ዓረብኛ

ከውክፔዲያ
(ከዐረብኛ የተዛወረ)


አረንጓዴ፡- ዓረብኛ ፡ ብቻ ፡ መደበኛ ፡ ነው።
ሰማያዊ፡- ዓረብኛ ፡ ከመደበኛ ፡ ቋንቋዎች ፡ አንዱ ፡ ነው።

ዓረብኛ (العربية)የሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ ቤተሠብ ፡ አባል ፡ ሆኖ ፡ የዕብራይስጥ ፡ የአረማያ ፡ እንዲሁም ፡ የአማርኛ ፡ ቅርብ ፡ ዘመድ ፡ ነው። ፪ ፻ ፶ (250) ፡ ሚሊዮን ፡ የሚያሕሉ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ እናት ፡ ቋንቋ ፡ ይናገሩታል። ከዚህም ፡ በላይ ፡ በጣም ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ እንደ ፡ ፪ ፡ ቋንቋ ፡ ተምረውታል። የሚጻፈው ፡ በዓረብኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። በዓረብ ፡ አለም ፡ ውስጥ ፡ አያሌ ፡ ቀበሌኞች ፡ ይገኛሉ።

ቋንቋው ፡ በእስልምና ፡ ታላቅ ፡ ሚና ፡ አጫውቷል። እስላሞች ፡ አላህ ፡ ለሙሐማድቁርዓንን ፡ ሲገልጽ ፡ በዓረብኛ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ስለሚያምኑ ፡ እንደ ፡ ቅዱስ ፡ ቋንቋ ፡ ይቆጥሩታል። አብዛኛው ፡ ዓረብኛ ፡ ተናጋሪዎች ፡ ሙስሊሞች ፡ ናቸው።

ዛሬ ፡ በምዕራብ ፡ ዓለም ፡ ደግሞ ፡ ብዙ ፡ ሰዎች ፡ አረብኛ ፡ እያጠኑ ፡ ነው። በታሪክ ፡ ከፍተኛ ፡ ሚና ፡ በማጫወቱ ፡ መጠን ፤ ብዙ ፡ የዓረብኛ ፡ ቃላት ፡ ወደ ፡ ሌሎች ፡ ቋንቋዎች ፡ ገብተዋል።

Wikipedia
Wikipedia