ትሪቶኒስ ሀይቅ

ከውክፔዲያ

ትሪቶኒስ ሀይቅ በጥንታዊ ግሪክ አፈ ታሪክ ውስጥ በሊብያ የተገኘ ታላቅ ሐይቅ ነበረ። ብዙ የግሪክ ሃይማኖት አማልክት እንደ ትሪቶንሃሞንፓላስአቴናዲዮኒስዮስክሮኖስ ከዚህ አካባቢ ጋር ግንኙነት ነበራቸው።

ሄሮዶቱስዲዮዶሮስ ሲኩሉስና ሌሎች እንዳሉት፣ ይህ ሀይቅ ከቀርታግና ደቡብ በዛሬው ቱኒዚያ ይገኝ ነበር። ከዚህ ጋር «ትሪቶን» የሚባል ወንዝ ይፈስበት ነበር። በሄሮዶቱስ ዘንድ ሁለት ደሴቶች እነርሱም ፍላ እና ሜኔ አሉበት። ዲዮዶሮስ እንዳለው ኒሳ ደሴት በትሪቶን ወንዝ ውስጥ ነበረ፤ ሄሮዶቱስ ግን ኒሳ በአይቲዮፒያ በተገኘ ሀይቅ ላይ መኖሩን መሰከረ።

ምድር መንቀጥቀጥ የተነሣ ሐይቁ በግማሽ ወራት ደርቆ አሁን በቱኒዚያ አገር በበጋ የሚሞላ በክረምትም የሚደረቀው ሐይቅ ሻት አል-ጀሪድ እንደ ሆነ ይታሥባል።