ግሪልድ ቺዝ ሳንድዊች

ከውክፔዲያ

በ15 ደቂቃ የሚደርስ

የሚያስፈልጉ ነገሮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • 4 በስሱ የተቆረጠ ዳቦ
  • 3 የሾርባ ማንኪያ የገበታ ቅቤ፣ ሦስቱም ተከፋፍሎ
  • 2 በስሱ የተቆረጠ ቼዳር ቺዝ

አሠራሩ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የታጠበውን መጥበሻ በመካከለኛ ሙቀት ማጋል። የተቆራረጠው ዳቦ በአንደኛው ጎን ቅቤ መቀባት። የተቀባውን ዳቦ መጥበሻው ላይ አስቀምጦ ላዩ ላይ አንድ የተቆረጠ ችዝ ማድረግ።

ሌላ ዳቦ ቅቤ በመቀባት ከቺዙ በላይ ማስቀመጥ። (ቅቤ የተቀባው የዳቦው ክፍል ወደ ላይ መሆን አለበት።) ዳቦው ቡናማ መልክ እስኪይዝ ድረስ መጥበሻው ላይ ማጋሉን መቀጠል። ቺዙም መቅለጥ ይኖርበታል። የቀሩትን ሁለት ዳቦዎችም በተመሳሳይ መልኩ መጥበስና ማቅረብ።