አስርቱ ቃላት

ከውክፔዲያ

አስርቱ ቃላት ወይም አስርቱ ትዕዛዛትመጽሐፍ ቅዱስ ዘንድ እግዚአብሔርሙሴደብረ ሲና የገለጣቸው 10 ትዕዛዛት ወይም ሕግጋት ናቸው። የሚገኘው በኦሪት ዘጸአት 20፡2-17 ሲሆን፣ ዳግመኛ በኦሪት ዘዳግም 5፡6-21 በጥቃቅን ተለውጦ ሊታዩ ይችላሉ። እስከምናውቀው ድረስ፣ መጀመርያ የተጻፉበት ቋንቋ ዕብራይስጥ ነበረ።

፩ (ዘጸአት 20፡2-3፣ ዘዳግም 5፡6-7)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ (በፊደል)፦

  • «አኖኪ ይሆዋህ ኤሎሄይካ እሼር ሆጸእቲካ መኤሬጽ ሚጽረዪም ሚበይት ዕባዲም።»
  • «ሎእ-ዪህዬህ ልካ ኤሎሂም እሐሪም ዐል-ፓናየ።»

አማርኛ

ግዕዝ

  • አነ ፡ ውእቱ ፡ እግዚእ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘአውፃእኩክሙ ፡ እምድረ ፡ ግብጽ ፡ እምቤተ ፡ ምቅናይክሙ ።
  • ኢታምልክ ፡ አማልክተ ፡ ዘእንበሌየ ።

፪ (ዘጸአት 20፡4-6፤ ዘዳግም 5፡8-10)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ-ተዕሤህ ልካ ፌሴል፣ ውካል-ቲሙናህ እሼር በሻመዪም ሚመዐል፣ ወእሼር ባአሬጽ ሚታሐት፣ ወእሼር በመዪም ሚተሐት ላአሬጽ።»
  • «ሎእ-ቲሽተሕዌህ ላሄም፣ ውሎእ ታዓብደም፣ ኪ አኖኪ ይሆዋህ ኤሎሄይካ ኤል ቀናእ፣ ፎቀድ ዕዎን አቦት ዐል-ባኒም ዐል-ሺለሺም ውዐል-ሪበዒም ልሥንአይ፤
  • ውዖሤህ ሔሜድ ለእላፊም ልኦህበይ ኡልሾምረይ ሚጽዎታይ።»

አማርኛ

  • በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
  • አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
  • ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።

ግዕዝ

  • ወኢትግበር ፡ ለከ ፡ አምላከ ፡ ከመዘ ፡ በውስተ ፡ ሰማይ ፡ በላዕሉ ፡ ወከመዘ ፡ በውስተ ፡ ምድር ፡ በታሕቱ ፡ ወበውስተ ፡ ማያት ፡ ዘበታሕቴሃ ፡ ለምድር ።
  • ኢትስግድ ፡ ሎሙ ፡ ወኢታምልኮሙ ፡ እስመ ፡ አነ ፡ እግዚእ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዚአከ ፤ እግዚአብሔር ፡ ቀናኢ ፡ አነ ፡ ዘእፈዲ ፡ ኀጢአተ ፡ አብ ፡ ለውሉድ ፡ እስከ ፡ ሣልስት ፡ ወራብዕት ፡ ትውልድ ፡ ለእለ ፡ ይጸልዑኒ ።
  • ወእገብር ፡ ምሕረተ ፡ ለለ፲፻ለእለ ፡ ያፈቅሩኒ ፡ ወትእዛዝየ ፡ እለ ፡ የዐቅቡ ፡ ወለእለ ፡ የዐቅቡ ፡ ሕግየ ።

፫ (ዘጸአት 20፡7፤ ዘዳግም 5፡11)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ ቲሣእ ኤት-ሸም-ይሆዋህ ኤሎሄይካ ለሻውእ፤ ኪ ሎእ ይነቄህ ይሆዋህ ኤት እሼር-ዪሣእ ኤት ሽሞ ለሻውእ።»

አማርኛ

  • የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።

ግዕዝ

  • ኢትምሐል ፡ ስመ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈጣሪከ ፡ በሐሰት ፡ እስመ ፡ ኢያነጽሕ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዘይነሥእ ፡ ስሞ ፡ በሐሰት ።

፬ (ዘጸአት 20፡8-11፤ ዘዳግም 5፡12-15)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ዛኮር ኤት-ዮም ሀሸባት ልቀድሾ።»
  • «ሸሼት ያሚም ተዕቦድ፣ ውዓሢታ ካል-ምለእክቴካ፤
  • ውዮም ሀሽቢዒ ሸባት ለይሆዋህ ኤሎሄይካ፤ ሎእ-ተዕሤህ ካል-ምላእካህ፣ አታህ፣ ኡቢንካ፣ ኡቢቴካ፤ ዐብድካ፣ ወእማትካ፣ ኡብሄምቴካ፣ ውገርካ እሼር ቢሽዓሬይካ።»
  • «ኪ ሸሼት-ያሚም ዓሣህ ይሆዋህ ኤት-ሀሻመዪም ውኤት-ሀአሬጽ፣ ኤት-ሀያም፣ ውኤት-ካል-እሼር-ባም፤ ወያነሕ በዮም ሀሽቢዒ፤ ዐል-ከን በረክ ይሆዋህ ኤት-ዮም ሀሸባት ወይቀድሸሁ።»

