1 ሻምሺ-አዳድ

ከውክፔዲያ
የሻምሺ-አዳድ መንግሥት በዘመኑ መጨረሻ

1 ሻምሺ-አዳድተርቃ ንጉሥ ኢላ-ካብካቡ ልጅ ነበረ። «የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» (MEC) የተባለው ሰነድ እንደሚለን፣ የሻምሺ-አዳድ ልደት ኢናያ (ወይም ዳዳያ) ሊሙ በሆነበት ዓመት፣ 1760 ዓክልበ. ሆነ ።[1] በኋላ በሻሩም-አዳድ ሊሙነት (1745 ዓክልበ.) «ሻምሺ-አዳድ ያባቱን ቤት ገባ» ማለት እድሜው 15 ዓመት ሲሆን የተርቃን ዙፋን ወረሰ።

የሻምሺ-አዳድ ስም በዚህ ዜና መዋዕል ብዙ ጊዜ ይጠቀሳል። በ1734 ዓክልበ. ኡኒናን አሸነፈ፤ ለሚከተሉት ዓመታት ግን ከስሙ በቀር ቃላቱ ጠፍቷል። ወደ አሦር ንጉሥ ናራም-ሲን ዘመን መጨረሻ በአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ ወደ «ካርዱንያሽ» (ባቢሎን) ወረደ። ይህ ማለት በዘመቻ ባቢሎንን ያዘ አይመስልም፤ ምናልባት ወደ ባቢሎን የሄደው በስደት ይሆናል። ሆኖም በ1723 ዓክልበ. ከባቢሎን ወጥቶ ኤካላቱምን እንደ ያዘ ይዘገባል። እዚያ ለ፫ ዓመታት ቆይቶ አሹርን ይዞ ንጉሡን 2 ኤሪሹምን አስወጥቶ የአሦርን መንግሥት ለራሱ ቃመው።

ከሻምሺ-አዳድ ዘመን በአሦር ጀምሮ የካሩም ንግድ በትንሹ እስያ ተመለሰ፤ በልጁም ዘመን እስከ 1678 ዓክልበ. ድረስ ተቀጠለ።

የዓመት ስሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሻምሺ-አዳድ መንግሥት በዘመኑ መጨረሻ (ሌላ አስተያየት)

የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።[2]

«የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» (MEC) የተባለው ሰነድ ለዚህ ዘመን የሊሙ ስምና ተጨማሪ የዓመት ድርጊቶች ይሰጣል።[3] ይህም በታች ይመለከታል።

