0
ከውክፔዲያ
| 0 | |
|---|---|
| ዜሮ |
ዜሮ ወይንም 0 ወይንም ፨ በቁጥር ጽሕፈት ወቅት የባዶነት ማመላከቻ ምልክት ነው። ዜሮ በራሱም ቁጥር ሲሆንም ያንድን መለኪያ ባዶነት ያመለክታል። ለምሳሌ የባዶ ስብስብ አባላት ቁጥር ዜሮ ነው እንላለን።
ታሪክ [ለማስተካከል]
የዜሮ ፅንሰ ሐሳብ በባቢሎኒያኖች የፈለቀ ሲሆን ይኼውም ከክርስቶስ ልደት በፊተ በ3ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። ሆኖም ባቢሎኒያኖቹ ዜሮን እኛ እንደምንጠቀምበት ሳይሆን እንደ ቦታ ያዢ ምልክት ነበር የሚጠቀሙበት። ለምሳሌ 304፣ ወይንም 450 ሲጽፉ 0 እዚህ ላይ የቁጥር አለመኖርንና ቦታ መያዝን ብቻ ያመላክታል።
ዜሮን እኛ በምንጠቀምበት መልኩ የተጠቀሙት ህንዶች ሲሆኑ ይሄውም ከክርስቶስ ልደተ በኋላ በ9ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ለህንዶች፣ ዜሮ ቦታ መያዣ ምልክት ብቻ ሳይሆን፣ እራሱን የቻለ ቁጥር ሲሆን ለስሌት የሚረዳ ነበር። በህንዶች ዘንድ 0 ለመደመር፣ ለመቀነስ፣ ለማካፈልና ለማባዛት ግልጋሎት ይውል ነበር።
አረቦች ከህንዶች የዚህ ቁጥር ጥበብ በመቅሰም ለአዲሱ ቁጥር ስፍር صفر የሚል ስያሜ ሰጡት። ትርጓሜውም ባዶ ማለት ነበር። ከአረቦቹ ይህን ቁጥር የቀሰመው ጣሊያኑ ፊቦናቺ ስፍር የሚለውን ወደ ዜፊር በመቀየር ቁጥሩ በ12ኛው ክፍለ ዘመን አውሮጳ እንዲስፋፋ ሆነ። በኋላም ዝፊር ወደ ዜሮ ተለውጦ ስሙ በዚህ ረጋ።
ዜሮና ሒሳብ [ለማስተካከል]
የዜሮ ጠባዮች [ለማስተካከል]
- መደመር: x + 0 = 0 + x = x. ዜሮን ሌላ ቁጥር ላይ መደመር ያን ቁጥር አይለውጥም
- መቀነስ: x − 0 = x and 0 − x = −x.
- ማባዛት: x · 0 = 0 · x = 0.
- ማካፈል: 0|x = 0, x እዚህ ላይ ዜሮ ያልሆነ ቁጥር ነው። በአንጻሩ x|0 ያልተተርጎመ ነው።
- ንሴት: x0 = x/x = 1, ይህ የማይሰራው x = 0 ሲሆን ብቻ ነው። በተጨማሪ ለማንኛው እውን ቁጥር x, 0x = 0.