ጥሩነሽ ዲባባ

ከውክፔዲያ
የሜዳሊያ መዝገብ

ጥሩነሽ በ2008 እ.ኤ.አ. በተካሔደው ቢስሌት ጨዋታዎች.
Women's Athletics
 ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ
Olympic Games
ወርቅ 2012 London 10000 m
ወርቅ 2008 Beijing 10000 m
ወርቅ 2008 Beijing 5000 m
ነሐስ 2004 Athens 5000 m
World Championships
ወርቅ 2003 Paris 5000 m
ወርቅ 2005 Helsinki 5000 m
ወርቅ 2005 Helsinki 10000 m
ወርቅ 2007 Osaka 10000 m
ወርቅ 2013 Moscow 10000 m
World Cross Country Championships
ወርቅ 2003 Lausanne Junior race
ወርቅ 2005 Saint-Galmier Short race
ወርቅ 2005 Saint-Galmier Long race
ወርቅ 2006 Fukuoka Long race
ወርቅ 2008 Edinburgh Senior race
ብር 2002 Dublin Junior race
ብር 2004 Bruxelles Short race
ብር 2007 Mombasa Senior race
African Championships
ወርቅ 2008 Addis Ababa 10000 m
ወርቅ 2010 Nairobi 10000 m
ብር 2006 Bambous 5000 m
World Junior Championships
ብር 2002 Kingston 5000 m

ጥሩነሽ ዲዲባባመስከረም 21 ቀን 1978 ዓ.ም. በኢትዮጵያአርሲ ክፍለ ሀገር በቼፋ ወረዳ ከኦሮሞ ብሄረሰብ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት 3 ናት። የጥሩነሽ አስተዳደግ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው። ነገር ግን የጥሩነሽ ቤተሰቦች የረጅም ርቀት አትሌቶች ናቸው። አክስቷ ደራርቱ ቱሉ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ እና አንድ ጊዜ ደግሞ የ 10000 ሜትር አሸናፊ እና የብዙ አገር አቋራጭ ውድድር አሸናፊ ነበረች። ሌላ አክስቷም በቀሉ ዲባባ ጥሩ ሯጭ ነበረች ጥሩነሽ ልጅ እያለች በበቆጂ ስትኖር። ሌላዋ እህትዋ እጅጋየሁ ዲባባ ከጥሩነሽ ቀደም ብላ መሮጥ ጀምራ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የቤተሰብዋን ፈለግ መከተል የጀመረችው እድሜዋ ከፍ ካለ በኋላ ነው። ጥሩነሽ ዲባባ ከ ሯጭ ቤተሰብ ብትፈጠርም ለመሮጥ ግን ምንም ፍላጎት አልነበራትም። ቱሉ በባርሴሎና ኦሎምፒክ በ 10000 ሜትር ባሸነፈች በሰባት አመቱ ጥሩነሽ ወደ አዲስ አበባ በ 2000 ዓ/ም መንገድ ጀመረች። ነገር ግን በቀሉ ዲባባ አባል ከሆነችበት ከእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ቡድን ስፖርት መስሪያ ክበብ ውስጥ አስመዝግባት ልምምድ ቀጠለች። ጥሩነሽ ዲባባ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች አንዷ ለመሆን በቃች። ጥሩነሽ ዲባባ በ 14 አመት እድሜዋ በጣም ወጣት እና ሰውነትዋም ተሰባሪ ይመስል ነበር። ብዙዎችም በሩጫ ምንም ተስፋ እንደሌላት እና ሩጫው የሚጠይቀውን ጠንካራ ሰውነት የላትም ብለው ያምኑ ነበር። ጥሩነሽ ዲባባ የኢትዮጵያ የረጅም ርቀት ተወዳዳሪ አትሌት ናት። በ 5000ሜትር የአለም ክብረ ወስን ባለቤት ስትሆን በ5000 ሜትር እና በ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር አሸናፊ ናት። ጥሩነሽ አራት የአለም አቀፍ ውድድር እና አምስት የአገር አቋራጭ ውድድር አሸነፊ ናት። በቅጽል ስም “የሕጻን ፊት ያላት ደምሳሽ” በማለት ይጠሩዋታል።

ውድድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያ አለም አቀፍ የውጪ ውድድር ያደረገችው በ 2001 በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ ነው። ውድድሩን ስታካሂድ የ 15 አመት ልጅ ነበረች በዚህ ውድድር አምስተኛ በመሆን ጨርሳለች። በ 2003 በተደረገው የአፍሮ ኤሽያ ውድድር ላይ በ 5000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። የጥሩነሽ ዲባባ አስደናቂ ውጤቶች ማምጣት የጀመረችው በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ በ 2003 2005 እና 2007 ላይ ነው። ጥሩነሽ በ 2003 በ 5000 ሜትር ተስፈንጥራ በመውጣት የስፔይኗን ማርታ ዶሚኒጌዝ እና የኬንያዋን ኤዲት ማሳያ ቀድማ በመግባት ነው። በወቅቱ የታወቀች አትሌት ባለመሆኗ ውድድሩን ያስተላልፉ የነበሩት እንግሊዛዊ ስቲቭ ክራም እና ብሬንዳን ፎስተር ውድድሩ 100 ሜትር እስኪቀረው አንድም ጊዜ ስሟን ሳይጠሩ ቀርተዋል። በ 2005 ውድድር ላይ ተስፈንጥራ በመውጣት ብርሀኔ አደሬን እና እህታዋን እጅጋየሁን ቀድማ በመግባት የመጀመሪያዋ 5000 / 10000 ሜትር የወርቅ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች። በ2007 ኦሳካ ላይ በተካሄደው የ 10000 ሜትር ውድድር የቱርክዋን ኤልቫን አቢይ ለገስን ተስፈንጥራ በመቅደም በ 31:55.41 አሽናፊ ሆናለች። በ 2004አቴንስ ኦሎምፒክ5000ሜትር ጥሩነሽ ሶስተኛ ወጥታለች በመሰረት ደፋር እና በ ኢሳቤላ ኦቺቺ በመሸነፍ። በሁኔታው ብዙ ሰዎች ቢበሳጩም የ 19 አመትዋ ጥሩነሽ የመጀመሪያዋ ወጣት ባለ ኦሎምፒክ ሜዳል ኢትዮጵያዊ አትሌት አሸናፊ አድርጓታል። በ2006ወርቃማው ማህበር ውድድር ከስድስት የወርቅ ሜዳሊያ አምስቱን አሸናፊ ሆናለች ። (5,000 ሜ) በዚህም $83,333 ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

የጥሩነሽ ዲባባ ሀይለኛ ተፎካካሪ መሰረት ደፋር ናት። ሁለቱንም በአንድ ውድድር ላይ ለማሳተፍ ታስቧል ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚሳካው በውድድር ላይ ብቻ ነው።

የጥሩነሽ ዲባባ የአሯሯጥ ዘዴ በመጨረሻው ዙር ላይ ተስፈንጥሮ በመውጣት ማሸነፍ ነው። በመጨረሻው የ 10000 ሜትር ውድድር ላይ በ 2005 ዓ/ም የመጨረሻውን 400 ሜትር በ 58.33 ሴኮንድስ ነው የጨረሰችው። ጥሩነሽ ዲባባ በአገር አቋራጭ ሩጫም የተሳካ ውጤት አምጥታለች። ጥሩነሽ ዲባባ አለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ባሰናዳው አለም አቀፍ የአገር አቋራጭ ውድድር አምስት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነች። ውድድሩም የወጣቶች (በላውሳኔ 2003) አንድ አጭር ርቀት (በ ሴይንት ጋልሚየር 2005) እና ሌሎች ሁለት ረጅም ርቀት (በ ሴይንት ጋልሚየር 2005 እና በፉኩኦካ 2006 ) ከ2007 ጀምሮ በየምድቡ አንድ ውድድር ብቻ ይካሄዳል። ጥሩነሽ ዲባባ ሞምባሳ በተካሄደው ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸልማለች። በ ኤዲንበርግ ላይ በተካሄደው የወርቅ ሜዳሊያ በ 2008 ተሸላሚ ናት።