1720 ዓክልበ. - አቢያ («አታማር-እሽታር») - «ሻምሺ-አዳድ (አሦርን ያዘ)።»
1719 ዓክልበ. - ኤዲኑም፣ በሉ-ራቢ ልጅ
1718 ዓክልበ. - አሹር-ታክላቱ
1717 ዓክልበ. - ኢሺም-ሲን
1716 ዓክልበ. - አዳድ-ባኒ
1715 ዓክልበ. - አቢ-ሻጊሽ
1714 ዓክልበ. - ጣብ-ጺሊ-አሹር
1713 ዓክልበ. - ኢዲን-አሹር
1712 ዓክልበ. - ናሚያ
1711 ዓክልበ. - አታል-ሻሪ፣ ኢሊ-አሉም ልጅ
1710 ዓክልበ. - ዳዳያ
1709 ዓክልበ. - አኒ-ማ[ሊክ]
1708 ዓክልበ. - ኢድና-አሹር - «ሻምሺ-አዳድ <...> ።»
1707 ዓክልበ. - አታኑም - «ሻምሺ-አዳድ ፲፪ ነገሥታትን አሸነፈ፤ የማሪ ንጉስ ያህዱን-ሊም፣ <...>፣ እኚህ ነገሥታት ተመልሰው <...> ።»
1706 ዓክልበ. - አሹር-ታክላቱ - «ሻምሺ-አዳድ <...> አሸነፈ።»
1705 ዓክልበ. - ሃያ-ማሊክ፣ ዱዳኑም ልጅ - («ሻምሺ-አዳድ ማሪን ያዘ ።»)
1704 ዓክልበ. - ሻሊም-አሹር፣ ሻሊም-አኑም ልጅ
1703 ዓክልበ. - ሻሊም-አሹር፣ ኡጽራኑ ልጅ
1702 ዓክልበ. - ኤናም-አሹር - «ሻምሺ-አዳድ <...> ምድር ያዘ ።»
1701 ዓክልበ. - ሲን-ሙባሊት - «ሻምሺ-አዳድ <...> ምድር ያዘ።»
1700 ዓክልበ. - ሪሽ-ሻማሽ - «1 እሽመ-ዳጋን <...> አሸነፈ።»
1699 ዓክልበ. - እብኒ-አዳድ፣ አሹር-ቱኩልቲ ልጅ - «ሻምሺ-አዳድ <...> ምድር ያዘ።»
1698 ዓክልበ. - አሹር-ኢሚቲ - «ሻምሺ-አዳድ <...> ምድርን አሸንፎ ያዘው፤ ዳዱሻ <...> ምድር፣ መቱራን ምድር፣ <...> ያዘ።»
1697 ዓክልበ. - አሂያያ፣ ታኪጊ ልጅ
1696 ዓክልበ. - ኢሊ-ኤላት፣ አሹር-ኒሹ ልጅ
1695 ዓክልበ. - ሪግማኑም - «ሙና-<...> (?)።»
1694 ዓክልበ. - ኢኩንፒያ፣ ሻሊም-አሹር ልጅ - «ሙና-<...> አሸነፈና ሻምሺ-አዳድ መቱራን ምድር ለዳዱሻ <...>።»
1693 ዓክልበ. - አስቁዱም - «ሻምሺ-አዳድ ቃብራን ያዘ ።»
1692 ዓክልበ. - አሹር-ማሊክ - «እሽመ-ዳጋን አሃዙምን አሸነፈ፤ ሻምሺ-አዳድ ኑሩጉምን ያዘ፤ እነኚህን ፱ ነገሥታት ማረከ፦ ኪብሩም፣ የ<...> ንጉሥ፣ <...> ያሹብ-አዳድ፣ የአሃዙም ንጉሥ፣ <...> ያሹብ-ሊም፣ የ<..> ንጉሥ፤ ለዳዱሻ እንደ ምርኮ ሰጣቸው።»
1691 ዓክልበ. - አዊሊያ - «ቱሩካውያን ጠላትነት ጀመሩ። ሻምሺ-አዳድና እሽመ-ዳጋን ቱሩካውያንንና <...>ን በቡሩላን አሸነፉዋቸው፤ ያስማህ-አዳድ ያሚናውያንን አሸንፎ የኤፍራጥስን ዳሮች አዋሀደ። ሙቱ-ቢሲር <...> በሳጋላቱም በር <...> አሸነፈ።»
1690 ዓክልበ. - ኒማር-ሲን፣ አሹር-ኒሹ ልጅ
1689 ዓክልበ. - አዳድ-ባኒ፣ ፑዙር-ኢሊ ልጅ
1688 ዓክልበ. - ጣብ-ጺሊ-አሹር

ከ1700 ዓክልበ. በፊት ትልቁን ልጅ እሽመ-ዳጋን በኤካላቱም ዙፋን ላይ አኖረው። በተጨማሪ በ1694 ዓክልበ. ታናሹን ልጅ ያስማህ-አዳድ በማሪ ዙፋን ላይ አኖረው።

ቀዳሚው
2 ኤሪሹም
አሹር ገዥ
1720-1688 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 እሽመ-ዳጋን
  1. ^ የሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል
  2. ^ የመስጴጦምያ ነገሥታት (ፈረንሳይኛ)
  3. ^ የሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል