ከ«ፐሽቶ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
ሎሌ መጨመር: pa:ਪਸ਼ਤੋ
r2.7.3) (Robot: Modifying da:Pashto to da:Pashto (sprog)
መስመር፡ 113፦ መስመር፡ 113፦
[[cv:Пушту]]
[[cv:Пушту]]
[[cy:Pashto]]
[[cy:Pashto]]
[[da:Pashto]]
[[da:Pashto (sprog)]]
[[de:Paschtunische Sprache]]
[[de:Paschtunische Sprache]]
[[diq:Peştuki]]
[[diq:Peştuki]]

እትም በ22:34, 26 ኦክቶበር 2012

ፕሽቶ (پښتو) በአፍጋኒስታን በምዕራብ ፓኪስታን እንዲሁም በስሜን ሕንድ አገሮች በሚኖሩት በፓሽቱን ሕዝብ የሚናገር ቋንቋ ነው።

የኢራናውያን ቋንቋዎች ስርጭት - ፐሽቶ የሚገኝ አፍጋኒስታንና ፓኪስታን ባለው ሐምራዊ ክፍል ነው።

1928 ዓ.ም. ጀምሮ ፐሽቶ ከዳሪ ፋርስኛ ጋራ ከአፍጋኒስታን ሁለት ይፋዊ መደበኛ ቋንቋ አንድ ነው። ከአፍጋኒስታን ኗሪዎች በ35 ከመቶ ወይም 22 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንደሚናገር ይገመታል።

ፐሽቶ ከአረብኛና ከቱርክኛ አያሌው ቃሎች ተበድሮዋል። በእስጅንደር ዘመን (ክ.በ. 330) ግሪኮች ይህን አገር ደረሱና አንዳንድ ሊቃውንት ከጥንታዊ ግሪክ ደግሞ የወረዱ ቃላት አሉ ብለው ይገመታሉ። በፓኪስታን ደግሞ ፐሽቶ የሚናገሩ 11-14 ከመቶ ወይም 13 ሚሊዮን ሰዎች ፐሽቶ እንደሚችሉ ይታመናል። በጠቅላላ 40-50 ሚሊዮን ያሕል ፐሽቶ ተናጋሪዎች አሉ።

ፕሽቶ በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ውስጥ ሲካተት በዚያ ላይ በኢራናውያን ቋንቋዎች ዘርፍ ውስጥ ይደመራል።

ስዋሰው

ፐሽቶ እንደ አማርኛ ግሡ በዕረፍተ ነገሩ መጨረሻ የሚሳክበት ቋንቋ ነው። ቅጽል ከስሙ ይቀድማል። ስምና ቅጽል የተባይና የአንስታይ ጾታዎች፥ ነጠላና ብዙ ቁጥር፥ ሳቢና ተሳቢ አይነቶች አሉዋቸው። መስተጻምር የለም።

ጽሕፈት

እስልምና ከተነሣ ጀምሮ ፐሽቶ የሚጻፍበት በአረብኛ ጽሕፈት አይነት ሆኗል. አንዳንድ ልዩ ድምጾች ስልላሉት ግን ተጨማሪ ምልክቶች ይኖራሉ። ፊደሉን በሙሉ ለመመልከት ወዲኅ ይሂዱ።

ምሳሌዎች

  • ማክታብ ታ ድዛ! (ወይም) ማክታብ ታ ላር ሻ!
  • (ትምህርት ቤት ጋ ሂድ!)


  • ማክታብ ታ ላር ሸይ!
  • (ትምህርት ቤት ጋ ሂዱ!)


  • ዙህ ማክታብ ታ ድዙም።
  • (እኔ ትምህርት ቤጥ ጋ እሄዳለሁ።)


  • ዙህ ግሗሩም ቼ ማክታብ ታ ላር ሹም።
  • (እኔ ትምህርት ቤት ጋ መሔድ እፍልጋለሁ።)


  • ዙህ ማክታብ ታ ትሊላይ ዩም።
  • (እኔ ትምህርት ቤት ጋ ሂጃለሁ።)


  • ዙህ ማክታብ ታ ዎላሩም።
  • (እኔ ትምህርት ቤት ጋ ሄድኩ።)


  • ዙህ ማክታብ ታ ትሊላይ ዉም።
  • (እኔ ትምህርት ቤት ጋ ሂጄ ነበር።)


  • ዙህ ማክታብ ታ ትሊሉም።
  • (እኔ ትምህርት ቤት ጋ እሔድ ነበር።)


  • ፓኒር ዎክሑራ!
  • (አይብ ብላ!)


  • ፓኒር ሙህክሑራ!
  • (አይብ አትብላ!)


  • ፓኒር ሙህክሑረይ!
  • (አይብ አትብሉ!)


  • ዙህ ፓኒር ክሑሩም።
  • (እኔ አይብ እበላለሁ።)


  • ዙህ ግሗሩም ቼ ፓኒር ዎክሑሩም።
  • (እኔ አይብ ለመብላት እፈልጋልሁ።)


  • ما پنېر خوړلی دی
  • ማ ፓኒር ክሗሪላይ ዳይ።
  • (እኔ አይብ በልቻለሁ።)


  • ማ ፓኒር ዎክሖሮ።
  • (እኔ አይብ በላሁ።)


  • ማ ፓኒር ክሗሪላይ ዎ።
  • (እኔ አይብ በልቼ ነበር።)


  • ማ ፓኒር ክሗሩህ።
  • (እኔ አይብ እበላ ነበር።)

የውጭ መያያዣዎች

Wikipedia
Wikipedia