ሄርበርት ሁቨር

ከውክፔዲያ
ሄርበርት ሁቨር

ሄርበርት ሁቨር (1866 - 1957 ዓ.ም.) ከ1921 እስከ 1925 ዓ.ም. ድረስ 31ኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ነበሩ።

የሁቨር ቤተሠብ ከስዊስጀርመን ትውልድ ሲሆን ሃይማኖቱ የክዌከር ('የሚንቀጠቀጡ' ማለት ነው) ቤተ ክርስቲያን ነበረ። ወላጆቹ በልጅነቱ ጊዜ ካረፉ አንስቶ ድሃ አደግ ሆነና ከአጎቱ ጋር አደገ። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቴ መጀመርያ ክፍል በመሆኑ ትምህርቱ በነጻ ተቀበለ። ከዚያ በላይ የዩኒቬርሲቴው የቤስባልና የፉትቦል ቡድኖች አለቃ ሆነ። በ1887 ዓ.ም. የጂዮሎጂ ዲግሪ ይዘው ተመረቁ። ለ20 ዓመት የማዕደን ሊቅ ሲሆኑ እንኳን በአውስትራልያና በእንግሊዝ በማዕደን ዘርፍ የሠሩት ሥራ ስመ ጥሩ ሆነ።

መጀመርያው ታላቅ አለማዊ ጦርነት በ1906 ዓ.ም. በጀመረበት ወቅት ሁቨር ከራሳቸው ኪስ ለጋሥነት አውጥተው 120,000 አሜሪካውያን ቱሪስቶችና ሠራተኞችን ከአውሮፓ ወደ አገራቸው አስመለሷቸው። ከዚያ በጀርመኖች በተወረረው በቤልጅግ ውስጥ የኖሩት ረሃብተኞች ምግብ እንዲደርሳቸው ብዙ አደረጉ። በዚህ አይነት ሥራ በጦርነት ጊዜ የሁቨር ስም ጀግና እንዳለው ሁኔታ በመገኘት ላይ ሄዶ ነበር። ጦርነቱም ከተጨረሰ በኋላ ለምሥራቅ አውሮጳ ድሃ ሕዝብ እስከ ሩስያም ድረስ በረሃብ ላሉት ሰዎች ምግብ አደረሷቸው።

1913 በፕሬዝዳንት ዋረን ሃርዲንግ ዘመን ሁቨር የአሜሪካ የንግድ ሚኒስትር ሆኑ። በሃርዲንግ ተከታይ በፕሬዝዳንት ካልቪን ኩሊጅ ዘመን ደግሞ እንዲህ ያለን ማዕረግ ይዘው አገለገሉ። የንግድ ሚኒስትር እየሆኑ ሃይለኛ ሰው ነበሩ። የንግድ ዘርፍና መንግሥት አንድላይ ይሠሩ የሚለውን ተስፋ በመያዛቸው በዚህ አንጻር ብዙ አደረጉ። በማዶ ባሕርና በውጭ አገር ለባለጉዳዮች ምክርና እርዳታ የሚሰጡ መሥርያ ቤቶች በማስከፈቱ የአለም አቀፍ ንግድ በጉልበት አስለሙ። በተለይም የሆሊዉድ ፊልም ማዶ ባሕር ለመግፋፋት ጉጉ ነበሩ። ዜጎችም ቤት እንዲያገነቡና የራሳቸው መሬት ባለአባት እንዲሆኑ አበረታቷቸው።

ሁቨር ደግሞ የራዲዮ ስርጭት እንዲስተዳደር የራዲዮን ጉባኤ ጠሩ። እንዲሁም ለአውሮፕላኖች አስተዳደር ጉባኤ ጠርተው በብዙ አይነት ኢንዱስትሪ ለምሳሌ ኤሌክትሪክ፥ መስኖ ወዘተ ከፍተኛ ሚና ተጫወቱ። በገዛ ገንዘባቸው የልጆች ጤንነት በትምህርት ቤቶች አጸኑ።

1919 ዓ.ም. የሚሲሲፒ ወንዝ በሃይል ሲጎርፍ ታላቅ አስጊ ሁኔታ ፈጠረ። በወንዙ አጠገብ ያሉት 6 ክፍላገሮች ሁቨር የአደጋ ማስታገሻ ጥረት ሊቅ እንዲሆኑ ጠየቁት። ስለዚህ ፕሬዝዳንት ኩሊጅ ላኳቸውና ቡድናቸው ብዙ ተስቦ እንደ ወባ በሽታ አስቆመ። በ1920 ዓ.ም. የዓለሙ መጀመርያው ቴሌቪዥን ስርጭት ፈተና ሲደረግ መጀመርያው ትርዒት የሁቨር ቃል ንግግር ነበረ።

ኩሊጅ ለሁለተኛ ዘመን ለማገልገል እምቢ ብለው በ1921 የፕሬዚዳንት ምርጫ ጊዜ ሁቨር የሬፑብሊካን ወገን ዕጩ ሆኑ። በተቃራኒው በዴሞክራት ወገን እጩ በአል ስሚስ ላይ በሰፊ መጠን አሸነፉ።

