ግሽጣ
ከውክፔዲያ
ግሽጣ (ሮማይስጥ፦ Annona muricata) ከሜክሲኮ እስከ ስሜናዊ ደቡብ አሜሪካ ድረስ የሚገኝ ሁሌ ለምለም ቅጠለ ስፋፊ አባባማ ዛፍ አይነት ነው። ከዚህ ደግሞ ዛሬ በፊልፒንስና በደቡብ-ምሥራቅ እስያ ይበቅላል። በጣም በሞቀ አገር ስለሚበቅል ከ3 ሴንቲ ግሬድ በታች ሊኖር አይችልም።
ፍሬውን መብላት ከባድ ሆኖ አብዛኛው ግዜ ለጭማቂ ይጠቅማል። ብዙ ካርቦሃይድሬት በተለይም ፍሩክቶስ አለበት። ደግሞ ቪታሚን-ሲ፣ ቪታሚን-ቢ1፣ ቪታሚን-ቢ2፣ ይበዛሉ። ፍሬው፣ ዘሩ፣ እና ቅጠሉ በተገኝባቸው አገሮች እንደ ተፈጥሮአዊ መድኅኒት ይጠቅማል። ከዚህ በላይ በአንዳንድ ትንተና ዘንድ የዛፉ ቅጠልና ግንድ የነቀርሳ (ካንሰር) ህዋስ እንደሚያጥፋ ችሎታ አለው።