C

ከውክፔዲያ
የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

C / cላቲን አልፋቤት ሦስተኛው ፊደል ነው።

ግብፅኛ
ቀመእ
ቅድመ ሴማዊ
ግመል
የፊንቄ ጽሕፈት
ግመል
የግሪክ ጽሕፈት
ጋማ
የጥንት ኤትሩስካዊ
C
ኋለኛ ኤትሩስካዊ
C
ጥንታዊ ላቲን
C
T14
Phoenician gimel Greek gamma Early Etruscan Classical Etruscan Roman C

የ«C» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ግመል» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የግመል ወይም የሚጣል ምርኩዝ ስዕል መስለ። ለምርኩዙም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት «ጋማ» (Γ γ) ደረሰ። የነዚህ ፊደላት ሁሉ ድምጽ «ግ» ነበረ። በኤትሩስክኛ ግን «ግ» የሚለው ድምጽ ስላልተለየ፣ ይህ ፊደል C እንደ K ለ«ክ» ይጠቅማቸው ነበር። የላቲን ሰዎች በፊደላቸው ደግሞ በመጀመርያ C እንደ «ግ» ወይም «ክ» ሊወክል ቻለ። በ230 ዓክልበ. ግድም አስተማሪው ስፑሪዩስ ካርቪሊዩስ ሩጋ የ«ክ» ከ«ግ» ድምጽ ለመለየት፣ «C» ትንሽ በመለውጥ አዲስ ፊደሉን «G» እንደ ፈጠረ ይባላል። ከዚህ ጀምሮ C ለ«ክ» ብቻ፣ G ለ«ግ» ብቻ ይበቃቸው ነበር።

ከዚህም በኋላ ከ500 ዓ.ም. ግድም ጀምሮ፣ «C» ከአናባቢዎቹ «E»፣ «I» ወይም «Y» ሲቀድም፣ በአሕዛብ ዘንድ እንደ «ስ» ይሰማ ጀመር። ስለዚህ ከሮማይስጥ በተወለዱት ቋንቋዎች እንደ ፈረንሳይኛ ወይም እስፓንኛ CE፣ CI እንደ «ሠ» «ሲ» ይሰማሉ፣ በእንግሊዝኛም ብዙ ጊዜ እንዲሁ ነው። በጣልኛም CE፣ CI እንደ «ቸ» «ቺ» ይሰማሉ። ሆኖም በነዚህ ልሳናት «C» ከ «A»፣ «O» ወይም «U» በፊት ሲቀድም፣ እንደ «ካ»፣ «ኮ»፣ «ኩ» ይሰማል።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ገ» («ገምል») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ግመል» ስለ መጣ፣ የላቲን 'C' ዘመድ ሊባል ይችላል።

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ C የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።