ጋምብሪቪ

ከውክፔዲያ

ጋምብሪቪ (ሮማይስጥ፦ Gambrivii፣ ጋምብሪቫውያን) የጌርማኒያ ጎሣ ነበሩ።

መጀመርያ በስትራቦን «ጋማብሪቪ» ተብለው ተጠቀሱ።[1]ካቲካቱዋሪ እና ኬሩስኪ ጋራ በአንድ ስብስባ እንደ ነበሩ ይለናል፤ ስለዚህ በቬዘር ወንዝ አካባቢ እንደ ተገኙ ይሆናል። ጋምብሪቪ ደግሞ በታኪቱስ ጌርማኒያ ይታያሉ። በአፈ ታሪካቸው ከማኑስ ልጅ ልጆች ከተወለዱት ነገዶች መካከል ይላቸዋል።[2] (ደግሞ ጋምብሪቪዩስ ይዩ።) ሱጋምብሪ በተባለው ብሔር ውስጥ እንደ ተቆጠሩ ይመስላል።

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • Max Ihm : Gambrivii. In: Paulys Realencyclopädie der classischen Altertumswissenschaft (RE). Band VII,1, Stuttgart 1910, Sp. 691.
  • Günter Neumann , Dieter Timpe : Gambrivi. In: Reallexikon der Germanischen Altertumskunde (RGA). 2. Auflage. Band 10, Walter de Gruyter, Berlin/New York 1998, ISBN 3-11-015102-2, S. 406–409.
  1. ^ Strabon Geographie VII, 291
  2. ^ Tacitus Germania 2