ኤውላጥ

ከውክፔዲያ

ኤውላጥ ማለት በዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ (ብሉይ ኪዳን) የሚጠቀስ አገርና ግለሰቦች ነው።

ኦሪት ዘፍጥረት 2፡10-12 የዔድን ገነት ሲገልጽ፦

«ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር። የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤ የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤ ከዚያም ሉልና የከበረ ድንጋይ ይገኛል።»

ከዚህ በኋላ በምዕራፍ 10 የኖኅ ልጆች ሲዘረዘሩ 2 «ኤውላጥ» የተባሉ ሰዎች ይገኛሉ። አንዱ የኩሽ ልጅ ሲሆን ሌላው ደግሞ የዮቅጣን ልጅ ይባላል። አገሩ ኤውላጥ በአረቢያ በረሃ ምዕራብ ስሙን ያገኘው ከዮቅጣን ልጅ ነበር።

እንዲህ ያለ ኤውላጥ አገር በአረቢያ በረሃ ውስጥ በዘፍጥረት 25፡18 እንደገና ይጠቀሳል፤ የእስማኤላውያን ነገዶች መኖሪያ «ከኤውላጥግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከ ሱር ድረስ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ ላይ ነበረ»። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 15፡7 ደግሞ እንዲህ ይጠቅሰዋል፦ «ሳኦልአማሌቃውያንከኤውላጥ ጀምሮ በግብፅ ፊት እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው»።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ባለው ሥነ ጽሑፍ፣ በሐሳዊ ፊሎ ታሪክ መሠረት፣ ከኢያሱ ወልደ ነዌ ዘመን በኋላ ቄኔዝ የእስራኤል ዳኛ ሲሆን አሞራውያን ጣኦታታቸውን ለመሥራት ዕንቁ ከኤውላጥ አገር አገኙ ይላል።

ኪታብ አል-ማጋል እና የመዛግብት ዋሻ የሚባሉት መጽሓፍት እንደሚሉ፣ አሕዛብ ከባቢሎን ግንብ ሲበተኑ የኤውላጥ ዮቅጣን ልጆች ከተማና መንግሥት ከወንድሞቹ ሣባኦፊር አጠገብ ሠሩ።