ጥገኛ አምክንዮ

ከውክፔዲያ
ጥገኝነት የሚፋለሰው A እውነት ሆኖ B ውሸት ሲሆን ብቻና ብቻ ነው። ከላይ ባለው ቬን ምስል ይህ የውሸት ክፍል በነጭ ቀለም ተለይቶ ይታያል።
ጥገኝነት በሂሳብ ትርጓሜው እንዲህ ይሰፍራል

A → B ¬A B
የጥገኝነት አምክንዮን የሚተገብር የማብሪያ ማጥፊያ ትልም

ጥገኛ አምክንዮ በሁለት የአምክንዮ ዋጋወች የሚተገበር ሲሆን፣ ውጤቱ ውሸት የሚሆነው ቀዳሚ አረፍተ ነገሩ እውነት ሁኖ ተከታይ አረፍተ ነገሩ (ጥገኛ አረፍተ ነገሩ) ውሸት ሲሆን ብቻና ብቻ ነው። (ቀዳሚና ተከታይ አረፍተ ነገር ምን ማለት እንደሆነ ከታች ሙሉ ማብራሪያ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ ) ከአምክንዮ አንጻር ጥገኛ አምክንዮ ከአይደለም....ወይም... ጋር እኩል ነው። በሂሳብ አጻጻፍ፣ p ቀዳሚ አረፍተ ነገር (አስጠጊ) ቢሆንና q ተከታይ (ጥገኛ) ቢሆን፣ የጥገኝነት ዝምድናቸው እንዲህ ይጻፋል p → q ፡ ሲነበብ p ስለዚህ q ነው። ይህ እንግዲህ ከላይ እንደተጠቀሰው ከ አይደለም p ወይም q ጋር ምንም ለውጥ የለውም። ይህን የመጨረሻውን ግኝት

በምሳሌ እንይ፡

መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ናት፣ ስለዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ናት

ከላይ በጻፍነው ትርጓሜ አንጻር ሲተረጎም

መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ አይደለችም ወይም መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ናት

ከላይ የተጻፉትን አረፍተ ነገሮች አነጻጽረው እኩለነታቸውን ያረጋግጡ


የጥገኛ አምክንዮ ጸባዮች ትርጓሜ ከእውነታ ሰንጠረዥ አንጻር
* ትርጓሚያዊ እኩለንት: (~a ወይም b) p q p ⇒ q
*ጥገኝነት የራሱ ነጸብራቅ ነው: እውነት እውነት እውነት
*ጥገኝነት ተሻጋሪ ነው: እውነት ውሸት ውሸት
*ጥገኝነት ታዳይ ነው: ውሸት እውነት እውነት
ውሸት ውሸት እውነት

ሙሉ ማብራሪያ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ምሳሌ ፩፡

  • « ነገ ዝናብ ዘነበ፣ ስራ አልመጣም።»
ነገ ዝናብ ቢዘንብና ስራ ባልመጣ፣ እውነት ነኝ።
ነገ ዝናብ ቢዘንብና ስራ ብመጣ፣ ውሸት ነኝ።
ነገ ዝናብ ባይዘንብና ስራ ብመጣ -- እንዲሁም
ነገ ዝናብ ባይዘንብና ስራ ብቀር፣ ዝናብ ሳይዘንብ የማደርገውን ስላልተናገርኩ በሁለቱም አቅጣጫ ውሸታም ነህ የሚለኝ አይኖርም። ዝምታ በአምክንዮ እውነት ስለሆነ፣ ቀዳሚው አረፍተ ነገር ሃሰት እስከሆነ ድረስ፣ እውነት ነኝ።

ምሳሌ ፪፡

  • መሰረት አዲስ አበባ ከአለች፣ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ አለች።
መሰረት አዲስ አበባ ውስጥና ኢትዮጵያ ውስጥ ካለች ከላይ የሰፈረው አረፍተነገር እውነት ነው እንላለን
መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ብትሆንና ኢትዮጵያ ውስጥ ባትሆን ውሸት ነው እንላለን -- ግን ይሄ በተጨባጭ ሊሆን የማይችል ነገር ነው።
መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ከሌለች ከላይ የሰፈረው አረፍተ ነገር መሰረት የት እንዳለች አይነግረንም። ስለዚህ አረፍተነገሩ የማያውቀውን የማይናገር፣ የታይታነት የሌለበት ትሁት አረፍተ ነገር ነው።
መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ ከሌለች አረፍተ ነገሩ የት ትሁን የት፣ ጨረቃ ላይ ትውጣ ኢትዮጵያ ውስጥ ትኑር፣ ቻይና አገር ትብረር የርሱ ጉዳይ አይደለም። ስለማያውቀው አይናገርም።
እንግዲህ የጥገኛ አምክንዮ ይህን መሰረታዊ እውነታ በመቀበል የሚነሳ የአምክንዮ አይነት ነው። መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ አለች የሚለው ክፍል ቀዳሚ አረፍተ ነገር ሲባል መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ አለች የሚለው ተከታይ አረፍተነገር ነው። እዚህ ላይ፣ ከላይ እንዳስተዋልነው፣ ቀዳሚው አረፍተ ነገር ውሸት ቢሆን እንኳ ሙሉው አረፍተ ነገር ምንጊዜም እውነት እንደሆነ እንረዳለን። ስለሆነም የጥገኛ አምክንዮ ዋጋ ከነባራዊው አለም እውነታ ተነጥሎ መታየት አለበት። ጥገኛ አምክንዮ፣ ቀዳሚ አረፍተ ነገሩ ውሸት ከሆነ፣ አጠቃላይ አረፍተ ነገሩ ምንጊዜም እውነት ነው።

ምሳሌ ፫፡

  • መሰረት ሰው ካላይደለች፣ መሰረት ተራራ ናት።
እዚህ ላይ መሰረት ሰው ካልሆነች ብቻ ይህ አረፍተ ነገር ስለ ተከታዩ አረፍተ ነገር ሊመረመር ይችላል። ሆኖም መሰረት ሰው አይደለችም የሚለው ውሸት ስለሆነ፣ ስለተከታዩ አረፍተ ነገር የሚናገረው ነገር አይኖርም። በአምክንዮ ዝምታ እውነት ነው። ከላይ የተጠቀሰው አረፍተ ነገር ስለማያውቀው ስለማይናገር እውነት ነው ይባላል። ይህ እንግዲህ ከለተ ተለት ንግግር ዘይቤአችን አንጻር እንግዳ ይሆናል።

ምሳሌ ፬፡

  • መሰረት ሴት ናት፣ ስለዚህ ቢራቢሮ ፈረስ ነው።
ቀዳሚው አረፍተ ነገር ምንም እንኳ ምንጊዜም እውነት ቢሆን፣ ተከታዩ ውሸት ስለሆነ፣ ይህ ጥገኝነት (አጠቃላይ አረፍተ ነገሩ) ውሸት ነው እንላለን።