አማርኛ*፦

  • ሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።
  • ስድስት ቀን ሥራ፣ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤
  • ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
  • እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንም፥ ያለባቸውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።


*(በኦሪት ዘዳግም 5፡12-15፣ ቃሉ እንዲህ ሲል ከኦሪት ዘጸአት 20፡8-11 ትንሽ ይለያል፦ «የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ ጠብቅ። ስድስት ቀን ሥራ፣ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ እንደምታርፍ ሎሌህና ገረድህ ያርፉ ዘንድ፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም ሎሌህም ገረድህም በሬህም አህያህም ከብትህም ሁሉ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ። አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ፣ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ።»)

ግዕዝ

  • ተዘከር ፡ ዕለተ ፡ ሰንበት ፡ አጽድቆታ ።
  • ሰዱሰ ፡ ዕለተ ፡ ግበር ፡ ተግበረ ፡ ቦቱ ፡ ኵሎ ፡ ትካዘከ ።
  • ወበሳብዕት ፡ ዕለት ፡ ሰንበት ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ለእግዚእከ ፡ ኢትግበሩ ፡ ባቲ ፡ ወኢምንተ ፡ ግብረ ፡ ኢአንተ ፡ ወኢወልድከ ፡ ወኢወለትከ ፡ ወኢአድግከ ፡ ወኢኵሉ ፡ እንስሳከ ፡ ወኢፈላሲ ፡ ዘይነብር ፡ ኀቤከ ።
  • እስመ ፡ በሰዱስ ፡ ዕለት ፡ ገብረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሰማየ ፡ ወምድረ ፡ ወባሕረ ፡ ወኵሎ ፡ ዘውስቴቱ ፡ ወአዕረፈ ፡ አመ ፡ ሳብዕት ፡ ዕለት ፤ በበይነዝ ፡ ባረካ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለሳብዕት ፡ ዕለት ፡ ወአጽደቃ ።

፭ (ዘጸአት 20፡12፤ ዘዳግም 5፡16)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ከበድ ኤት-አቢካ ውኤት-ኢሜካ፤ ልመዐን የእሪኩን ያሜይካ ዐል ሃእዳማህ እሼር-ይሆዋህ ኤሎሄይካ ኖተን ልካ።»

አማርኛ

  • አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም*።


*(በኦሪት ዘዳግም 5፡16፣ «መልካምም እንዲሆንልህ» የሚለውን ይጨመራል።)

ግዕዝ

  • አክብር ፡ አባከ ፡ ወእመከ ፡ ከመ ፡ ይኩንከ ፡ ጽድቀ ፤ ብዙኀ ፡ ዕለተ ፡ ትረክብ ፡ በውስተ ፡ ምድር ፡ ዘጻድቅት ፡ ውእቱ ፡ እግዚእ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሀብከ ።

፮ (ዘጸአት 20፡13፤ ዘዳግም 5፡17)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ ቲርጸሐ።»

አማርኛ

  • አትግደል።

ግዕዝ

  • ኢትቅትል ።

፯ (ዘጸአት 20፡14፤ ዘዳግም 5፡18)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ ቲንአፍ።»

አማርኛ

  • አታመንዝር።

ግዕዝ

  • ኢትዘሙ ።

፰ (ዘጸአት 20፡15፤ ዘዳግም 5፡19)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ ቲግኖብ።»

አማርኛ

  • አትስረቅ።

ግዕዝ

  • ኢትስርቅ ።

፱ (ዘጸአት 20፡16፤ ዘዳግም 5፡20)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ-ቴዕኔህ ብረዕካ ዐድ ሻቄር።»

አማርኛ

  • በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።

ግዕዝ

  • ስምዐ ፡ በሐሰት ፡ ኢትስማዕ ፡ ለቢጽከ ፡ ስምዐ ፡ በሐሰት ።

፲ (ዘጸአት 20፡17፤ ዘዳግም 5፡21)[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዕብራይስጥ

  • «ሎእ ተሕሞድ በይት ረዔካ፤ ሎእ ተሕሞድ ኤሼት ረዔካ፣ ውአብዶ፣ ወእማቶ፣ ውሾሮ፣ ወሕሞሮ፣ ውኮል እሼር ልረዔካ።»

አማርኛ

  • የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።


*(በኦሪት ዘዳግም 5፡21፣ ቃሉ እንዲህ ሲል ከኦሪት ዘጸአት 20፡17 ትንሽ ይለያል፦ «የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ፤ የባልንጀራህንም ቤት እርሻውንም ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም፥ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።)

ግዕዝ

  • ኢትፍቶ ፡ ብእሲተ ፡ ካልእከ ፤ ኢትፍቶ ፡ ቤቶ ፡ ለካልእከ ፡ ወኢገራህቶ ፡ ወኢገብሮ ፡ ወኢአመቶ ፡ ወኢላህሞ ፡ ወኢብዕራዊሁ ፡ ወኢኵሎ ፡ በውስተ ፡ እንስሳሁ ፡ ዘአጥረየ ፡ አጥርዮ ፡ ቢጽከ ።