ)
Wikipedia
Wikipedia