አጋሮ

ከውክፔዲያ

አጋሮኢትዮጵያኦሮሚያ ክልል ከተማ ሲሆን በጅማ ዞንና በጎማ ወረዳ ይገኛል። አጋሮ በቡና ምርቷ የምትታወቅ ሞቅ ደመቅ የውቦች እና የደጋጎች ሕዝቦች ድንቅ ከተማ ናት::

በ1960ዎቹ መጀመሪያ ከጂማ ቀጥሎ ሌሎች በምዕራብ ኢትዮጵያ ያሉ አብዛኞቹ ከተሞች የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገድ ሳይኖራቸው አጋሮ ግን ከንጉሡ ዘመን ጀምሮ በአስፓልት ያጌጡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ነበሯት:: አጋሮ በአየሯ መልካነት እና ለኪነ-ጥበብ ባላት ፍቅር በዝነኛ አርቲስቶች ተመራጭ ነበረች :: ከ1960-70ዎቹ ከድምፃውያን ጥላሁን ገሠሠ, መሐሙድ አህመድ, ብዙነሽ በቀለ, መልካሙ ተበጀ, ነዋይ ደበበ, ሐማልማል አባተ, ሃጫሉ ሁንዴሳ, ጌትሽ ማሞ እንዲሁም ሌሎችም... የሚመርጡዋት ከተማ ነበረች ::

አጋሮ ከ1960-70ዎቹ መገባደጃ ከ3-4ሰው የሚይዙ ታክሲ(ላዳ) በመጠቀም ከትላልቅ ከተሞች ጎን ታሪክ ያላት ከተማ ናት አጋሮ.... በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ41,616 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 21,549 ወንዶችና 20,067 ሴቶች ይገኙበታል።[1] እስከ 1878 ዓ.ም. ድረስ የጎማ መንግሥት ዋና ከተማ ነበረ።

በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ28,668 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ7°5′ ሰሜን ኬክሮስ እና 36°39′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።[2]

📝ኢዩኤል ጌትነት (Toni) agaro city.

ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን Archived ኦገስት 13, 2007 at the Wayback Machine, population.pdf
  2. ^ Butler, Rhett A., 2005 population estimates for cities in Ethiopia


📚አዩኤል ጌትነት ሙላት (Toni), Agaro city