ደበበ እሸቱ

ከውክፔዲያ

ደበበ እሸቱ (1936 ዓ.ም. ተወልደው) ስመ ጥሩ ተዋናይ ሲሆኑ በእሁኑ ጊዜ የቅንጅት ቃል አቀባይ ሆነዋል። ከፊልሞቻቸው ሚናዎች መሃል በዓለም ከሁሉ የታወቀው በShaft in Africa (1973 እ.ኤ.አ.) እንደ 'ዋሳ' ነበረ። ዘሰይለር ፍሮም ጂብራልታር፤ ዘግሬቭ ዲገር፤ እና ሌሎችም

ትምህርታቸውን በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ጨርሰው ወደ ደብረ ብርሃን መምህራን ማሰልጠኛ ት/ቤት ገቡ። ነገር ግን በ1953 ዓ.ም. በመንግሥቱ ነዋይ እና በገርማሜ ነዋይ መሪነት በተካሄደው የመንግሥት ግልበጣ ሽብር ወቅት ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ኢሉባቦር ታስረው ከ1 አመት በላይ እዚያ ቆዩ።

መጀመሪያ በቴያትር የታዩት በመንግስቱ ለማ በተጻፈው ያላቻ ጋብቻ ሲሆን ከዚያ በአንዳንድ እንግሊዝኛ ትርኢት (The game of chesse, 'Waiting for Godot') እንዲሁም በራዲዮም ሆነ በቴሌቪዥን ተጫወቱ።

ከዚያ በኋላ በሀንጋሪ አገር ከወጋየሁ ነጋቱ ጋራ ቴያትር አጠኑና ወደ አገራቸው ተመልሰው ደበበ 'ንጉሥ ሄሮድያስ' በተባለ ድራማ የአርእስቱ ሚና ተጫወቱ።

ከዚህ በላይ በሀገር ፍቅር ቴያትር እንደ ዋነኛ ዳይረክተር፣ በመረጃ ሚኒስቴር እንደ ጋዜጠኛ፣ እና ከስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ጋር በቁም ነገር መጽሔትበባለቤትነትና አዘጋጂነት አገልግለዋል።

ለአፍሪካዊ ቴያትር ስላደረጉት አስተዋጽኦአቸው ሽልማት በ1991 ዓ.ም. ከቦስቶን ከተማ እና በ1994 ከአትላንታ ከተማ በአሜሪካ ተቀበሉ። ከዚህ በላይ በ1994 ዓ.ም. የጣይቱ ሽልማት ተቀባይ ነበሩ።

የ30 አመት ሚስታቸው ው/ሮ አልማዝ እና እሳቸው 4 ልጆች አሏቸ ከሴት ልጆቹም 2ቱ በ1 ቀን ውስጥ በ1995 ዓ.ም. ለባሎቻቸው ተዳሩ።

በቅርብ ጊዜ ከፖለቲካ ነክ ሚናቸው የተነሣ እቶ ደበበ ከ1998 እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ የቃላቲ እስረኛ ነበሩ።

ፊልሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • Gouma (1975)
  • Zelda (1974)
  • Shaft in Africa (1973) - Wassa
  • Una Stagione all'inferno (1970)
  • The Sailor from Gibraltar (1967)