ከ«ኡሰርካሬ ኸንጀር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{የንጉሥ መረጃ | ስም =ኡሰርካሬ ኸንጀር | ርዕስ = የግብጽ ፈርዖን | ስዕል=Khendjer 1.jpg...»
(No difference)

እትም በ16:43, 7 ጁን 2014

ኡሰርካሬ ኸንጀር
በኸንጀር ሀረም ውስጥ የተገኘው የኸንጀር ሀረም ምስል
በኸንጀር ሀረም ውስጥ የተገኘው የኸንጀር ሀረም ምስል
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1772-1760 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ኹታዊሬ ወጋፍ
ተከታይ ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው
ባለቤት ሰነብኸናስ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ኡሰርካሬ ኸንጀር ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1772 እስከ 1760 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። ምናልባት የኹታዊሬ ወጋፍ ተከታይ ነበረ።

ቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ «ኡሰር<..>ሬ <...>ጀር» ይገኛል። በመምኅር ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ «ኸንጀር» የሚለው ስያሜ ግብጽኛ ሳይሆን በአንዳንድ ሴማዊ ቋንቋዎች «እሪያ» ማለት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሴማዊው ፲፬ኛው ሥርወ መንግሥት በጌሤም እየገዛ ምናልባት የሴማውያን ተጽእኖ በጤቤስ መንግሥት ደግሞ በዚህ ሊታይ ይችላል።

ኸንጀር በተለይ ስላሠራው «የኸንጀር ሀረም» ይታወቃል። በዚህ ሀረም በሁለት ድንጋዮች የኸንጀር ፩ኛው ዓመትና የ፭ኛው ዓመት ዘመነ መንግሥት ተመዘገበ። ስለዚህ ብዙ ሊቃውንት ከ፭ ዓመታት በላይ እንደ ገዛ አያምኑም።

በዚህ ዘመን «ኦሩስ፣ አኸንኸሬስ፣ አኮሪስ፣ ኸንክሬስ፣ አኸሬስ» በግብጽ እንደ ገዙ በአንዳንድ ምንጭ ይገኛል። እነዚህ ስሞች ሆር አዊብሬሰኸምሬኹታዊ ኻውባውሰጀፋካሬ፣ ኸንጀር፣ እና ስመንኽካሬ ቢመስሉም፣ ከማኔጦን ጀምሮ ስሞቻቸው ከ፲፱ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች ጋር እንደ ተዛቡ ይመስላል። «ኸንክሬስ» የ፲፪ ዓመታት ዘመን እንደ ነበረው ይባላል። በአንዳንድ የድሮ ምንጭ ደግሞ «ኸንክሬስ» በዘጸአት ዘመን የጠፋው ፈርዖን ሲባል ይህ ደግሞ እንደ ተዛበ ይመስላል።

ቀዳሚው
ኹታዊሬ ወጋፍ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1772-1760 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ስመንኽካሬ ኢሚረመሻው

ዋቢ ምንጭ

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)