ከ«የማቴዎስ ወንጌል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Jump to navigation Jump to search
5,895 bytes added ፣ ከ3 ዓመታት በፊት
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
35፤ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡ወንድሙን፡ከልቡ፡ይቅር፡ካላለ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡የሰማዩ፡አባቴ፡ያደርግባችዃል።
== '''ምዕራፍ ፲፱''' ==
1፤ኢየሱስም፡ይህን፡ነገር፡ከፈጸመ፡በዃላ፥ከገሊላ፡ኼዶ፡ወደይሁዳ፡አውራጃ፡ወደዮርዳኖስ፡ማዶ፡መጣ።
2፤ብዙ፡ሕዝብም፡ተከተሉት፥በዚያም፡ፈወሳቸው።
3፤ፈሪሳውያንም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡና፡ሲፈትኑት፦ሰው፡በኾነው፡ምክንያት፡ዅሉ፡ሚስቱን፡ሊፈታ፡
ተፈቅዶለታልን፧አሉት።
4፤ርሱ፡ግን፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ፈጣሪ፡በመዠመሪያ፡ወንድና፡ሴት፡አደረጋቸው፥
5፤አለም፦ስለዚህ፡ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥ከሚስቱም፡ጋራ፡ይተባበራል፥ኹለቱም፡አንድ፡ሥጋ፡
ይኾናሉ፡የሚለውን፡ቃል፡አላነበባችኹምን፧
6፤ስለዚህ፥አንድ፡ሥጋ፡ናቸው፡እንጂ፡ወደ፡ፊት፡ኹለት፡አይደሉም።እግዚአብሔር፡ያጣመረውን፡
እንግዲህ፡ሰው፡አይለየው።
7፤እነርሱም፦እንኪያስ፡ሙሴ፡የፍቿን፡ጽሕፈት፡ሰጥተው፡እንዲፈቷት፡ስለ፡ምን፡አዘዘ፧አሉት።
8፤ርሱም፦ሙሴስ፡ስለልባችኹ፡ጥንካሬ፡ሚስቶቻችኹን፡ትፈቱ፡ዘንድ፡ፈቀደላችኹ፤ከጥንት፡ግን፡እንዲህ፡
አልነበረም።
9፤እኔ፡ግን፡እላችዃለኹ፥ያለዝሙት፡ምክንያት፡ሚስቱን፡ፈቶ፟፡ሌላዪቱን፡የሚያገባ፡ዅሉ፡
ያመነዝራል፥የተፈታችውንም፡የሚያገባ፡ያመነዝራል፡አላቸው።
10፤ደቀ፡መዛሙርቱም፦የባልና፡የሚስት፡ሥርዐት፡እንዲህ፡ከኾነ፡መጋባት፡አይጠቅምም፡አሉት።
11፤ርሱ፡ግን፦ይህ፡ነገር፡ለተሰጣቸው፡ነው፡እንጂ፡ለዅሉ፡አይደለም፤
12፤በእናት፡ማሕፀን፡ጃን፡ደረባዎች፡ኾነው፡የተወለዱ፡አሉ፥ሰውም፡የሰለባቸው፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፥ስለ፡
መንግሥተ፡ሰማያትም፡ራሳቸውን፡የሰለቡ፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፦ሊቀበለው፡የሚችል፡ይቀበለው፡አላቸው።
13፤በዚያን፡ጊዜ፡እጁን፡እንዲጭንባቸውና፡እንዲጸልይ፡ሕፃናትን፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡
ገሠጿቸው።
