ከ«ማልዲቭስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Jump to navigation Jump to search
2,416 bytes added ፣ ከ7 ዓመታት በፊት
no edit summary
(ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 2 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q826 ስላሉ ተዛውረዋል።)
'''ማልዲቭስ''' በ[[ሕንድ ውቅያኖስ]] የተገኘ የደሴቶች አገር ሲሆን ዋና ከተማው [[ማሌ]] ነው። ለ[[ሕንድ]]ና [[ስሪ ላንካ]] አገራት ይቀርባል። 400 ሺህ ያሕል ኗሪዎች አሉት።
 
የማልዲቭ ሕዝብ መጀመርያ ከሰሜናዊ ሕንድ ደረሱ፣ ቋንቋቸው [[ዲቬሂኛ]] ይባላል። ይህ [[የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋ]] ስለሆነ በውኑ የ[[እንግሊዝኛ]] ዘመድ ነው። እንደ [[አረብኛ ፊደል]] በሚመስል ልዩ ጽሕፈት ይጻፋል።
 
በማልዲቭዝ ለሚኖሩ ሰዎች ከ[[እስልምና]] በቀር ሌላ አምልኮት አይፈቀድም። የደሴቶቹ ሕዝብ አስቀድሞ [[የሕንድ ሃይማኖት]] ተከታዮች ሲሆኑ ከዚያ ለጊዜ የ[[ቡዲስም]] አማኞች ሆኑ። በመጨረሻ በ[[1145]] ዓ.ም. እስላሞች ሆኑ።
 
ከ[[1879]] ዓ.ም. ጀምሮ ሡልጣናቸው በ[[ብሪታንያ]] ጥብቅና ሥር ይቆይ ነበር። በ[[1957]] ዓ.ም. ከብሪታንያ ነጻ ሆነ፣ በ1960 ዓ.ም. [[ሪፐብሊክ]] ሆነ። በ[[1980ዎቹ]] 3 መንፈቅለ መንግሥት ሙከራዎች ቢሆኑም አልተከናወኑም። በ[[1996]] ዓ.ም. ከታላቅ [[የምድር መንቀጥቀጥ]] በኋላ አንድ ትላቅ ጐርፍ በማዲቭስ ደሴቶች ላይ ብዙ ጉዳት አደረገ። የዓለም ውቅያኖሶች መጠን በ[[ዓለማዊ መሞቅ]] ከፍ ከፍ እያለ፥ ምናልባት በመቶ አመት ውስጥ ማልዲቭስ ምንም ኗሪዎች የማይኖሩባቸው ደሴቶች እንዳይሆኑ የዕውነት ተግሳጽ አለ። ስለዚህ ነው ከዓለም አገራት ማልዲቭስ የ[[ካርቦን]] ማገዶነት ለመከልከል መጀመርያው አገር የሆነው።
 
ከ1964 ዓም ጀምሮ [[ቱሪስም]] የሀገሩ ምጣኔ ሀብት ዋና ዓምድ ሆኖ በየዓመቱ 500 ሺህ ቱሪስቶች ይጎበኛሉ። ከደሴቶቹ አንዳንድ በተለየ ለሆቴል ብቻ ተለይተዋል። እንዲሁ ሲሆን ቱሪስቶቹ የማልዲቭስ ኗሪ ዜጎች በመኖርያዎቻቸው ላይ ከቶ አይደርሱም።
 
በርካታ የ[[ሙዚቃ]] አይነቶች ከማዲቭስ ይገኛሉ፣ ከነርሱም ውስጥ [[ቦዱቤራ]] እና [[ጣራ]] የተባሉ ሙዚቃ አይነቶች አሉ። ከነዚህም ጋር የተለመዱ ጭፍራዎች ይሄዳሉ።
 
{{መዋቅር}}
Anonymous user

Navigation menu