አየለ ተሰማ

ከውክፔዲያ


ፊት ፡ አውራሪ ፡ አየለ ፡ ተሰማ 1 ፊታ አውራሪ አየለ ተሰማ


‹‹ ዳዊት ፡ ዘጎንደር ፡ ዘምትዉልደ ፡ ጌድዮን ፡ ዘገበዘ ፡ አክሱም፡፡ ›› 2 ዳዊት ፡ ዘጎንደር ፡ ዘምትዉልደ ፡ ጌድዮን ፡ ዘገበዘ ፡ አክሱም፡፡

‹‹ ጀግና ፡ ሚታወሰው ፡ ወይም ፡ ከሞተ ፡ ወይም ፡ ከተለየ! ›› ያሉት አበው እውን ሁኖ ያሄዉ አሁን አንድ ስመ ጥር ጀግና ልናነሳ ተገደድን ‹‹ ፊት ፡ አውራሪ ፡ አየለ ፡ ተሰማ! ›› የጀግና ባህሪው ብዙ ቢሆንም ‹‹ ጀግናን ፡ ከደረቱ ፡ አበባን ፡ ከአናቱ ፡ ይለዩ! ›› እንደ ተባለ አየለም የጀግንነት ባህሪው የተለየ ገና በንጭጩ በደረቱ ነው፡፡ ‹‹ የማይችሉት ፡ ድንጋይ ፡ ሲያወጡት ፡ ደረት ፡ ሲያወርዱት ፡ ጉልበት ፡ ይመታል! ›› እንደ ተባለ አየለም በልጅነቱ ለሸክም አይመችም ነበረ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት ጉልበት ይጎነትላል፡፡ አገሬውም ‹‹ እግሩ ፡ ለጠጠር ፡ ደረቱ ፡ ለጦር ፡ የተመቸ ፡ ነው! ›› ይለዋል፡፡ አሱም እራሱ መጀገን አምሮት ፋሺስት ጣሊያን ኑሮዉን ሊኖር ሀገር ሲገባ ‹‹ አይ! ፡ ጣሊያን ፡ አንተ ፡ ያየኸኝ ፡ ከጉልበት ፡ እኔ ፡ ያየሁህ ፡ ከደረት! ›› ሰላለ ፡ ጀግነቱ ፡ የተለየ ፡ ከደረቱ ፡ ነው ፡ የተባለዉም ፡ ለዚያ ፡ ነው፡፡

እና አየለ ለሀገሩ ዳር ድንበር  ፤ ለሀገሩ ነፃነት ፤ ‹‹ ነፍጥ! ››  አንግቶ ጫካ ሲገባ ያገሩ ነዋሪ ፤ ያገሩ ጉበል ‹‹ ሽማግሌ ፡ በምክሩ  : አርበኛ : በሰናድሩ ፡ ይለያል! ›› ብሎ ለሱ ሊገዛ ፣ ለሱ ሊያድር ገብቶለታል፡፡ እንደሱ ተከታዮች አባባል ‹‹ የሱ ነፍጥ! ››  አሉ ‹‹ ለእርሳሱ ፡ ማስፈንጠሪያ  ፡ መዶቃዱቅ ( ቧንቧ ) ፡ አለው ፡ ውስጥ ፡ ለውስጥ ፡ ጥይቱ ፡ ሲሄድ ፡ ያለው ፡ ባሩድ ፡ እሳትን ፡ የሚተፋና ፡ ርሳሱም ፡ መትቶ ፡ የሚገድል ፡ ነው! ››  ይላሉ፡፡
 ነፍጥ 

ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ‹‹ ባልንጀራዬ! ፤ ባልደረባዬ! ፤ የኔ ቢጤ! ›› ሚለዉ ቢኖር ‹‹ አባ ጓንዴ! ነዉ ፈረሱ! ›› አንድ ቀን አሉ አየለ እና ፈረሱ ፋሺስት ጣሊያን ሲያሳዳቸዉ ቢያድር በመንገድ ላይ ሳሉ እራባቸዉ በዚህን ጊዜ አባ አየለ ከፈረሱ ጋር ወደ መንደር ወጠዉ ካንድ ባዶ ቤት የሚበላ ሲያዩ በስርቆት ማለት ነዉ ህሊናቸዉን ወቀሳቸዉ እና ለፈረሳቸዉ ‹‹ የማናውቀውን ፡ ሌብነት፣ ልንሰርቅ ፡ ገብተን ፡ ከሰው : ቤት፣ ይቅርብን ፡ ጓዴ ፡ እንውጣ፣ የሚጠብቀን : መጣ! ›› ብለዉ ፈረሳቸዉን በቃለ ሰብአዊ አወሩት ፡፡ ይህን ነገር የሰማ ያአገሩ ኗሪም ‹‹ ለፈረስ ፡ ለበቅሎ ፡ ይተርፍ ፡ የነበረ፣ ዛሬስ ፡ ለሰው ፡ ያኽል ፡ ይቸግር ፡ ጀመረ! ›› ብሎ አነባ፡፡ እሳቸዉ እራሳቸዉም ይባላል ለሰዉ ሲመክሩ ‹‹ ሌሊት ፡ ከጭቃ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ ቢጥልህ፣ ወንድሜ ፡ አትናደድ ፡ ማንም ፡ አላየህ፣ ይልቁን ፡ ተጠንቀቅ ፡ ቀን ፡ እንዳይጥልህ! ›› ነዉ ሚሉ አሉ፡፡ እና አንድ ቀን ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ ሶስት ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት ‹‹ ምን? ፡ ቀረኝ ፡ በሎ ፡ ነዉ ፡ ይሄን ፡ ሚያረገዉ! ›› ብለዉ አጠገብ ባሉ ባንዳወች ቢያፈጡ ‹‹ ተሰማ ፡ ሳይቀጣው ፡ በልጅነት ፡ ቀርቶ፣ ገና ፡ ራስ ፡ ይመታል ፡ እንኳን ፡ ባት ፡ አግኝቶ! ›› ብለዋል፡፡

