ታላቁ አልፍሬድ

ከውክፔዲያ
የታላቁ አልፍሬድ ሐውልት በዊንቼስትር፣ እንግሊዝ

ታላቁ አልፍሬድ (ጥንታዊ እንግሊዝኛ፦ Ælfrēd፤ 840-892 ዓ.ም. ገደማ የኖሩ) ከ863 ዓ.ም. እስከ 892 ዓ.ም. ድረስ የዌሴክስ ንጉሥ ነበሩ። እርሳቸው መጀመርያ 'የንግሊዞች ንጉሥ' ተባሉ። 'ታላቁ' የተባሉት አገራቸውን ከዴንማርክ ከመጡት ወራሪዎችና ቫይኪንጎች ስለ ተከላከሉ ነው።

ከዚህ በላይ የእንግሊዝ ንጉሥ አልፍሬድ ክርስቲያንና ዕጅግ የተማሩ ሊቅ ሲሆኑ አያሌው መጻሕፍት ከሮማይስጥ ወደ እንግሊዝኛ አስተረጎሙ፣ እንዲሁም የአገራቸውን ሕገ መንግሥት አሻሻሉ። ይህም ሕገ መንግሥት ወይም ዶም ቦክ በመጀመርያ ክፍሎቹ ከአስርቱ ቃላትና ከሕገ ሙሴ (ከኦሪት ዘጸአት 21 & 22) ተመሠረተ። ዋና ከተማቸው ዊንቼስትር፣ እንግሊዝ ነበረ።

ጥቅስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

«Ond for ðon ic ðē bebīode ðæt ðū dō swǣ ic gelīefe ðæt ðū wille, ðæt ðū ðē ðissa woruldðinga tō ðǣm geǣmetige; swǣ ðū oftost mæge, ðæt ðū ðone wīsdōm ðe ðē God sealde ðǣr ðǣr ðū hiene befæstan mæge, befæste. Geðenc hwelc wītu ūs ðā becōmon for ðisse worulde, ðā ðā wē hit nōhwæðer nē selfe ne lufodon, nē ēac ōðrum monnum ne lēfdon: ðone naman ānne wē lufodon ðætte wē Crīstne wǣren, ond swīðe fēawe ðā ðēawas.»

«ስለዚህ ልታደርጉት ፈቃደኛ መሆናችሁን እንደማመን ለማድረግ አዝዛችኋለሁ፣ እንደምትችሉበት ጊዜ ራሳችሁን ከዓለማዊ ነገሮች እንድትፈቱና እግዚአብሔር የሰጣችሁን ጥበብ ለማቆም በምትችሉበት እንድታቆሙት ነው። እኛ ራሳችን (ጥበብን) ምንም ሳንወድደው ወይም ለሌሎች ሰዎች ሳናወርሰው በዚሁ ዓለም ምን ያሕል መቅሠፍት እንደ ደረሰብን አስቡበት፤ ክርስቲያኖች እንደ ነበርን ስሙን ብቻ ወደድንና ዕጅግ ጥቂቶች ልማዶቹን።» -- ኩራ ፓስቶራሊስ (እረኛዊ እንቅብቃቤ) መቅድም