ኤምፒ3

ከውክፔዲያ

ኤምፒ3 ድምፅን ወይም ዘፈንን በኮምፒውተር ላይ ማስቀመጫ ፎርማት ነው። ቴክኖሎጂው ከተፈጠረ ፳ ዓመት ገደማ ይሆነዋል። በብዛት በዘፈን ማጫዎቻዎች እንዲሁም ለድረ ገጽ ራዲዮዎች፣ ለፖድካስት ማጫዎቻዎች ይጠቅማል።

ኤምፒ3 ለምን ይጠቅማል?[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ዋና ጥቅሙና ተወዳጅ ያደረገው ነገር ብዙ የድምፅ መረጃን፣ዘፈን በጣም ጥቂት በሆነ ቦታ ለማስቀመጥ ያስችላል። ለምሳሌ 20(፳) ገደማ የሚሆን ሲዲ ከኤምፒ3 የዘፈን ፎርማት ውጭ የተዘጋጀ ሲዲ ኤምፒ3 የዘፈን ፎርማት በመጠቀም በአንድ ሲዲ ልናዘጋጀው እንችላለን።ይህ ማለት ወደ 200(፪፻) ዘፈኖችን በአንድ ሲዲ ማስቀመጥና ማጫዎት ማለት ነው።

የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች አይነት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች ሙዚቃውን የሚያከማችበት የተለያየ ዘዴ አለው። አይነቶቹም የሚከተሉት ናቸው።

  1. ሶሊድ ስቴት(ፍላሽ ዲስክ) አይነት የኤምፒ3 ማጫዎቻ።
  2. ሐርድ ዲስክ አይነት የኤምፒ3 ማጫዎቻ።
  3. ባለ ሲዲ አይነት የኤምፒ3 ማጫዎቻ።

የኤምፒ3 ማጫዎቻዎች።[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • አይፖድ(ipod)
  • አፓሰር(Apacer)
  • ሶኒ(Sony)
  • የማይክሮሶፍት ዙን (Zune from Microsoft)
  • የክሬቲቭ ዜን( Creative Zen)