ታይ ካንግ

ከውክፔዲያ

ታይ ካንግ (ቻይንኛ፦ 太康) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ፫ኛ ንጉሥ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ አባቱ ካረፈ በኋላ (1985 ዓክልበ. ግድም) ልጁ ታይ ካንግ ተከተለው። ግቢው በዠንሡ ነበር። በዘመኑ ከልዎ ወንዝ ማዶ ለረጅም ወራት እያደነ መኮንኑ ሆውዪ መጥቶ በዠንሡ ተቀምጦ አቃወመው። «የ፭ቱ ልጆች መዝሙር» የሚባለው ግጥም ስለዚሁ ሁኔታ ነው። ታይ ካንግ አራት ዓመት ብቻ ከነገሠ በኋላ ሞተ። ወንድሙ ዦንግ ካንግ ተከተለው።

ቀዳሚው
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ
1985-1981 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ዦንግ ካንግ