አራፕኻ

ከውክፔዲያ
አራፕኻ

አራፕኻ በዛሬው ኪርኩክኢራቅ በጥንታዊ ዘመን የተገኘ ከተማ ነበር።

ከተማው ከ2000 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ሲታወቅ የጉቲዩም ዋና ከተማ ነበረ። ከዚህ በኋላ አራፕኻ የሑራውያን መንግሥት ሆነ። በ1742 ዓክልበ. የኤሽኑና ንጉሥ 2 ኢፒቅ-አዳድ ከተማውን ያዘው፣ እንዲሁም በ1693 ዓክልበ. የአሦር ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ ያዘው። በማሪ ንጉሥ ዝምሪ-ሊም ዘመን (1687-1675) አራፕኻ እንደገና ነጻ መንግሥት ነበር፤ ከትንሽ በኋላ ግን ለባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ተገዥ ሆነ። በሃሙራቢ ልጅ ሳምሱ-ኢሉና ዘመን ደግሞ ነጻ ግዛት ሆነ። ከተማው ትልቅ ሆኖ የጐረቤቱን ከተማ ኑዚን (የቀድሞው ጋሱር) በግዛቱ ውስጥ ያጠቅልል ነበር። ይህም የሚታኒ መንግሥት በ15ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ግድም አራፕኻን እስከ ያዘው ድረስ ቆየ፤ ሚታኒም ከወደቀ በኋላ አራፕኻ ከአሦርና ከባቢሎን መካከል ለብዙ ዘመናት ይፈራረቅ ነበር።