የወርቅ ሜዳሊያ በኦሎምፒክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጥሩነሽ ዲባባ በ 2008 ኦስሎ በተካሄደው የ 5000 ሜትር በ14 ደቂቃ 11.15ሴኮንድስ በመግባት በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች።

ጥሩነሽ ዲባባ በ ነሐሴ 15 2008 በቤጂንግ ኦሎምፒክ በተደረገው የ 10 000 ሜትር ውድድር በ 29:54.66 በመግባት በውድድሩ አንደኛ በመውጣት የአዲስ ክብረ ወሰን ባለቤት ለመሆን በቅታለች። አሮጌው ሰአት 30:17.49 ነበር። የክብረ ወሰኑም ባለቤት የነበረችው የጥሩነሽ ዲባብ አክስት ደራርቱ ቱሉ ነበረች። ይህም ሰአት የተመዘገበው በሲድኔ ኦሎምፒክ2000ዓ/ም ነበር። አዲሱ የጥሩነሽ ዲባባ ክብረ ወስን ሁለተኛው ፈጣኑ የ 10000 ሜትር ሰአት ሲሆን ለአፍሪካ ደግሞ ፈጣኑ ክብረ ወሰን ነው። የቀድሞው የአፍሪካ ክብረ ወሰን (30:04.18) ነበር በ 2003 አለም አቀፍ ውድድር ላይ በ ብርሃኔ አደሬ የተመዘገበ።

ከአንድ ሳምንት በኋላ በነሐሴ 22 2008 በ 5000 ሜትር መሰረት ደፋርን ቀድማ በመግባት በ 15:41.40 የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። በዚህ ኦሎምፒክ በሁለት ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘቷ በአለም የመጀመሪያዋ የሴት አትሌት ሆናለች። በ 5000 እና በ10000 ሜትር በአንድ ኦሎምፒክ አሸናፊ በመሆኗ።

2008 የቤት ውስጥ እና የሜዳ ዜና የአመቱ ታላቅ አትሌት በማለት ሸልሟታል። በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽንም አስደናቂ የሴት አትሌት በማለት ሽልማት አበርክቶላታል። ተመሳሳይ ሽልማት በ 2005 ቀደም ብሎ ተበርክቶላታል።

2009 በጤና ችግር ምክንያት በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ባዘጋጀው አገር አቋራጭ ውድድር በአማን ተሳታፊ ሳትሆን ቀርታለች። እንዲሁም በ 2009 በበርሊን በተካሄደው የአለም አቀፍ ውድድርም አልተሳተፈችም።

በህዳር 15 2009 በዜቬኡቬሌንሉፕ(ሰባት ኮረብታ) በተካሄደው የ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ውድድር በኔዘርላንድ ኒጄምገን የካዮኮ ፉኩሺን የ15 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰን በግማሽ ደቂቃ በመስበር በ 46:28 አሸናፊ ለመሆን በቅታለች። ከ 2005 በኋላ ይህ ውድድር የመጀመሪያዋ ነበር። ይህንንም አገር አቋራጭ የውጭ ውድድር እንደወደደችው ተናግራለች። ነገር ግን በቤት ውስጥ ውድድር እንደምትቆይ ተናግራለች።

በሃምሌ 27 2012 እ.ኤ.አ በለንደን በተካሄደው የ10000 ሜትር የኦሎምፒክ ውድድር 30 ደቂቃ ከ20.75 ሰከንድ ገብታ ውድድሩን በማሸነፍ በኦሎምፒክ ያገኘችውን የወርቅ ሜዳሊያ ቁጥር ወደ ሶስት ከፍ አድርጋለች። በመሆኑም በኢትዮጲያ ውስጥ እጅግ ውጤታማ የሆነ አትሌትነትን ቦታ ከቀነኒሳ በቀለ ጋር ተጋርታለች። በጋጠማት ጉዳት ምክንያት ለ16 ወራት ከውድድር ተገልላ ታህሳስ 2012 ወደ ውድድር የተመለሰችው ጥሩነሽ ውድድሩ ሊጠናቀቅ አንድ ዙር ሊቀረው አካባቢ አፈትልካ በማምለጥ በረጅም ርቀት አሸንፋለች። [1]