በዚህን ጊዜ የፋሽስት ጣሊያን ጦር እሱን ለመያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታሰሩበት እስር ቤት አጎሯቸዉ፡፡ በእሰር ቤቱም በተነሳዉ የታይፎይድ ወረርሽኝ ብዙ አርበኞች ሲያልቁ ወንድማቸዉ ልጅ ታደሰም የዚህ ገፈት ቀማሽ ሆኑ፡፡ እህታቸዉም ወ/ሮ አቻም የለሽ ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረት እንዲሁም ፋሺስት ጣሊያ ‹‹  ሎሌ ፡ ለሰህተት ፡ ጌታ ፡ ለምህረት! ›› እንደ ተፈጠረ ይታወቅላቸዉ ዘንድ ጥቂት አርበኞችን በምህረት ፈቱ፡፡ አባታቸዉ ግን ቀኝ አዝማች ተሰማ ከእስር እንደ ወጡ በሳምንቱ ሞቱ፡፡

ፊት አዉራሪ አየለም ተሰማም ከአባታቸዉ ሞት በዉሃላ በከፍተኛ ቁጭት እና የአርበኝነት ስሜት ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን ‹‹ በሜጀር ፡ ባንቲ : ቸኮ : ሴንታታ! ›› የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር ‹‹ አማኒት ›› ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ ሰኔ ሃያ ዘጠኝ ቀን 1938 ዓ.ም አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። በዚህን ጊዜ ሜጀር ፡ ባንቲ : ቸኮ : ሴንታታ!

‹‹ የዕድሌ ፡ ክፋቱ ፡ ፈተና ፡ አብዝቶብኝ፣

 አየለ ፡ አየለና ፡ ኀይሌን ፡ ወሰደብኝ! ›› ብሎ አነባ፡፡ 
ይህን ያየና የሰማ የሀገሩ ኗሪ እና ጉብል 

‹‹ አባት ፡ አስገዳይ ፡

 ወንደም : አስገዳይ : ብለዉ : ሲያሙት
 ነጭ : ሰዉ : ገዳይ ፡ ወርዶ : አማኒት
 ገዳይ ፡ አማኒት
 እንደ  ፡ አራስ : ነብር : ተጉዞ ፡ ሌሊት
 ገዳይ ፡ ኩመር ፡ በር
 በለዉ : እያለ : ከቀስቅስ : ጋር
 የአባቱን ፡ ጠላት : የተሰማን
 የታዴን : ጠላት : የወንድሙን
 በቁሙ ፡ ጠጣዉ : በሳንጃ : አልቢን
 አርዶ : በካር : ጠጣዉ : ደሙን፡፡ ›› እያለ ሲሸልል እና ሲፎክር 

አንዲት የጎንደር ጉበል እርጉዝ ሁኗ ኑሯ ‹‹ ሰጋ አማረኝ! ›› አለች አገሬዉ

‹‹ ሥጋ ፡ አማረኝ : አለች :የቀለቤሰ ፡ እናት፣ መተማ ፡ አትሄድም ፡ ወይ ፡ ከታረደበት! ›› ብለዉ መለሱላት ፡፡

ይህን አኩሪ ደል የሰሙትም ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በግራዝማች ራዳ አማካኝት ‹‹ ያባይ ፡ ምልክቱ ፡ አንደበቱ ፡ የገዳይ : ምልክቱ : ሽልማቱ! ››  ብለዉ የአድንቆት ደብዳቤና 300 ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ላኩ። 





