ገንዘብ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ሳንቲም እና ብር – በብዛት በስራ ላይ በተጨባጩ አለም ውስጥ የተሰማሩ የገንዘብ አይነቶች ናቸው። ገንዘብ ከነዚህ ውጭ ሊሆን ይቻላል።

በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሸቀጥ (አሰፈላጊ እቃ) ና አገልግሎት መግዢያ እንዲሁም እዳ መክፈያ የሚያገለግ ማንኛውም ነገር ሁሉ ገንዘብ ይባላል።

የጥንቱ ገንዘብ ዋጋ ይመነጭ የነበረው ከራሱ ከተሰራበት እቃ ዋጋ ነበር (ለምሳሌ፡ ከወርቅ የተሰራ ሳንቲም) ። በዚህ ምክንያት እንዲህ አይነቱ ገንዘብ የኮሞዲቲ ገንዘብ ይባላል። በአሁኑ በአለማችን የሚሰራባቸው ገንዘቦች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ዋጋ የላቸውም (ለምሳሌ ከተልባ እግር የተሰራው ዶላር በራሱ ዋጋ የለውም) ። ይህ አይነት ገንዘብ ፊያት ገንዘብ ሲባል ዋጋው የሚመነጨው የአንድ አገር መንግስት ህጋዊ መገበባያ ብሎ ስላወጀው ብቻ ነው። ህጋዊ መገበባያ ሲባል ለማንኛውም በዚያ አገር ውስጥ ላለ እዳ ይህ የታወጀው ገንዘብ እንደ ክፍያ ሲቀርብ "አይ! አልቀበልም" ማለት ክልክል ነው። በዚህ ምክንይት የፊያት ገንዘብ ዋጋ ከመንግስት ሃይል ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው።

ያንድ ዘመናዊ ሃገር የገንዘብ አቅርቦት በሁለት ይከፈላል፣ ይኸውም ተጨባጭ የሆነው የታተመው ብርና በማይጨበጥ መልኩ በባንክ ቤት ተጠራቅሞ ያለው በቼኪንግ እና ሴቪንግ የሚከፈለው የባንክ ሒሳብ ነው። ባብዛኛው ጊዜ እኒህ የ ባንክ ሒሳቦች ታትሞ ከቀረበው ብር በላይ ናቸው። በምናባዊ አለም ውስጥ የተቀመጡት እነዚህ የቁጥር ሰነዶች ምንም እንኳ የማይታዩና የማይዳሰሱ ቢሆንም ልክ እንደ ጥሬ ብር እኩል ለመሸጥና ለመለወጥ ያገለግላሉ። [1][2] [3]

[ለማስተካከል] ታሪክ

ከክርስቶስ ልደበት በፊት በ640 ዓ.ዓ. ታትሞ የነበረው የመጀመሪያ ነው ተብሎ የሚታመነው የጥንቱ የልድያ አገር ሳንቲም
  • የጥንቶቹ ሰወች እቃን በቃ በመለዋወጥ መገበያየት ቻሉ። ይህም በማይተዋወቁ ሰወች ዘንድ ነበር። በሚተዋወቁ ግን የስጦታ ልውውጥ ይደረግ ነበር።[4]
  • ቀስ ብሎ የተለያዩ ባህሎች ኮሞዲቲ ገንዘብ መጠቀም ጀመሩ። በተለይ ዛጎል በብዙ ህብረተሶቦች ዘንድ እንደ መገበባያ ገንዘብ ይጠቅም ነበር። [5] እንደ ታሪክ ጸሃፊው ሄሮዱተስ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሳንቲም እና የብር ሳንቲም መጠቀም የጀመሩት ልድያውያን ነበር።.[6] በኢትዮጵያም በአክሱም ነገሥታት የታተሙ የወርቅ ሳንቲሞች ስራ ላይ ውለዋል።
  • ከዚህ ቀጥሎ የተነሳው ተወካይ ገንዘብ የሚባለው ገንዘብ አመጣጡ እንዲህ ነው። ወርቅብር ነጋዴወች ለደንበኞቻቸው ደረሰኝ በመጻፍ፣ ያንን ደረሰኝ ደምበኞች በማምጣት በፈለጉት ሰዓት ወርቁንና ብሩን ማግኘት ቻሉ። ቀስ በቀስ ደረሰኙ በወርቁና በብሩ ቦታ ተተክቶ እንደ ሙሉ ገንዘብ መስራት ጀመረ። የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በሶንግ ስርወ መንግስት (970 ዓ.ም. - 1276 ዓ.ም.) ዘመን በቻይና አገር ነበር፣ ብሮቹም ያወዚ ይባሉ ነበር፣ አመጣጣቸውም ከላይ እንደተገለጸው የደረሰኝ ጽሁፈትን ተከትሎ ነው። አውሮጳ ውስጥ የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በ1661፣ ስዊድን አገር ነበር። በዚህ ወቅት እያንዳንዱ ጥሬ የወረቀት ብር ወደ ተወሰነ የወርቅ ክብደት የሚቀየርበት ስሌት ነበረው። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀሪያ ላይ ይህ በወርቅ የተደገፈ የተሰኘው የገንዘብ ስርዓት በመላው ዓለም ተንሰራፋ።
  • ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በብሬቶን ውድስ ስብሰባ፣ አብዛኞቹ የአለማችን አገሮች ፊያት ገንዘብን በማጽደቅ ገንዘባቸውን በቀጥታ በወርቅ ከመደገፍ ይልቅ ከአሜሪካን ዶላር አንጻር እንዲተረጎም አደረጉ። የአሜሪካን ዶላር በተራው በወርቅ የተደገፈ ነበር።
  • በ1971 የአሜሪካን መንግስት ዶላሩን በወርቅ መደገፍ/መተርጎም አቆመ። ከዚህ በኋላ ሌሎቹም አገሮች የየራሳቸውን ገንዘብ ከአሜሪካን ዶላር አንጻር መተርጎም አቆሙ። በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የአለማችን ገንዘቦች በወርቅም ሆነ በሌላ ቋሚ ነገር የሚደገፉ ሳይሆን በየአገሩ ባሉ መንግስታ እንደ ህጋዊ መገበባያ በወጡ አዋጆች ምክንያት ነው።


የገንዘብ አይነቶች

[ለማስተካከል] ማጣሻ

  1. ^ "Learn More About Coins and Money — Treasure Trove - Philadelphia Fed". Philadelphia Fed.. በ2009-04-20 የተወሰደ.
  2. ^ "On2 Money / A History of Money". Pbs.org. በ2009-04-20 የተወሰደ.
  3. ^ Bernstein, Peter, A Primer on Money and Banking, and Gold, Wiley, 2008 edition, pp29-39
  4. ^ Graeber, David. 'Toward an Anthropological Theory of Value'. pp. 153-154.
  5. ^ Kramer, History Begins at Sumer, pp. 52–55.
  6. ^ Herodotus. Histories, I, 94
የኔ መሣርያዎች

Variants
Actions
የማውጫ ቁልፎች
ጠቃሚ መሣሪያዎች
በሌሎች ቋንቋዎች