ውክፔዲያ:የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ
የአዲስ መጣጥፍ ሰም ሲያወጡ ይህን መጣጥፍ እንዲያዩ ይመከራል።
ማውጫ |
[ለማስተካከል] ነጠላ ቃል ይጠቀሙ
ለምሳሌ ስለ መኪና አዲስ ገጽ ሊጨምሩ ከሆነ አርዕስቱን መኪናዎች ሳይሆን መኪና ብለው ይሰይሙት። ለመደቦች ግን የተለየ መመሪያ አለ።
[ለማስተካከል] የአማርኛ ቃል ይጠቀሙ
ስለ orange የሚጽፉ ከሆነ አርዕስቱን ብርቱካን ይበሉት፤ በመጣጥፉ መጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ላይ ግን በኩር (አሪጅናሉ) ቋንቋ ካለ በቅንፍ ይጻፉት። ለምሳሌ፦
- ሴንት ጆንስ (እንግሊዘኛ፡ St. Johns) በአሪዞና የሚገኝ ከተማ ነው።
- ኮኝስኮቮላ (ፖሎኝኛ፡ Końskowola) በደቡባዊ ምስራቅ ፖላንድ የሚገኝ ሰፈር ነው።
[ለማስተካከል] ከምጻረ ቃሎች ዝርዝር ቃሎችን ይምረጡ
ከምጻረ ቃሎች ዝርዝር ቃሎችን ይምረጡ ግን ከምጻረ ቃሉ ወደዝርዝሩ መያያዣ ይስሩ። ለምሳሌ፦ ኢዜአ ከማለት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ይበሉት።
[ለማስተካከል] የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት
ለስፖርት-ነክ ዓመታት የእግር ኳስ ንዑስ ክፍልን ከስር ይዩ።
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ቢጠቀሙ ይመረጣል። ነገር ግን ለአሁኑ ጊዜ ዓመታት የሚጻፉት እንደ አቅራቢው ምርጫ ነው። የሚሻ ግን መቆጠሪያው በምን አይነት እንደሆነ በግልጽ ለመግለጽ ነው።
- በኢትዮጵያ መቁጠሪያና በግሬጎርያን መካከል የ7 ወይም 8 አመት ልዩነት አለ። ስለዚህ ፦
1998 አመተ ምህረት = 2005 ወይም 2006 እ.ኤ.ኣ.።
ከዚያ ደግሞ የአውሮፓ አቆጣጠር አንዳንዴ "ዓመተ ምህረት' ሊባል ይችላል። ስለዚህ፦
- "(ዓ.ም.)" ለኢትዮጵያ ዓመታት
- "(እ.ኤ.አ.)" ለግሪጎርያን ብቻ ቢጠቀም ጥሩ ነው።
ወራት ደግሞ የኢትዮጵያ ወይም የግሪጎርያን ሊሆኑ ይችላሉ።
- እንደ ዓመታት አይነት ተመሳሳይ ይሁኑ። ምሳሌ፦
- December 26, 2005 እ.ኤ.ኣ.
- -ወይም-
- ታኅሣሥ 18 ቀን 1998 ዓ.ም.
- በቀጥታ ወሮችን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የሚያስለውጥ መለጠፊያ ዘዴ አለ።
በተጨማሪ ለመረዳት ውክፔዲያ:የቀን መለወጫ ይዩ።
[ለማስተካከል] የቦታ ስም አጻጻፍ
ለአርዕስት፦
- የሀገር ስም ከሆነ በቀላሉ ወይም በሙሉ ስሙን መጻፍ ይቻላል። ከሌላኛው ግን መያያዣ መሥራት ጥሩ ነው።
ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ የሚል መጣጥፍ ካለ፣ ከየኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወደ ኢትዮጵያ መያያዣ መሥራት ያሻል።
- የክፍለ ሀገር ስም ከሆነ - ስሙ ከዚያም ነጠላ ሠረዝ (፣) እና አንድ ባዶ ሕዋእ ቦታ (space) እና የሀገሩ ስም
ምሳሌዎች፦
- አፓቼ ካውንቲ፣ አሪዞና
- ፓሪስ፣ ፈረንሣይ
[ለማስተካከል] የትምህርት ቤቶች ስም አጻጻፍ
የትምህርት ቤቶችን ሙሉ ስም ይጠቀሙ። ያስታውሱ፥ በመጀመሪያው መስመር ላይ በኦሪጂናሉ ቋንቋ ይጻፉ።
ምሳሌዎች፦
- Arizona State University ወደ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ
- Massachusettes Institue of Technology የማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት
- Northern Arizona University ሰሜን አሪዞና ዩኒቨርስቲ
- University of Maryland የሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ
[ለማስተካከል] የአውሮፕላን ማረፈያ ሰም አጻጻፍ
የአውሮፕላን ማረፊያ ስም ሲጽፉ በተቻለ መጠን ሙሉ ስሙን ይጻፉ። ምሳሌዎች፦
- ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ
- ዋሽንግተን ሮናልድ ሬገን ብሔራዊ አውሮፕላን ማረፊያ
[ለማስተካከል] የፊልም አርዕስት አጻጻፍ
የፊልም አርዕስት ሲጽፉ፦
- አንድ ከሆነ ስሙን ብቻ ይበቃል
- ተከታታይ ወይም ከአንድ በላይ ፊልም በአንድ አርዕስት ካለ የተሰራበትን ዓ.ም. ይጨምሩ (የዘመን አቆጣጠር ሥርዐትን ይዩ)
- በስሙ መጽሐፍ ወይም ሌላ ነገር ካለ (ፊልም) ይጨምሩ - ምሳሌ፦ ታይታኒክ (ፊልም)
[ለማስተካከል] የሰው ስም አጻጻፍ
አርዕስቱ የሰው ስም ከሆነ "ዶ/ር"፥ "አቶ"፥ "ክቡር"፥ "ወ/ሮ" ፥ ወዘተ አይጨምሩ። በመጣጥፉ የመጀመሪያ መስመር ግን ቢጨምሩ ያሻል። ለንጉሦች ደግሞ "ዓፄ"፥ "ንጉሥ"፥ "ንጉሠ ነገሥት"፥ ወዘተ መንታ መንገድ ለመፍታት ካልሆነ በስተቀር አይጨምሩ።
[ለማስተካከል] እግር ኳስ
[ለማስተካከል] ዓመታት
ለእግር ኳስ ውድድሮች፣ የሚካሄዱበት ዓመት በይፋ አርዕስታቸው ስለሚጠቃቀል ከግሬጎርያን ወደ የኢትዮጵያ አቆጣጠር ወይም ከኢትዮጵያ ወደ ግሬጎርያን አይለውጡ። ለምሳሌ፦
[ለማስተካከል] የቡድኖችና ክለቦች አሰያየም
F.C. «የእግር ኳስ ክለብ» በማለት ይተርጉሙ። ለምሳሌ፦
- F.C. Barcelona -> ባርሴሎና የእግር ኳስ ክለብ