ዳካ

ከውክፔዲያ

ዳካባንግላደሽ ዋና ከተማ ነው። ከ7ኛ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሰዎች በሥፍራ ኑረውበታል። በ1600 ዓ.ም. የሙጋል መንግሥት ዋና ከተማ ሆነ። ከ1600 እስከ 1620 ዓ.ም. ድረስ የከተማው ስም ጃሃንጊር ናጋር ነበረ።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 12,560,000 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 5,378,023 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 23°42′ ሰሜን ኬክሮስ እና 90°22′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

Gallery[ለማስተካከል | ኮድ አርም]