ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Jump to navigation Jump to search
22 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
፲፯. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ኣደረግን የሚሉትን ኣንድኣንድ ዋሾዎች ከኣሳጧቸው መካከል የግዕዝ ኣልቦ ኣለመኖሯቸው ኣንዱ ነው። ምክንያቱም በታይፕራይተር ኣጠቃቀም ሥራ ላይ ማዋል የሚቻለው የላቲኑን ኣኃዞች ብቻ ስለሆነ የዶክተሩን የኣልቦ ኣኃዝ ኣስተሳሰብ ኣልደገፉም። ፲፰. በነገራችን ላይ የመጀመሪያዎቹ የላቲን ካፒታል ቀለሞች የግዕዙን ኣኃዞች የመሰሉት ኣንድኣንዶቹ ቀንና ደራሲ በሌለው ጽሑፍ ሊያሳምኑን በመፈለግ ምንጩ የግሪክ ሳይሆን ኣይቀርም እንደሚሉት ሳይሆን [https://www.geez.org/Numerals/] ገልባጮቹ ግሪኮች ሳይሆኑ እንዳልቀረ መረጃ ኣለ። እዚሁ ጽሑፍ ውስጥ መጨረሻ ላይ መቀየሪያ ተብለው የቀረቡ ኣሉ። ሥራው ጥሩ ሆኖ ሳለ የቀረበው የኣረብኛን የኮምፕዩተር ቍጥሮች ወደ ግዕዝና ግዕዙን ወደ ኣረብኛው ያስቀይራል ተብሎ ነው። ዩኒኮድ ውስጥ የኣሉት የግዕዝ ቍጥሮች ፊደል እንጂ በኮምፕዩተር ወግና ኣሠራር ቍጥሮች ስለኣልሆኑ ለኮምፕዩተር ሂሳብ ሥራ የተዘጋጀ ኣለመሆኑ መታወቅ ኣለበት። ኣሁን በኣለው ወግና ኣሠራር ኮምፕዩተር በግዕዝ ኣኃዞች እንዲጠቀም ዶክተሩ ከብዙ ዓመታት በፊት የፈጠሩት የተሻለና ዘለቄታ የኣለው ዘዴ ነው። ፲፱. ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ከተደረገ በኋላ ለትላልቆቹ ኣኋዞች የተለያዩ ቀለሞች መፍጠር የሞከሩ ኣሉ። ምሳሌ [http://www.goolgule.com/what-scholars-say-about-our-alphabet/] ። ቍጥሮችን ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ በኣሉ ቀለሞች መጠቀም ሳይንሳዊ ነው። ስለዚህ ኣዲስ ኣሥር የግዕዝ ኣኋዞችን መፍጠርን ዶክተሩ ኣያበረታቱም። [http://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2013/09/Geez-Amharic-Letters.pdf] በእዚህ ኣጋጣሚ ዶክተሩ ማሳሰብ የሚፈልጉት ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች ከሌሎች የኣገኙትን ዋቢ ኣድርጎ የማቅረብ ጥቅምና ኣስፈላጊነት መገንዘብ ነው። ዋቢ የሌለውን ጽሑፍ በዋቢነት መጠቀም ኣስቸጋሪ ነው። ፳. ኣልቦን ጨምሮ የእንግሊዝኛውን የኣኃዞች ኣጠቃቀም በተለይም ኣኃዞች በቃላት ሲገለጹ ጠንቅቆ ማወቅ ለትርጕም ጠቃሚ ነው። [https://www.aresearchguide.com/writing-out-numbers-in-words.html]
 
