ከ«ኡር-ናንሼ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''ኡር-ናንሼ''' ከ2309 እስከ 2279 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ መጀመርያ ንጉሥ ነበር። ቀ...»
(No difference)

እትም በ03:11, 23 ሴፕቴምበር 2011

ኡር-ናንሼ ከ2309 እስከ 2279 ዓክልበ. ድረስ ግድም የሱመር ከተማ ላጋሽ መጀመርያ ንጉሥ ነበር። ቀዳሚው ሉጋል-ሻግ-ኤንጉር ንጉሥ ሳይሆን አለቃ ወይም ከንቲባ ነበር፤ ለመሲሊም ተገዥ ነበር። ከመሲሊም ዘመን በኋላ ላጋሽ ነጻ ወጣ። ኡር-ናንሼ የጉኒዱ ልጅ ነበር። በዘመኑ ግድግዳዎች፣ ቤተ መቅደሶችና መስኖዎች እንደ ተሠሩ ይመዘገባል። ከድልሙን ጋር ንግድ ያካሄድ ነበር። የላጋሽ ጎረቤት ኡማ በዚህ ዘመን ነጻነቱን አግኝቶ ንጉሡ ኡር-ሉማ ላጋሽን ተዋጋ፤ ግን አልተከናወነም። የኡር-ናንሼ ልጅ አኩርጋል ተከተለው።