14፤ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፦ሕፃናትን፡ተዉአቸው፥ወደ፡እኔም፡ይመጡ፡ዘንድ፡አትከልክሏቸው፤መንግሥተ፡
ሰማያት፡እንደነዚህ፡ላሉ፡ናትና፥አለ፤
15፤እጁንም፡ጫነባቸውና፡ከዚያ፡ኼደ።
16፤እንሆም፥አንድ፡ሰው፡ቀርቦ፦መምህር፡ሆይ፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡እንዳገኝ፡ምን፡መልካም፡ነገር፡
ላድርግ፧አለው።
17፤ርሱም፦ስለ፡መልካም፡ነገር፡ለምን፡ትጠይቀኛለኽ፧መልካም፡የኾነ፡አንድ፡ነው፤ወደ፡ሕይወት፡
መግባት፡ብትወድ፡ግን፡ትእዛዛትን፡ጠብቅ፡አለው።
18፤ርሱም፦የትኛዎችን፧አለው።ኢየሱስም፦አትግደል፥አታመንዝር፥አትስረቅ፥በሐሰት፡አትመስክር፥
19፤አባትኽንና፡እናትኽን፡አክብር፥ባልንጀራኽንም፡እንደ፡ራስኽ፡ውደድ፡አለው።
20፤ጐበዙም፦ይህንማ፡ዅሉ፡ከሕፃንነቴ፡ዠምሬ፡ጠብቄያለኹ፥ደግሞስ፡የሚጐድለኝ፡ምንድር፡
ነው፧አለው።
21፤ኢየሱስም፦ፍጹም፡ልትኾን፡ብትወድ፥ኺድና፡ያለኽን፡ሸጠኽ፡ለድኻዎች፡ስጥ፥መዝገብም፡በሰማያት፡
ታገኛለኽ፥መጥተኽም፡ተከተለኝ፡አለው።
22፤ጐበዙም፡ይህን፡ቃል፡በሰማ፡ጊዜ፡ብዙ፡ንብረት፡ነበረውና፡እያዘነ፡ኼደ።
23፤ኢየሱስም፡ለደቀ፡መዛሙርቱ፦እውነት፡እላችዃለኹ፥ለባለጠጋ፡ወደ፡መንግሥተ፡ሰማያት፡መግባት፡
ጭንቅ፡ነው።
24፤ዳግመኛም፡እላችዃለኹ፥ባለጠጋ፡ወደእግዚአብሔር፡መንግሥት፡ከሚገባ፡ግመል፡በመርፌ፡ቀዳዳ፡ቢገባ፡ይቀላል፡አለ።
25፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ሰምተው፡እጅግ፡ተገረሙና፦እንኪያስ፡ማን፡ሊድን፡ይችላል፧አሉ።
26፤ኢየሱስም፡እነርሱን፡ተመልክቶ፦ይህ፡በሰው፡ዘንድ፡አይቻልም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ግን፡ዅሉ፡
ይቻላል፡አላቸው።
27፤በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡መልሶ፦እንሆ፥እኛ፡ዅሉን፡ትተን፡ተከተልንኽ፤እንኪያስ፡ምን፡እናገኝ፡
ይኾን፧አለው።
28፤ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦እውነት፡እላችዃለኹ፥እናንተስ፡የተከተላችኹኝ፥በዳግመኛ፡ልደት፡የሰው፡ልጅ፡በክብሩ፡ዙፋን፡በሚቀመጥበት፡ጊዜ፥እናንተ፡ደግሞ፡በዐሥራ፡ኹለቱ፡የእስራኤል፡ነገድ፡
ስትፈርዱ፡በዐሥራ፡ኹለት፡ዙፋን፡ትቀመጣላችኹ።
29፤ስለ፡ስሜም፡ቤቶችን፡ወይም፡ወንድሞችን፡ወይም፡እኅቶችን፡ወይም፡አባትን፡ወይም፡እናትን፡ወይም፡
ሚስትን፡ወይም፡ልጆችን፡ወይም፡ዕርሻን፡የተወ፡ዅሉ፡መቶ፡ዕጥፍ፡ይቀበላል፡የዘለዓለምንም፡ሕይወት፡
ይወርሳል።
30፤ነገር፡ግን፥ብዙዎቹ፡ፊተኛዎች፡ዃለኛዎች፥ዃለኛዎችም፡ፊተኛዎች፡ይኾናሉ።
== '''ምዕራፍ ፳''' ==
 
 
 

Navigation menu