ስለ ድሃነት፦ «እኛ በአሜሪካ ዛሬ ከማንም አገር ታሪክ ይልቅ በድሃነት ላይ በመጨረሻ ድል ልናደርግ ነው» ብለው ነበር።

ከዚህ ከጥቂት ወራት በኋላ የ1921 ዓ.ም. የእስቶክ ገበያ ውድቀት በመከሠቱ የአገሩ እንዲሁም የመላ አለም ምጣኔ ሀብት ወደ 'ታላቁ ጭፍግግ' በ1 አመት ውስጥ ቶሎ ወረደ። ባንኮችና ፌዴራላዊ መንግሥት ያስገኙ የገንዘብ መጠን ወደ አንድ ሢሶ ተቀነሰ።

ስለ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የክላርክ ሰነድ1920 ተጽፎ ሁቨር ፕሬዝዳንት እየሆኑ በ1922 ግልጽ ሆኖ ወጣ። በዚህ ሰነድ ዘንድ፥ አውሮጳ በላቲን አሜሪካ ላይ ዛቻ ካልጣለች በተቀር አሜሪካ በውጭ አገር ጥልቅ ለማለት ሕጋዊ መብት አልነበራትም የሚል ማስታወሻ ነበር። በዚያን ጊዜ አሜሪካ ሠራዊት በኒካራጓና በሃይቲ ነበራት። ስለዚህ ሁቨር ከነዚህ አገራት የሠራዊቱን ቁጥር ቀነሱ። በላቲን አሜሪካ ውስጥ የጦርነት መሣርያ እንዳይደርስ ማዕቀብ ለመጣል አሠቡ። በ1924 ጃፓን ማንቹርያን በወረረ ጊዜ አዲስ ፖሊሲ አወጡ። እሱም በግፍና በወረራ የሚገኝ የመሬት ለውጥ ሁሉ አናከብርም የሚል ነበር።

ከታላቁ ጭፍግግ የተነሣ ብዙ ባንክ ቤቶች ስለወደቁ አንዳችም ብድር ለማግኘት ከባድ ሆነ። ብዙ ሰዎች ሥራ ፈት ሆኑ። በአውሮፓም ምጣኔ ሃብቱ ችግር ውስጥ ስለ ገባ ሁቨር ጀርመን ስለመጀመርያው ጦርነት ለፈረንሳይ ከምትከፍል ካሣ ለአንድ አመት ይቅር ትበል የሚል ዕቅድ አዋጁ። በሚከተለውም አመት የጀርመን ዕዳ በሙሉ ተሰረዘ።

ሥራ ፈትነት ለመቀነስ፥ ከ1 እስከ 2 ሚሊዮን ድሃ ሰዎች ወደ ሜክሲኮ አስመለሱ። ሆኖም ከነዚህ መካከል 60 ከመቶ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሜክሲካዊ-አሜሪካውያን ነበሩ። ደግሞ በተራ ዜጎች ላይ ቀረጥና ግብር በያይነቱ እጅግ ከፍ አደረጉባቸው። በዘመናቸው መጨረሻ በ1925 ዓ.ም. 25 ከመቶ አካለ መጠን ከደረሱት ሰዎች ሥራ ፈት ሆነው ነበር።

1924 ዓ.ም. የፕሬዚዳንት ምርጫ እንደገና ሲቀርብ፥ 20 ሺህ በመጀመርያው አለማዊ ጦርነት ልምድ ያላቸው የድሮ ወታደሮች ከነቤተሰቦቻቸው በዋና ከተማው በዋሺንግቶን ዲሲ ሠፈሩ። እነሱ ጡረታቸውን እንዲያገኙ ፈልገው ነበር። ይህም ስብሰባ 'የጡረታ ሰልፍ' ተባለ። ከፖሊሶች ጋራ ከታገሉ በኋላ ፌዴራል ሠራዊት ገቡና ጡረተኞቹን በግድ በሳንጃና በእንባ አውጭ ጋዝ አስወጡአቸው። ብዙ ሰዎች ተገደሉ ብዙም መቶ ተቆሰሉ።

በዚህ ሁሉ ምክንያት ሁቨር የተወደዱ ፕሬዚዳንት አልነበሩም። በ1925 ምርጫ ተቃራኒው ፍራንክሊን ሮዘቨልት በሰፊ መጠን አሸነፉና በሳቸው ፈንታ ፕሬዚዳንት ሆኑ።

ሁቨር ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ረጀም ዕድሜ ነበራቸው። እስከ 1957 ዓ.ም. ድረስ ኖሩ። ከ2ኛ አለማዊ ጦርነት ቀጥሎ በ1939 ስለ ቀድሞው ልምዳቸው ፕሬዚዳንት ሃሪ ትሩማን የአውሮፓ ምግብ ፍላጎት ለመወሰን ወደ አውሮፓ ላኳቸው።