፳፩. በዓማርኛ የጽሕፈት ሥርዓት ውስጥ የሒሳብ ምልክቶች ኣለመገኘታቸው ችግር ነው የሚሉ ኣሉ። [https://selam251.wordpress.com/2014/12/07/%e1%8b%a8%e1%8d%8a%e1%8b%b0%e1%88%8d-%e1%8a%90%e1%8c%88%e1%88%ad/] ከሒሳብ ምልክቶቹ ይልቅ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ምልክት ኣለመኖር ነበር ችግሩ። ምንም እንኳ የዜሮ ምልክት በቊጥሩ ስርዓት ውስጥ ባይኖርም፣ የዜሮ ጽንሰ ሐሳብ ግን ለብዙ መቶ ዓመታት አልቦ በሚለው ቃል ውስጥ ተካቶ እናያለን፣ በተለይ የማካፈል ስሌት ውጤቶች ውስጥ። [https://andemta.com/2017/08/06/%e1%8b%98%e1%88%98%e1%8a%95-%e1%89%8a%e1%8c%a5%e1%88%ad%e1%8a%93-%e1%88%b5%e1%88%8c%e1%89%b5/] ፳፪. የዶክተሩ ኣሥር ኣዳዲስ የግዕዝ ቍጥራዊ (Numeric) ኣኃዞች ከኣንድ እስከ ዘጠኝ ከኣሉት የዩኒኮድ መደብ ውስጥ የገቡት ዘጠኙ ጥንታዊ ፊደላዊ (Alpahbetic) ኣኃዞች እንዲለዩ በቅርቡ ዶክተሩ መቀመጫዎቻቸውን ኣንስተዋል። ይህ ከግዕዝ ቀለሞች ጠባይም ጋር የሚሄድ ነው። ምክንያቱም ቍጥራዊና ፊደላዊ ኣኃዞች ቅርጾች መጋራት ስለሌለባቸውም ነው። ኣልቦው ጥቅም ላይ እንዲውል ዶክተሩ ከ"1" እስከ "9" ተጨማሪም ኣኃዞች በመጨመር የግዕዝን ቍጥሮች ብዛት ከ፳ ወደ ፴ ከፍ ቢያደርጉም ኣሥሮቹን በቊጥርኝት በመቀጠል አንድንጠቀም ኣድርገዋቸዋል። ዶክተሩ ከዩኒኮድ በፊት የፈጠሩት የኣልቦ ቍጥራዊ ኣኃዝ መቀመጫ የኣለው ቀለም ሲሆን ከዩኒኮድ በኋላ በቅርቡ የጨመሯቸው ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ የኣሉት መቀመጫ የሌላቸው ኣዳዲስ ኣሥር ቍጥራዊ ኣኃዛት ናቸው። ስለዚህ የዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዞች ሁለት ዓይነቶች ናቸው። ሕዝቡ በኣማራጭነት እንዲጠቀምበት የሚፈልጉትም በኣዲሶቹ ኣሥሮቹ ቊጥራዊ ኣኃዞች ነው። እነዚህ ግኝቶችና ኣጠቃቀሞቻቸው በፓተንት ማመልከቻቸውም ተጠቅሰዋል። ዶ/ሩ GeezEdit Amharic P ፊደል ውስጥ የኣቀረቡት የግዕዝ ኣልቦ ዩኒኮዱ ውስጥ እንደኣሉት ኣኃዞች ፊደላዊ ነው። ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶክተሩ ከኣረቡ ሌላ ለኣሥሩ ኣኃዛዊ ቍጥሮች ከሰባት በላይ ምርጫዎች ሲኖራቸው ታይፕራይተሩ በኣንድ የእንግሊዝኛ ፊደል ምትክ የቀረበ ቴክኖሎጂ ስለሆነ ለኣንድም ግዕዛዊ ኣኃዝ ስፍራ ኣልነበነውም። የኣማርኛ ታይፕራይተር ኮምፕዩተራይዝድ ሲደረግ ለፊደላት የነበረው 128 ስፍራዎች ብቻ ስለነበሩና ለኣማርኛም በቂ ቦታዎች ስለኣልነበሩት ግዕዝን በታይፕራተር ዲጂታይዝ ኣደረግን የሚሉት ፊደሉንና መጻፊያውን የሌላቸውየኣልነበራቸው ዋሾዎች ጭምር ናቸው። ፳፫. ለግዕዙ ግኝት ቀለም ቅርፅ የተጠቀሙት በእንግሊዝኛ እዝባራዊ ኣልቦ (Slashed zero) የሚባለውን ነው። [https://en.wikipedia.org/wiki/0_(disambiguation)] ከላቲኑ “o” (“ኦ”) ቀለም እንዲለይ የላቲኑም ኣልቦ ጠበብና ረዘም የተደረገ ስለሆነ ቅርፁ ወደ የግዕዝ ኣራት ቍጥር (“፬”)፣ ዓይኑ “ዐ” እና ፀሓዩ “ፀ” የቀረበ ስለሆነ እንዳያምታቱ ነው። ስለ ዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዝ ፈጠራ እስከኣሁንም ከኣልሰሙት መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይገኙበታል። [https://eotcmk.org/a/%E1%8B%A8%E1%8C%8D%E1%8A%A5%E1%8B%9D-%E1%89%81%E1%8C%A5%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%8A%A0%E1%8C%BB%E1%8C%BB%E1%8D%8D/] ፳፬. የግዕዝ ቍጥሮች ዩኒኮድ ውስጥ የኣሉት በፊደልነት ቢሆንም እንጠቀምባቸው። ሃያዎቹ የግዕዝ ኣኃዞች ፩/1 ፪/2 ፫/3 ፬/4 ፭/5 ፮/6 ፯/7 ፰/8 ፱/9 ፲/10 ፳/20 ፴/30 ፵/40 ፶/50 ፷/60 ፸/70 ፹/80 ፺/90 ፻/100 ፼/10,000 ናቸው። ምሳሌ፦ ሰኔ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም.።
 
===የግዕዝ ምልክቶች===
Anonymous user

Navigation menu