የዝባድ በሬ

ከውክፔዲያ
?የዝባድ በሬ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ሙሉ ጣት ሸሆኔ
አስተኔ: የቶራ አስተኔ Bovidae
ወገን: የዝባድ በሬ Ovibos
ዝርያ: O. moschatus
የዝባድ በሬ በተፈጥሮ (ቀይ) እና ሰዎች አስገብተው (ሰማያዊ) የሚገኝባቸው ቦታዎች
የዝባድ በሬ በተፈጥሮ (ቀይ) እና
ሰዎች አስገብተው (ሰማያዊ) የሚገኝባቸው ቦታዎች

የዝባድ በሬ (ሮማይስጥOvibos moschatus) በአርክቲክ ዙሪያ የሚገኝ የቶራ አስተኔ አባል ነው።

የእንስሳው ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዝባድ በሬ መንጋ መከላከያ ሠልፍ

የዝባድ በሬ ወንድ ብርቱ ጠረን የሚሰጡ እጢዎች አሉት። ይህ ሴቶችን ለማዳራት ነው። ወንዶችም ሴቶችም ሁለት ረጅም፣ ጥምዝ ቀንዶች በራሳቸው ላይ አሏቸው። ወንዶችም ከደመነፍስ የተነሣ እርስ በርስ ለሴቶችም ሆነ ለሣር ቡጢ ያደርጋሉ።

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የዝባድ በሬ የሚበላው ሣርበለሴትሳርንስትየአርክቲክ አኻያ ቊጥቋጥ፣ ወዘተ. ነው።

ዝባድ በሬን የሚበላው ነጣቂ በተለይ የአርክቲክ ተኲላ ነው። አልፎ አልፎ የዋልታ ድብ ወይም ቡናማ ድብ ድካሙን ይነጥቃል። በሚበዙበት ጊዜ፣ የሰው ልጅ ደግሞ ለሥጋው ያድናቸዋል።

በመንጋው ምናልባት 8-24 በሬዎች ይሆናሉ። ጥቃት ቢደርስባቸው፣ ለመከላከያ ፊታቸውን ወደ ውጭ አድርገው በክብ ነገር ቁመው የቀለበት ቅርጽ ይሠራሉ።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር እና ብዛቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የተፈጥሮ መኖሪያቸው በስሜን ግሪንላንድና በስሜን ካናዳ ሲሆን፣ ከዚህ በላይ የሰው ልጆች ወደ አላስካስካንዲናቪያሳይቤሪያ አስገብተዋቸዋል። አንዳንዴ ይህ የሚደረግ ለማደኑ እንዲበዙ ነው። በመላው ዓለም በጠቅላላ አሁን ምናልባት 125 ሺህ ያህል ዝባድ በሬዎች ይኖራሉ።

የእንስሳው ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«ቂቪዩት» የተባለ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ሱፍ ይሰጣሉ። አልፎ አልፎ ብቻ የዝባድ በሬዎች ለሱፍ፣ ለወተትና ለሥጋ ለማዳ እንስሶች ተደርገዋል።