የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን

ከውክፔዲያ
ብሔራዊ ቡድኑ በ2008 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ዋንጫ ሲሟሟቅ

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን (አፍሪካንስ፡ Suid-Afrikaanse nasionale sokker span ስዊድ-አፍሪካንስ ናሲዮናል ሶከር ስፓን) ወይም ባፋና ባፋና ደቡብ አፍሪካን ወክሎ በእግር ኳስ ይወዳደራል። አስተዳዳሪው አካል የደቡብ አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ሲሆን መቀመጫው ሶከር ሲቲ ነው። በአሁኑ ጊዜ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፒትሶ ሞሲማኔ ሲሆን አምበሉ ደግሞ ስቲቨን ፒየናር ነው። በደቡብ አፍሪካ በነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ምክንያት ከ1992 እ.ኤ.አ. በፊት ቡድኑ በፊፋ ማዕቀብ ተጥሎበት ነበር። በ2010 እ.ኤ.አ. ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ አገር ስትሆን፣ የቡድኑ ሲፊዌ ሻባላላ የውድድሩን የመጀመሪያ ግብ አግብቷል። የቡድኑ ትልቅ ድል በ1996 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫን ማግኘቱ ነው።

ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

እግር ኳስ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ የታወቀው በ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ቅኝ ገዢነት አማካኝነት ነው። በአገሩ የነበረው የአፓርታይድ ሥርዓት ፬ በዘር የተለያዩ የእግር ኳስ ማህበራት እንዲኖሩ አድርጓል።

ደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያግብፅ እና ሱዳን ጋር በመሆን የፊፋን 1953 እ.ኤ.አ. ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል። በዚህም ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ሀገራት በፊፋ ውክልና እንዲያገኙ ጠይቀዋል። በዚህም የተነሳ በ1956 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ተመስርቷል።

የአሁን ተጫዋቾች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፳፫ ተጫዋቾችን ያቀፈ ቡድን በግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ከግብፅ ጋር ለሚደረገው የ2012 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ ማጣሪያ ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም ፬ ሌላ ተጫዋቾች ለምልከታ ተጠርተዋል።

ጨዋታዎችና ጎሎች እስከ ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ድረስ ትክክል ናቸው።

ቁጥር ቦታ ተጫዋች የትውልድ ቀን ጨዋታዎች ጎሎች ክለብ
በረኛ ዌይን ሳንዲላንድስ ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ
ተከላካይ ሞርጋን ጉድ መጋቢት ፲፬ ቀን ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. 13 0 ደቡብ አፍሪካ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ
ተከላካይ ሲያንዳ ኩሉ ታኅሣሥ ፳ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ
ተከላካይ ሙሎሞዋንዳው ማቶሆ የካቲት ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ብሎምፎንቲን ሴልቲክ
ተከላካይ ፕሪንስ ህሌላ ግንቦት ፳ ቀን ፲፱፻፸፮ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ብሎምፎንቲን ሴልቲክ
ተከላካይ ምዙቩኪሌ ቶም ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. 1 0 ደቡብ አፍሪካ ጎልደን አሮውስ
ተከላካይ ሲያንዳ ዝዋኔ ግንቦት ፳፮ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ጎልደን አሮውስ
ተከላካይ ሲያቦንጋ ሳንግዌኒ መስከረም ፲፱ ቀን ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. 5 1 ደቡብ አፍሪካ ጎልደን አሮውስ
ተከላካይ ቴፉ ማሻማይቴ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አከፋፋይ ህሎምፎ ኬካና ግንቦት ፲፭ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ብሎምፎንቲን ሴልቲክ
አከፋፋይ ታንዱዪሴ ኩቦኒ ግንቦት ፲፬ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. 10 0 ደቡብ አፍሪካ ጎልደን አሮውስ
አከፋፋይ ታንዳኒ ንትሹማዬሎ ሚያዝያ ፲፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ
አከፋፋይ ታቦ ማትላባ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ፍሪ ስቴት ስታርስ
አከፋፋይ ኧርዊን ኢሳክስ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ሳንቶስ
አከፋፋይ ሲፊሶ ምየኒ ሰኔ ፫ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አጥቂ በርናርድ ፓርከር መጋቢት ፯ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. 35 10 ግሪክ (አገር) ፓንሴራይኮስ
ተከላካይ ቩዪሲሌ ዋና ታኅሣሥ ፳፫ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ሳንቶስ
አከፋፋይ ሌህሎሆኖሎ ማጆሮ ነሐሴ ፲፫ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ አማዙሉ
አጥቂ ካትሌጎ ምፌላ ኅዳር ፳ ቀን ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. 38 19 ደቡብ አፍሪካ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ

ተጨማሪ ተጫዎቾች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቁጥር ቦታ ተጫዋች የትውልድ ቀን ጨዋታዎች ጎሎች ክለብ
ተከላካይ ፑንች ማሴናሜላ ጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ካይዘር ቺፍስ
አከፋፋይ ሲፊሶ ምየኒ ሰኔ ፫ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. 1 0 ደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አጥቂ ቦንጎልዌቱ ጃዪያ መጋቢት ፲፪ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 0 0 ደቡብ አፍሪካ ዊትስ ዩኒቨርስቲ
አጥቂ ከርሚት ኢራስመስ ሐምሌ ፩ ቀን ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. 1 0 ደቡብ አፍሪካ ሱፐርስፖርት ዩናይትድ