የሾጣጣ ክፍሎች

ከውክፔዲያ
የሾጣጣ ክፍሎች አይነቶች:
1. ባላ
2. ክብ እና ሞላላ
3. ቦላላ

በሂሳብ ትምህርት የሾጣጣ ክፍሎች የምንላቸው መስመሮች ቀጥተኛ ክብ ሾጣጣን በጠፍጣፋ ስንከትፍ የምናገኛቸውን ቅርጾች ነው። እኒህ መስመሮች በሌላም መንገድ ሲተረጎሙ የሾጣጣ ክፍሎች ማለት ከአንድ ነጥብ (ፎከስና ከአንድ መስመር (ዳይሬክትሪክስ) ያላቸው ርቀት በቋሚ ውድር ላይ የተመሰረቱ ማናቸውንም መስመሮች ያጠቃልላል።

በነገራችን ላይ የሾጣጣ ክፍሎች ከዛሬ 2200 አመታት በፊት በግሪካዊው አፖሎኒየስ ዘፐርጋ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተጠንተዋል።

ዲሪክትሪክስና ከፎከሱ ባለ የርቀት ውድር ምክናይት እንዴት መስመሮቹ እንደሚቀየሩ እንመልከት