ደርባ

ከውክፔዲያ

ደርባ የቦታ መጠሪያ ሲሆን ይህውም ቦታ በቀድሞ አጠራር ሸዋ ክ/ሃገር በሱሉልታ አውራጃ ውስጥ ከአዲስ አበባ በሰሜን በኩል 63 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ደርባ ትንሽ ከተማ ሲሆን ወደ 3000 የሚጠጋ ነዋሪዎች አሉት።

ደርባ ቃሉ ከኦሮምኛ ቅዋንቅዋ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም «እርሰዎ ይለፉ» ማለት ነው። የገጠር ከተማዋ ስያሜ የመጣው በምጥሰት ሲሆን ዙርያዋን ዳር በገደል ከመታጠርዋ የተነሳና ማለፍያ ስለሌለ ደርባ ተባለ «በሉ ይለፉ!» እንደማለት።