ዊሊያም ማኪንሌይ
ከውክፔዲያ
ዊሊያም ማኪንሌይ (እንግሊዝኛ: William McKinley) የአሜሪካ ሃያ አምስተኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ፕረዝዳንቱ ሥልጣን ላይ የወጡት እ.አ.አ. በ1897 ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ሁነው የተሾሙት ጋሬት ሆባርት እና ቴዎዶር ሮዝቬልት ናቸው። ፕሬዝዳንቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የነበሩ ሲሆን ከሥልጣን የወረዱት እ.አ.አ. በ1901 ነበር።