ፊታውራሪ አየለ ተሰማ

ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ

ፋሽስት ጣሊያን መንግስት ሃገራችን በግፍ በወረረበት ወቅት ሃገራችን ብዙ ስመጥር ጅግኖችን አፍርታለች። በዚህ ወረራ ወቅት በጎንደርጓንግ ወንዝ እስከ መተማ ድረስ በጀግንነት ሃገሩን ከወረራ ነፃ ካደረጉት መካከል ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ አንዱ ነበሩ። በአንድ ወቅት ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ሰባስጌ በተባለ የፋሽስት የጦር ካምፕ ቦታ ላይ ከትንሽ ተከታዩቻቸዉ ጋር ጥቃት ፈፅመዉ 3 ወታደር ገድለዉና ብዛት ያለቸዉን በማቁሰላቸዉ፤ የፋሽስት ጣሊያን ባለስልጣናት በፊት አዉራሪ አየለ ላይ የተጠናከረ ዘመቻ በማድረግ አሳድደዉ ለመግደል ያላደረጉት ጥረት አልነበረም። ነገር ግን እሱን መያዝ ቢቸግራቸዉ ቤተሰቦቹን አባቱን ቀኝ አዝማች ተሰማን ፤ ወንድሞቹን ልጅ ታደሰ እና ረዳን በመያዝ በጎንደር አርበኞች በሚታጎሩበት እስር ቤት አሰሯቸዉ። ነገር ግን በወቅቱ በእስር ቤቱ በተነሳዉ የታይፎይድ በሽታ ብዙ አርበኞች ሲሞቱ ልጅ ታደሰ የገፈቱ ተቃማሽ ነበር። ይሁን እንጅ የቀሪዎች ህይወት ለማትረፍ በተደረገዉ ጥረት ወ/ሮ አቻሽማን ተሰማ ሽማግሌዉ አባቷን ቀኝ አዝማች ተሰማ እና ወንድሟን ረዳን ለማስፈታት ባደረገችዉ ጥረትና በዚህ ወቅትም ብዙ የጎንደር አርበኞች በጣሊያን ባለስልጣናት ምህረት ተደርጎላቸዉ ከስር ተፈተዋል። ይሁን እንጅ ቀኝ አዝማች ተሰማ በወቅቱ በታመሙት የታይፎይድ በሽታ በተፈቱ በሳምንታት ዉስጥ ለሞት አበቃቸዉ። ታዲያ ለዚህ ሁሉ የቤተሰብ ችግር አምጭ ተደርጎ የታየዉ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ ነበር። ለፊት አዉራሪ ግን የእነሱ ሞት ለነፃነታቸዉ እንደ መሰዋዕትነት አድረጎ ነዉ የቆጠረዉ። በዚህ ልዩ የቁጭት አርበኝነትና ሃገር ወዳድነት ስሜት ጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ አባ ጓዴ ከወንድሙ ከግራዝማች ረዳና ከልጅ አበራ ጋር በመሆን በሜጀር ባንቲ ቸኮ ሴንታታ የሚመራዉን የጣሊያንን ጦር በመተማ አካባቢ ነጋዴ ባህር አማኒት ተብሎ በሚጠራዉ ቦታ በሰኔ 29 ቀን 1938 ዓ.ም በመሄድ አስደናቂ ጀብድ በመስራት የፋሽስትን ጦር በመደምሰስ አኩሪ ታሪክ ሰሩ። ይህ ጀብዳቸዉም እስከ ስደተኛዉ ንጉስ ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ድረስ በመሰማቱ ጃንሆይም የአድንቆት ደብዳቤና በግራዝማች ራዳ አማካኝት 300ጠበንጃ፤ 3000 ጥይትና 1000 ብር ልከዋል። በአባባ ገሪማ ታፈረ "ጎንደሬ በጋሻዉ" እና በሕይዎት ህዳሩ የቀ.ኃ.ስ መልክተኛ "ያች ቀን ተረሳች" መፃህፎች ስለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ እና ወንድማቸዉ ግራዝማች ረዳ ተገልፆል። በዚህ የአማኒት ጦርነት ድል መሰረት ለጀግናዉ አርበኛ ፊት አዉራሪ አየለ ተሰማ በህዝብ እንዲህ በፉከራና በቀረርቶ ተገጠላቸዉ፡፡

አባት አስገዳይ ወንደም አስገዳይ ብለዉ ሲያሙት
ነጭ ሰዉ ገዳይ ወርዶ አማኒት
ገዳይ አማኒት
እንደ አራስ ነብር ተጉዞ ሌሊት
ገዳይ ኩመር በር
በለዉ እያለ ከቀስቅስ ጋር፡፡
የአባቱን ጠላት የተሰማን
የታዴን ጠላት የወንድሙን
በቁሙ ጠጣዉ በሳንጃ አልቢን
አርዶ በካር ጠጣዉ ደሙን፡፡

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለምንጊዜም ሃገር ወዳድ የነፃነት ጀግኖች አባቶቻችና እናቶቻችን!! አሹ ዋሴ ጊዜ