ያዋን

ከውክፔዲያ

ያዋን (ዕብራይስጥיָוָן) በኦሪት ዘፍጥረት 10 መሠረት የያፌት ልጅና ከኖህ 16 ልጅ ልጆች አንዱ ነው።

የተለመደው አስተያየት ፍላቭዩስ ዮሴፉስ እንደሚለው፣ ያዋን የግሪክ ሕዝብ አባት ሆነ።

«ያዋን» ማለት በዕብራይስጥ ደግሞ ለግሪክ አገርና ለግሪኮች ሁሉ ይጠቅማል። የጥንት ምሥራቅ ግሪኮች ወገን «ኢዮኔስ» (ቀድሞ «ያዎኔስ») ወይም ኢዮናውያን የተዛመደ ነው። የግሪክ ሕዝብ ይህን በሚመሳስሉ ስሞች በመካከለኛ ምስራቅና በሕንድ (ሳንስክሪት፦ «ያዋና») ይታወቅ ነበር። በጥንታዊ ግሪኮች ልማድ ደግሞ የኢዮናውያን አባት የአፖሎ ልጅ ኢዮን ይባላል።

ዘፍጥረት 10 ደግሞ የያዋን ልጆች ይዘረዝራል፦

ትንቢተ ዳንኤል 8:21-22 እና 11:2 የያዋን ንጉሥ ሲጠቀስ ይህ ታላቁ እስክንድር ማለት እንደ ሆነ ብዙ ጊዜ ይተረጎማል።