ከንባታ

ከውክፔዲያ

ከምባታ በአብዛኛው በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሌሎችም አካባቢዎች በስፋት ከሚገኙ ብሄረሰቦች አንዱ ሲሆን የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ስነጥበብ፣ ወግና፣ የኑሮ ዘይቤ ያለው ህዝብ ነው። የከምባታ ዋና ከተማ ዱራሜ ተብሎ የሚጠራ ከተማ ነው፡፡

ቋንቋ የደጋማው ምሥራቃዊ ኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ የሆነው ‹‹ከምባታኛ›› የከምባታ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲሆን በተጨማሪ ብዙዎቹ ሀዲይኛን ፤ ኦሮምኛን ሀላበኛን ወላይትኛንና አማርኛ በሁለተኛ ቋንቋነት ይናገራሉ፡፡ ከምባታኛ ከንግግር ቋንቋነት አልፎ የጽሑፍ ቋንቋ መሆን የጀመረው በ1920ዎቹ ዓለም አቀፍ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር መጽሐፍ ቅዱስን በከምባታኛ ቋንቋ አስተርጉሞ ካሳተመበት ወቅት ጀምሮ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ1967 እስከ 1968 ዓ.ም በነበረው የእድገት በኀብረትና የዕውቀት ዘመቻ ወቅት የሳባን ፊደላት በመጠቀም ለመሠረተ ትምህርት ማስተማሪያነት መዋል እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ግን በሀገሪቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማስተማር ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ከመስከረም 1986 ዓ.ም ጀምሮ በከምባታኛ የአንደኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል ከንድ እስከ አራት ሁሉም የትምህርት ዓይነቶች በከምባታኛ በላቲን ፊደላት እየተሰጠ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የከምባታ ጠምባሮ ዞን የሥራ ቋንቋ ከምባታኛ ነው፡፡

ከንባታ የኢትዮጵያ ብሔር ነው።