ዧንሡ

ከውክፔዲያ
የጥንታዊ ቻይና ንጉሥ ዧንሡ

ዧንሡ (ቻይንኛ፦ 顓頊) ወይም ጋውያንግ (高陽) በቻይና አፈ ታሪክ የጥንታዊ ቻይና ንጉሥ ነበር። የኋንግ ዲ ልጅ-ልጅ ሲሆን ዧንሡ የኋሥያ ነገድ ወደ ምሥራቅ ወደ ሻንዶንግ መራቸው። በዚያ ከዶንግዪ ሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ።

ሽጂ በሲማ ጭየን[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

100 ዓክልበ. ሲማ ጭየን በጻፈው የታላቁ ታሪክ ጸሐፊ መዝገቦች ወይም ሽጂ እንደሚለን፣ የጋውያንግ አባት የኋንግ ዲ ልጅ ቻንግዪ ነበር። እናቱ ቻንግጱ ነበረች። በሲማ ጭየን መዝገቦች ዘንድ የኋንግ ዲ በኲር ሻውሃው መቸም ንጉሥ አልሆነም። ይልቁንም ከኋንግ ዲ ቀጥሎ ይህ ጋውያንግ 'ዟንሡ' ተብሎ በቀጥታ እንደ ተከተለው ይላል። ዧንሡን ጥበበኛ፣ ቅንና ጨዋ ንጉሥ ይለዋል። በግብርናና በሥነ ፈለክ ዘዴዎች እርምጃ አስተማረ፣ ሕገጋቱንም ከመንፈሳውዊ ተጽእኖ አወጣ። ከዘመኑም በኋላ፣ ዘመዱ የሻውሃው ልጅ ጅያውጂ ልጅ ጋውሢን ንጉሥ ተብሎ ተከለተው።

በቀርከሃ ዜና መዋዕሎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ደግሞ ጋውያንግ ወይም ዧንሡ ከአጎቱ ሻውሃው ተከተለው። በርዎሽዌ ወንዝ ለቻንግዪና ለኒውጩ ተወልዶ እድሜው 10 አመት ሲሆን የሻውሃው ረዳት ሆነ፣ 20 አመት ሲሆን ንጉሥ ሆነ። የንጉሥ ዧንሡ ድርጊቶች፦

  • 1ኛው አመት (2283 ዓክልበ.) - ዋና ከተማው በፑ፣ ሻንዶንግ አደረገ።
  • 12ኛው ወይም 13ኛው አመት (2271 ዓክልበ.) - የዘመን አቆጣጠር አሻሸለ፣
  • 21ኛው አመት (2263 ዓክልበ.) - «መልስ ለደመናት» የሚባል ሙዚቃ ጻፈ።
  • 30ኛው አመት (2254 ዓክልበ.) - ልጁን ፒቋንን ወለደ፣ ፒቋንም በጢንሙ ደቡብ ኖረ።
  • 78ኛው አመት (2206 ዓክልበ.) - ዧንሡ አረፈ፣ ሹቄ (ከሸንኖንግ ወገን) ሁከት አነሣ፣ ነገር ግን የሢን ልዑል ጋውሢን (ኩ) አጠፋው።

ዋቢ መጽሐፍት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የታላቁ ታሪክ ጸሐፊ መዝገቦች በሲማ ጭየን (እንግሊዝኛ)


ቀዳሚው
ሻውሃው
ኋሥያ (ቻይና) ንጉሥ
2283-2206 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ዲ ኩ