የግል ሕይወት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ጥሩነሽ ዲባባ ስለሺ ስህንን አግብታለች። ስለሺ ስህን በ2004 እና 2008 የ 10000 ሜትር ኦሎምፒክ ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ አትሌት ነው።

ጥሩነሽ ዲባባ ከቤጂንግ ኦሎምፒክ በኋላም የእስረኞች ማረሚያ ፖሊስ ለቡድኑ እና ለሀገርዋ ላደረገችው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የ ሌ/ኮለኔልነት ማዕርግ ተሰጥቷታል። በስሟም በአዲስ አበባ ውጭ ሆስፒታል ተሰይሞላታል።

የአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ውድድር ውጤት

የአልማዝ ማህበር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አልማዝ ማህበር በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ሲሆን የተጀመረውም በ 2010 ነው።

ጥሩነሽ ዲባባ የ 10,000 ሜትር ድልዋን ስታከብር በ 2007 በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር.
አመት ቦታው ውድድሩ ውጤት ሰአት
2010 Adidas Grand Prix, New York City 5000 m 1st 15:11.34

የአለም አትሌቲክስ መጨረሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አለም አትሌቲክስ መጨረሻ በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 2003 እስከ 2009.

አመት ቦታው ውድድር ውጤት ሰአት
2003 Monaco 5000 m 3rd 14:57.87
2005 Monaco 5000 m 2nd 14:46.84
2006 Stuttgart 3000 m 2nd 8:34.74
5000 m 1st 16:04.77
2009 Thessaloniki 5000 m 2nd 15:25.92

የወርቅ ማህበር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ወርቅ ማህበር በየአመቱ የሚካሄድ የቤት ውስጥ እና የሜዳ ውድድር ነው። ውድድሩም የሚዘጋጀው በአለም አቀፍ አትሌቶች ፌዴሬሽን ነው የተጀመረውም በ 1998 እስከ 2009.

አመት ቦታው ውድድር ውጤት ሰአት
2002 Bruxelles 3000 m 11th 8:41.86
Berlin 5000 m 6th 14:49.90
2003 Oslo 5000 m 3rd 14:39.94
Roma 5000 m 4th 14:41.97
2004 Bergen 5000 m 2nd 14:30.88
Roma 5000 m 4th 14:47.43
2005 Roma 5000 m 1st 14:32.57
2006 Oslo 5000 m 1st 14:30.40
Paris Saint-Denis 5000 m 1st 14:54.24
Roma 5000 m 1st 14:52.37
Zürich 5000 m 1st 14:45.73
Bruxelles 5000 m 1st 14:30.63
Berlin 5000 m 2nd 15:02.87
2007 Paris Saint-Denis 5000 m 1st 15:21.84
2008 Oslo 5000 m 1st 14:11.15
Roma 5000 m 1st 14:36.58

የውጭ ውድድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ውድድር ሰአት ቀኑ ቦታው
3,000 m 8:29.55 July 28, 2006 London
5,000 m 14:11.15 (WR) June 6, 2008 Oslo
10,000 m 29:54.66 August 15, 2008 Beijing
15 km (road) 46:28 (WR) November 15, 2009 Nijmegen

በቤት ውስጥ ውድድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ውድድር ሰአት ቀኑ ቦታው
3,000 m 8:33.37 January 26, 2008 Boston
5,000 m 14:27.42 January 27, 2007 Boston

የቪዲዮ ቃለ መጠይቅ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ማጣቀሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "Tirunesh bagged the first Gold Medal at London 2012 for Ethiopia". thearadaonline.com (28 ሃምሌ 2012). Archived from the original on 2016-03-11. በ28 ሃምሌ 2012 የተወሰደ.

ወደ ውጭ የሚያገናኙ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]